74237 Criminal law/ tax law/ value added tax (VAT)/ criminal liability of corporate bodies/ managers

አንድ የንግድ ድርጅት (ማህበር) የተጨማሪ እሴት ታክስ ህግንና ማሻሻያውን ተላልፏል በሚል በወንጀል ጥፋተኛ ሊሰኝና ሊቀጣ ስለሚችልበት አግባብ፣  የህግ ሰውነት የተሰጠው (legal personality) ድርጅት የወንጀል ተካፋይ ሊሆን የሚችልበት አግባብ፣  የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት ወንጀል እንዳደረገ ተቆጥሮ የሚቀጣው ኃላፊዎቹ ወይም ከሰራተኞቹ አንዱ ከድርጅቱ ሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የድርጅቱን ጥቅም በህገ ወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም ህጋዊ ግዴታን በመጣስ ወይም ድርጅቱን በመሳሪያነት ያለአግባብ በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ በአነሳሽነት ወይም በአባሪነት ወንጀል ሲያደርግ ስለመሆኑና የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በወንጀል ተከስሶ የጥፋተኛነትና የቅጣት ወሣኔ እስከተሰጠበት ድርስ ድርጅቱ የወንጀሉ ተካፋይ እንደሆነ የሚቆጠር ስለሆነ ጥፋተኛ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 34(1),(2) አዋጅ ቁ. 285/95 አንቀጽ 56(1)

Download Cassation Decision