76786 civil procedure/ customary law/ summon/ court fee/ refund of court fee

የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ በግልጽ ያልሸፈናቸውና ለፍ/ቤት የቀረቡ ጉዳዮችን አካሄድ (አሰራር) በተመለከተ ህጉ ከመውጣቱ በፊት ተጽፈው በሥራ ላይ የነበሩ አግባብነት ያላቸው ህጐች እንደ አግባብነቱ ሥራ ላይ ሊውሉ የሚችሉ ስለመሆኑ፣ ክስ አቅርቦ ለከሳሽ የሚላከውን መጥሪያ ከፍ/ቤት ወጪ አድርጐ ነገር ግን ለተከሣሽ መጥሪያውን ከማድረሱ በፊት ክሱ እንዲቋርጥ ያደረገ ከሣሽ ለዳኝነቱ የከፈለው ገንዘብ በመሉ እንዲመለስለት የሚያቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ በፍ/ቤት ክስ የመሰረተ (ያቀረበ) ወገን የክስ መሰማቱ ሂደት ከመጀመሩ በፊት ክሱን በማንሣት መዝገቡ እንዲዘጋ ያደረገ ከሆነ ለዳኝነት ከከፈለው ገንዘብ ለፍ/ቤቱ በኪሣራ ስም የሚቀነሰው ተቀንሶ ቀሪው ገንዘብ ሊመለስለት የሚገባ ስለመሆኑ የፍብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 232(1) (ለ) ,245(4),3,278(1) የህግ ክፍል ማስታወቂያ 177/74 አንቀጽ 11

Download Cassation Decision