80241 property law/ possessory action/ contract of rent

የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ የሚቻለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ነገር በቀጥታ ወይም በጥበቃ ሥር የሆነ ይዞታ ሲኖረው ስለመሆኑ፣  የይዞታ ክስ የሚቀርበው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት በወቅቱ ለመያዝ ምንም አይነት መብት በሌለው ሰው ላይ ስለመሆኑ፣  የሁከት ይወገድልኝ ክስ የሚያቀርብ ሰው ንብረቱ በይዞታው ሥር የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚዉ የኃይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጥር ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን ማስረዳት ያለበት ስለመሆኑ፣ የሁከት ተግባር ተፈጥሯል ለማለት ባለይዞታ የሆነው ሰው በይዞታው ሥር በሚገኘው ንብረት እንዳይገለገልበት ሌላ ሰው ጣልቃ ገብቶበት መሰናክል ወይም ረብሻ የፈጠረበት ስለመሆኑ መረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ፣  በህግ አግባብ በተደረገ የኪራይ ውል መነሻነት ይዞታን በእጁ ያደረገ ሰው (ተከራይ) ላይ አከራይ የሚያቀርበው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣

Download Cassation Decision