Search laws, cases

 

Cassation Index volume 1-18

 
 • ለህፃን ልጅ ማሳደጊያ ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ወላጅ፣ የሚከፍለውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ ለመወሰን ግምት ውስጥ ሊገቡ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች የተሻሻለው ፌዴራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 197 (2) ፣202

  Download Cassation Decision

 • በ ጋብቻ በተሳሰሩ ባልና ሚስት መካከል ከአንዱ ጋር የውል ግዴታ የገባ ሰው በዋናው ክርክር ሁለቱን አጣምሮ ሊከስ የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ እንዲሁም ተዋዋይ በሆነው ተጋቢ ላይ የተሰጠ ውሳኔ የተጋቢዎች የጋራ እዳ ነው ወይስ የተወሰነበት ተጋቢ የግል እዳ ነው የሚለው ክርክር ሊነሳ የሚችለው በአፈጻጸም ወቅት እንጂ ሌላኛው ተጋቢ ሊከሰስም ሆነ ሊፈረድበት ስላለመቻሉ፡-

  Download Cassation Decision

 • የጉዳት ካሳ ጥያቄ ከጋብቻ ፍቺ ጋር ተያይዞ የቀረበ በሆነበት እና ጉዳቱም የደረሰው ከፍቺው ጋር ተያያዞ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ጥያቄው የባልና ሚስት ፍቺን ተከትሎ ከሚነሳ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ጋር በአንድ ላይ ሊስተናገድ አይችልም በሚል የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፡- የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 84Download Cassation Decision

 • አ ንድ የንግድ ቤት በኪራይ የተሰጠው በትዳር ግንኙነት ወይም በጋብቻ ውስጥ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ የንግድ ፈቃድ የተሰጠው ከትዳር ግንኙነት በፊት መሆኑ ብቻ የንግድ ሱቅ ከጋብቻ በፊት የተገኘ የግል ንብረት ነው ለማለት የማያስችል ስለመሆኑ፣

  Download Cassation Decision

 • በ ኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ ጋብቻ በፍቺም ሆነ በሞት ምክንያት ሲፈርስ ንብረት የሚጣራበት አግባብ በውል ወይም በስምምነት ተለይቶ ባልተቀመጠበት ሁኔታ የባልና ሚስት ሀብት የሚጣራው በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 113 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ስለመሆኑ፡- ኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 በአዋጅ ቁጥር 83/96 እንደተሻሻለው አንቀጽ 93

  Download Cassation Decision

 • ባ ል እና ሚስት በጋራ ሲጠቀሙበት የነበረ መሬት ጋብቻው በአንደኛው ተጋቢ ሞት የተቋረጠ ቢሆንም ሌላኛው ተጋቢ በሌላ ህጋዊ ምክንያት መብቱ እስካልተቋረጠ ድረስ ይዞታው በስሙ ተመዝግቦ ደብተር ለማግኘት እና በይዞታው ለመጠቀም የሚችል ስለመሆኑ፣ ሴቶች መሬትን በመጠቀም፤በማስተላለፍ፤በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 35/7/፣ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አዋጅ ቁ. 130/99 አንቀጽ 6/3/ እና ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 15

  Download Cassation Decision

 • የ ባልና ሚስት ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ ለአፈፃፀም የቀረበ አከራካሪ የሆነ ቤት ሊካፈልም ሆነ ሊሸጥ የማይችል ሲሆን ሊካፈል የሚችለው በፕሮፖርሽን / በተነጻጻሪ ካርታ / ነው በማለት ባለሙያ አስተያየት በተሰጠበት ሁኔታ በዚሁ አግባብ ክፍፍሉ ሲደረግ የበለጠ ይዞታ የደረሰው ወገን ለሌላው ወገን ግምቱን እንዲከፍል በማድረግ መፈፀም የሚገባው እንጂ በፍርዱ በተቀመጠው ሌላ አማራጭ መሠረት ክፍፍሉ እንዲፈጸም ማድረግ የማይገባ ስለመሆኑ፡- የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 91(1)እና(2)

  Download Cassation Decision

 • ባልና ሚስት በፍቺ ከተለያዩና የንብረት ክፍፍል ከተደረገ በኋላ ከአንደኛው ተጋቢ የግል ተግባር የሚመነጭ ዕዳ አፈፃፀም የተጠየቀው /የቀረበው/ ከፍቺ በኋላ እስከሆነ ድረስ ለዕዳው ምክንያት ከሆነው ተጋቢ ብቻ የሚጠየቅ ስለመሆኑ

  Cassation Decision no. 22930

 • የፍ/ብ/ህ/ቁ. 658 ተጋቢ ወገን ከሦስተኛ ወገን ጋር ያደረገውን ውል ለማፍረስ ምክንያት ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 658, 686

  Cassation Decision no. 28663

 • Download Cassation Decision

 • ከጋብቻ በፊት የግል የነበረን ንብረት መነሻ በማድረግ በጋብቻ ጊዜ በግብይት የተገኘ ንብረት የግል ሆኖ ሊቀጥል የሚችለው በፍ/ቤት ቀርቦ የፀደቀ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 58(2) 57 62(2)

  Download Cassation Decision

 • የአንደኛው ተጋቢ ስምምነት ሣይኖር የጋራ የሆነ የማይንቀሣቀስ ንብረት በሌለኛው ተጋቢ የተሸጠ እንደሆን ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢ ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ 6 ወር ውስጥ እንዲሁም በማናቸውም ሁኔታ ደግሞ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየት ስለመቻሉ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 69(2)

  Download Cassation Decision

 • በጋብቻ ውል ላይ ባልና ሚስት “መተዳደሪያችን” ነው በሚል ያመለከቷቸው ንብረቶች የጋራ ንብረት ተደርገው የሚቆጠሩ ስለመሆናቸው

  Download Cassation Decision

 • ቀደም ብሎ የተሰጠን የፍች ውሣኔ ወደጐን በመተው አዲስ የተደረገን ጋብቻ ህገ ወጥ ነው ማለት የማይቻል ስለመሆኑ

  Download Cassation Decision

 • በጋብቻ ላይ የተደረገ ጋብቻ ከጅምሩ ውጤት አልባ ነው (void ab initio) ሊባል የሚችል ስላለመሆኑ የጋብቻ ውል ተጋቢዎች ንብረታቸውን በተመለከተ ጋብቻው የሚያስከትለውን ውጤት ስምምነት የሚያደርጉበት ሰነድ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 42 44 33 1

  Download Cassation Decision

 • አንድ ተጋቢ በግሉ ያመጣው ዕዳ ከሌለኛው ተጋቢ የጋራ ንብረት እንዲከፈል የሚደረገው ዕዳውን ያመጣው ተጋቢ ዕዳውን ለመክፈል አለመቻሉ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የደቡ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ እና የፌዴራል መንግስት የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ

  Download Cassation Decision

 • ፀንቶ ባለ ጋብቻ ውስጥ የተወለደ ልጅ አባት በጋብቻ ውስጥ ባል የሆነው ወገን ስለመሆኑና የዚህን ሰው አባትነት ለመቃወም የሚቻልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 144 126 167 168 173

  Download Cassation Decision

 • ጋብቻ በሁለት የተለያዩ ሥርዓቶች የተፈፀመ ቢሆንም አንድ ጊዜ በህግ አግባብ የተደረገ ፍቺ በቂና ሙሉ ህጋዊ ውጤት የሚያስከትል ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 75(ሐ)

  Download Cassation Decision

 • ጋብቻ ህጋዊ ውጤት የሚኖረው በህግ አግባብ ተፈፅሟል ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 28(3)

  Download Cassation Decision

 • ልጅነት ሊረጋገጥ የሚችልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 156 168 158 169

  Download Cassation Decision

 
 
 

Google Ad