criminal law

  • ፍ/ቤት በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰን ሰው በተመለከተ አስቀድሞ የፈቀደውን የዋስትና መብት በራሱ አነሳሽነት ወይም በማናቸውም ባለጉዳይ አመልካችነት አዲስ ነገር ተከስቷል ብሎ ካመነ ዋስትናው እንዲነሳ ትዕዛዝ ሊሰጥ የሚችል ስለመሆኑ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 74

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ድርጊት በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ያደረሰ ሰው ከጉዳቱ በኋላ ተጐጂውን ወደ ህክምና ቦታ የወሰደው መሆኑ ብቻ በድርጊቱ የተፀፀተ መሆኑን ያሳያል በሚል ቅጣትን ከመነሻው በታች በመወረድ ቀልሎ እንዲወሰን ለማድረግ የሚያስችል ስላለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 543/3/, 59/1/, 575/2/, 82/1/ የትራንስፖርት ማሻሻያ ደንብ ቁ. 279/56 አንቀጽ 35

    Download Cassation Decision

  • በኤግዚቢትነት በፖሊስ ከተያዙ ንብረቶች ጋር በተገናኘ የንብረቶቹ ባለቤት ነኝ የሚል ወገን ንብረቱ ይመለስለት ዘንድ በፖሊስ ጽ/ቤቱ ላይ የሚያቀርበው ክስ በተገቢው ማስረጃ ተጣርቶ እልባት ሊሰጠው የሚገባ ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • የሰበር ችሎት ፍሬ ጉዳይ የማጣራት ማስረጃ የመመዘንና የመመርመር ስልጣን የሌለው ቢሆንም በሥር ፍ/ቤቶች ወይም የዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው ሌሎች አካላት መሰረታዊ የሆነ የዳኝነት አካሄድ ስርዓትን ሳይከተሉ፣ መመስረት የሚገባቸውን ጭብጥ ሳይመሰርቱና ጭብጡን የማስረዳት ግዴታ (Buden of proof) ያለበት ተከራካሪ ወገን የማስረዳት ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ ሳያደርጉና መጣራት ያለበትን (የሚገባውን) ፍሬ ጉዳይ ሳያጣሩ የሰጡትን ውሣኔ በሰበር አይቶ ለማረም ስልጣን ያለው ስለመሆኑ፣ በወ/ህ/አ. 419

    Download Cassation Decision

  • በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ክስ የቀረበበት ሰው በዋስትና ወረቀት ለመለቀቅ የሚያቀርበውን ጥያቄ ፍ/ቤቶች ተከሳሹ በቀረበበት የሙስና ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝ ሊጣልበት የሚችለውን የቅጣት ጣሪያ መነሻ በማድረግ ውሣኔ ሊሰጡበት የሚገባ ስለመሆኑ ተከሳሹ የተከሰሰበት ወንጀል ከአስር ዓመት በላይ በእስራት ሊያስቀጣ የሚችል በሆነ ጊዜ በዋስትና ወረቀት እንዲለቀቅ ሊፈቀድ የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 434/97 አንቀጽ 4/1/ አዋጅ ቁ. 239/93 አንቀጽ 2 አዋጅ ቁ. 236/93 የወንጀል ህግ ቁጥር 676/1/

    Download Cassation Decision

  • አንድ የወንጀል ድርጊት በእርግጥም ተጀምሯል /ተፈጽሟል/ ለማለት የሚቻለው የተደረገው ተግባር በማያጠራጥር ሁኔታና በቀጥታ ወንጀሉን ለመፈፀም ወደታሰበለት ግብ ለማድረስ የተደረገ መሆኑን ለማረጋገጥ ሲቻል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 27/1/ 540 555/ሀ//ለ/

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ተከስሶ የቀረበ ተጠርጣሪ በፍ/ቤት በሰጠው የእምነት ቃል መሰረት ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣት ከተጣለበት በኋላ በተሰጠው የጥፋተኝነት ውሣኔ ላይ ይግባኝ ለማለት የማይችል ስለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • በጉምሩክ ወንጀል የተከሰሰ ሰው በነፃ የተለቀቀ ቢሆንም ወንጀሉ የተፈፀመበት እቃ ወይም ማጓጓዣየሚወረሰው የጉምሩክ ህግን የመተላለፍ ድርጊት ስለመፈፀሙ ፍርድ ቤቱን የሚያጠግብ ማስረጃ ሲቀርብ ስለመሆኑና ማስረጃው አጥጋቢ ካልሆነ ብቻ ፍ/ቤት እቃውን (ማጓጓዣውን) እንዳይወረስ በማድረግ ተገቢውን ቀረጥና ታክስ እንዲከፈል ሊያዝ የሚገባው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀፅ 104(3)(ሀ), 104(3)(ለ)

    Download Cassation Decision

  • ከመንግስት ሰራተኞች ውጪ በሆኑ ሰዎች የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎችን በተመለከተ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ክስ ሊያቀርብ ስለመቻሉ ኮሚሽኑ የወንጀል ክስ ለመመስረት ስልጣን ከተሰጠው ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ወይም ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ የተከሰሰ ሰው ከሙስና ወንጀሉ ጋር አንድ ላይ መከሰስ ያለበትን የወንጀል ድርጊት አንድ ላይ (አጣምሮ) ሊያቀርብ ስለመቻሉ የወ/ህ/ቁ 379(2), 375, 404(4)(3) አዋጅ ቁ. 434/97 አንቀፅ 58 አዋጅ ቁ.236/93 አንቀፅ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ.110

    Download Cassation Decision

  • ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ በሥር ፍ/ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ እውነታ የተጠቀሰውን ወንጀል የሚያቋቁም መሆን አለመሆኑ ጉዳይ የህግ ጭብጥ በመሆኑ በሰበር ችሎት ሊመረመር የሚችል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር 675/1/

    Download Cassation Decision

  • ከጉምሩክ ባለስልጣን ሹም ፈቃድ ሳያገኝ በመተላለፍ ላይ ያሉ ወይም የጉምሩክ ወደብ በደረሱ ወቅት የእቃ መያዣ ላይ የተደረገን ማሸጊያ መፍታት በወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ በጉምሩክ ወደብ በምርመራ ላይ ካሉ ዕቃዎች ለሳምፕልነት በሚል ወስዶ አለመመለስ በወንጀል የሚያስጠይቅ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀፅ 100, 95(ሀ)

    Download Cassation Decision

  • ውልን /ስምምነትን/ መሰረት ባደረገ ግንኙነት አንድን ንብረት ወስዶ በውሉ መሰረት ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽሟል በሚል የወንጀል ክስ ሊቀርብበት የማይቻል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 23/2/, 24, 57, 58

    Download Cassation Decision

  • በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ከአንድ አይነት የወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዘ በሁለት የተለያዩ የወንጀል ክሶች የተከሰሰ ተጠርጣሪ በአንዱ የወንጀል ክስ የተመለከቱ ፍሬ ነገሮች መከሰት ጋር በተገናኘ ጥፋተኛ ለማለት ያልተቻለ እንደሆነ በሌላኛው ክስ ጥፋተኛ ለማድረግ የማይቻል ስለመሆኑ የወ/ህ/ቁ 407(ሐ), 670, 677 የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 141, 142, 149(1)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል የተከሰሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግላቸው ጠበቃ ለማቆም የማይችሉ በሆነ ጊዜ በመንግስት ወጪ የጠበቃ ድጋፍና እርዳታ ሊያገኙ የሚችሉበት አግባብ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 20(5) አዋጅ ቁ.27/88 አንቀፅ 35 አዋጅ ቁ.123/90 አዋጅ ቁ.27/885

    Download Cassation Decision

  • ተጨማሪ ማስረጃን ከመቀበል ጋር በተያያዘ በወንጀል ህግ ቁጥር 143/2/ ሥር የተመለከተው ድንጋጌ ፍ/ቤቱ ለፍትህ አሰጣጥ ተገቢ ነው ብሎ ሲያመን ትዕዛዝ ሊሰጥበት የሚችል ስለመሆኑ በፈቃጅነት (permissive) የተቀመጠ እንጂ አስገዳጅ የህግ ድንጋጌ ስላለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 143/2/

    Download Cassation Decision

  • አንድ የወንጀል አፈፃፀም ተግባር ሙከራ ደረጃ ላይ ደርሷል (Attempt) ሊባል የሚችልበት አግባብ የወ/ህ/አ 32(1)(ሀ),27(1),671(1)

    Download Cassation Decision

  • በፍ/ቤት የወንጀል ክስ ቀርቦ የጥፋተኝት ውሣኔ በተሰጠበት የወንጀል ድርጊት ወንጀለኛው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ያገኘው ንብረት ለመንግስት እንዲወረስ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ 98(1)(2),

    Download Cassation Decision

  • አንድ ወኪል ከወካዩ በውክልና ስልጣኑ የወሰደውን ንብረት ለመመለስ ፈቃደኛ ያለመሆኑ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 676(2) ድንጋጌ መሰረት ሊያስጠይቀው ስለመቻሉ የወ/ህ/ቁ 676(2)

    Download Cassation Decision

  • ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ በመገኘት ወንጀል አንድ ሰው ተጠያቂ የሚሆነው የምዝገባ ሥርዓት የተዘረጋ እንደሆነ ብቻ ነው ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ ስላለመኖሩ የወ/ህ/ቁ.419

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ህግ ቁጥር 448 ስር አንድ ሰው ለፍትህ እርዳታ ለመስጠት እንቢተኛ ሆኗል በሚል ወዲያውኑ ጉዳዩን በያዘው ፍ/ቤት ለመቅጣት ስለሚቻልበት አግባብ የወ/ህ/ቁ 448(1), (3), 23(2), 58

    Download Cassation Decision