criminal law

  • ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ የዋስትና ጥያቄን ላለመቀበል ሥልጣን (discretion) ያላቸው ስለመሆኑ፣ ዋስትናን ለመከልከል ፍ/ቤቶች የሚሰጡት ምክንያት በቂና ህጋዊ ናቸው ሊባሉ የሚችሉበት አግባብ፣ የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ.67

    Download Cassation Decision

  • “የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት” በሚል በወንጀል ህጉ ውስጥ የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት ለማቋቋም ቼኩ ለክፍያ ባንክ በቀረበበት ጊዜ በቂ ስንቅ የሌለው መሆኑን /ያለመኖሩ ማረጋገጥ ብቻ በቂ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁ. 693/1/

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰ ሰው የሚያነሳው የጤና ችግር ከዋስትና መብት አኳያ ሲታይ ስላለው ህጋዊ ጥበቃ

    Download Cassation Decision

  • የተጨማሪ እሴት ታክስን ተግባራዊ ለማድረግ በወጣው አዋጅ ቁ.285/94 አንቀጽ 49 መሰረት በወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ተከሳሽ ላይ ቅጣት ሊጣል ስለሚችልበት ሁኔታ፣ አዋጅ ቁ.285/94 አንቀጽ 49,47,50(2) የወ/ህ/አ 2(2)

    Download Cassation Decision

  • ለግል አገልግሎት ከቀረጥና ከታክስ ነፃ የገባን መኪና ለብድር መያዣነት መስጠት በወንጀል ኃላፊነትን (ተጠያቂነትን) የሚያስከትል ስለመሆኑ በወንጀል ጉዳይ በቅጣት መልክ የሚጣለው የገንዘብ መቀጮ በፍ/ብሔር ጉዳይ ከሚኖረው የአንድነትና የነጠላ ኃላፊነት የተለየ ስለመሆኑና ቅጣቱ በእያንዳንዱ አጥፊ ላይ ለየብቻ ሊጣል የሚገባው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.345/95 አንቀጽ 73(1) አዋጅ ቁ. 60/89 አዋጅ ቁ.280/94 የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ), 41

    Download Cassation Decision

  • የግንባታና የኮንስትራክሽን ማዕድን ማውጣት ሥራ ጋር በተያያዘ በሚመለከተው የመንግስት አካል የተሰጠ የፀና ፈቃድ ሣይኖር ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የመግዛትና የመሸጥ ውል መፈፀም በወንጀል ተጠያቂነትን ሊያስከትል ስለመቻሉ ህገ ወጥ ወይም ወንጀል ስለመሆኑ የተደነገገ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የተደረጉ ውለታዎችን (ውሎችን) በህግ ኃይል እንዲፈፀሙ በሚል ለፍ/ቤት ጥያቄውን በቀረበ ጊዜ ዳኞች ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ የሚገባቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1718, 1716 የወ/ህ/ቁ.353(1)(ለ) አዋጅ ቁ.52/85 አንቀፅ 53(5) ደንብ ቁ.182/86 አንቀፅ 39

    Download Cassation Decision

  • የንግድ ፈቃድ መብትን መጣስ በአዋጅ ቁ. 501/98 መሰረት የወንጀል ተጠያቂነትን ስለሚያስከትልበት አግባብ

    Download Cassation Decision

  • ከቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጋር በተያያዘ የፊልም ባለቤት ለመሆን በማሰብ በባለሃብትና ፊልሙን ለመስራት በሚል በተደረገ ስምምነት መነሻነት ፊልሙን ለህዝብ ከማቅረብ ጋር ተያይዞ ጉዳዩ በፍ/ብሔር ክርክር ተደርጐበት በተሰጠ ውሣኔ መሰረት ፊልሙን በእጅ አድርጐ መገኘት በወንጀል ተጠያቂነት የማያስከትል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.410/96 አንቀፅ 7(1)(ሀ), 36(1) የወ/ህ/ቁ.23(2), 57-59

    Download Cassation Decision

  • የሥራና ሠራተኛን ማገናኘት አዋጅ ቁ.632/2002 በመተላለፍ ሊኖር ስለሚችለው የወንጀል ተጠያቂነት ከቀረበ የወንጀል ክስ ጋር በተያያዘ የግል ተበዳይ የሆነ ሰው ቀርቦ ካልመሰከረ በስተቀር ክሱን ለማስረዳት የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተከሳሹን ጥፋተኛ ለማለት ብቁ አይደሉም ሊባል የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.632/2002 አንቀፅ 16(1)(መ), 18(1)(ሀ), 20(2), 40(3)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በወንጀል ህግ አንቀጽ 598(2) መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ውጪ አገር ልኳል በሚል ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ ስለሚችልበት አግባብ የወ/ህ/ቁ 598(2)

    Download Cassation Decision

  • ማንኛውም ሰው በወንጀል ህግና ሥርዓት መሠረት ተከስሶ የመጨረሻ በሆነ ውሣኔ ጥፋተኝነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም (Principle of Double Jeopardy) በሚል የሚታወቀው የወንጀል ህግ መርህ ሊተረጐምና ሥራ ላይ ሊውል የሚችልበት አግባብ፣ አንድ በወንጀል የተከሰሰ ሰው በድጋሚ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በአንድ ጉዳይ በድጋሚ ያለመከሰስና ያለመቀጣት መብቴ ተጥሷል በሚል ክርክር ለማቅረብ ሊሟሉ ስለሚገቡ ህጋዊ መስፈርቶች፣ ዐቃቤ ህግ በአንድ ተከሳሽ ላይ የወንጀል ክስ ከማቀርቡ በፊት ተከሳሹ አንድ ወንጀል በመፈፀም ሀሣብ የሠራው አንድ የወንጀል ድርጊት ያስከተላቸውን ወይም ሊያስከትላቸው የሚችላቸውን ውጤቶች ሁለተናዊ በሆነ መንገድ በማገናዘብ አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች በመለየትና በመጥቀስ የወንጀል ክሱን በጥንቃቄ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ 2(5), 24(1) የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130,131, 41, 111, 112 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ህግ መንግስት አንቀጽ 23,13(2)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ በተሰጠ ውሣኔ ቅሬታ ያለው ወገን ይግባኙን ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ለማቅረብ በህጉ ተለይቶ ስለተመለከተ የጊዜ ገደብ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 187(2)

    Download Cassation Decision

  • ተከሳሽ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በተመለከተ በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት ሊያቀርባቸው ስለሚችላቸው መከራከሪያዎች  ተከሳሽ በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት የሚያቀርባቸው መቃወሚያዎች በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130 ላይ የተመለከተቱት ጉዳዬች ጋር ብቻ በተገናኘ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  ማንኛውም ሰው የወንጀል ክስ ሲቀርብበት የተከሰሰበት የወንጀል ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈፀሙ ወይም አለመፈፀሙ ወንጀል መሆኑ ካልተደነገገ በስተቀር ሊቀጣ የማይችልና ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ተፈፃሚ በነበረው ህግ ከተመለከተው የቅጣት ጣሪያ በላይ ሊቀጣ የማይችል ስለመሆኑ፣  የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራ ስለመሆኑና ዳኞች ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ክስ የቀረበበት ድርጊት ወንጀል ስለመሆኑ የሚደነግገው ህግ ፀንቶ በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት መሆኑን ከተረዱ በማናቸውም ጊዜ አንስተው ውሣኔ ለመስጠት የሚችሉ ስለመሆኑ፣  ፍ/ቤቶች በዐ/ህግ የቀረበ የወንጀል ክስ በህገ-መንግስቱና በወንጀል ህጉ የሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር የተቀመጡ መርሆዎችና ድንጋጌዎችን የሚያሟሉ መሆን አለመሆኑን በመመርመር የመወሰን ግዴታ ያለባቸው ስለመሆኑ፣ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 5(2) ,13(1), 22(1 ) የወ/ህ/አ. (414/96)3,402,419,5(2) የወ/ህ/ቁ.(214/74) አለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ስምምነት (ICCPR) አንቀጽ 15(1) የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130(2)(1)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብቱ በፍ/ቤት ከተከበረለት በኋላ ህጋዊ ምክንያቶችን በማቅረብ የዋስትና መብቱን በመተው ያስያዘው ገንዘብ ተመልሶለት ጉዳዩን ማረሚያ ቤት ሆኖ ለመከታተል የሚያቀርበውን ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • የትራፊክ ደንብ መተላለፍ ጋር በተያያዘ የክስ ቻርጅን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆን በወ/ህ/አ.438 በየመንግስት ሥራን ማሰናከልና የመተባበር ግዴታን መጣስ ወንጀል ሊያስጠይቅ ስለመቻሉ፣ የወ/ህ/አ.348

    Download Cassation Decision

  • አንድ ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ በሚል ፍ/ቤት በሚሰጠው ብይን ላይ ይግባኝ ለማቅረብ የሚያስችል የህግ መሠረት የሌለ ስለመሆኑ የሙስና ክስ ከሚመራበት ሥርዓት ጋር በተገናኘ ተከሳሽ የሆነ ተከራካሪ ወገን ይግባኝ ለማቅረብ ስለሚችልባቸው ህጋዊ ጉዳዮች፣ ለሰበር ችሎት የሚቀርቡ ማናቸውም ጉዳዮች የይግባኝ አቅራረብ ሥርዓትን ያጠናቀቁና የመጨረሻ ፍርድ የተሠጠባቸው መሆን የሚገባቸው ስለመሆኑ፣ አዋጀ ቁ. 25/88 አንቀጽ 22 አዋጀ ቁ. 434/97 አንቀጽ 36(2) 40, 55 አዋጀ ቁ. 236/93

    Download Cassation Decision

  • አንድ የንግድ ድርጅት (ማህበር) የተጨማሪ እሴት ታክስ ህግንና ማሻሻያውን ተላልፏል በሚል በወንጀል ጥፋተኛ ሊሰኝና ሊቀጣ ስለሚችልበት አግባብ፣  የህግ ሰውነት የተሰጠው (legal personality) ድርጅት የወንጀል ተካፋይ ሊሆን የሚችልበት አግባብ፣  የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት ወንጀል እንዳደረገ ተቆጥሮ የሚቀጣው ኃላፊዎቹ ወይም ከሰራተኞቹ አንዱ ከድርጅቱ ሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የድርጅቱን ጥቅም በህገ ወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም ህጋዊ ግዴታን በመጣስ ወይም ድርጅቱን በመሳሪያነት ያለአግባብ በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ በአነሳሽነት ወይም በአባሪነት ወንጀል ሲያደርግ ስለመሆኑና የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በወንጀል ተከስሶ የጥፋተኛነትና የቅጣት ወሣኔ እስከተሰጠበት ድርስ ድርጅቱ የወንጀሉ ተካፋይ እንደሆነ የሚቆጠር ስለሆነ ጥፋተኛ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 34(1),(2) አዋጅ ቁ. 285/95 አንቀጽ 56(1)

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በወ/ህ/አ. 675(1) የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት ፈጽሟል በሚል ሊከሰስና ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ ስለሚችልበት አግባብ፣ የወ/ህ/አ.675(1),23

    Download Cassation Decision

  • ፍ/ቤቶች በወንጀል ረገድ የሚሰጧቸው ማናቸውም ውሣኔ በወ/ህ/አ. 2 የተደነገገውን የህጋዊነት መርህ መሠረት በማድረግ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ ፍ/ቤቶች በወንጀል ጉዳይ ንብረት ወይም ሀብት እንዲወረስ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዲሆን በሚል ውሣኔ ለመስጠት የሚችሉት በወንጀል ህግ በግልጽ የተደነገገ ድንጋጌ የተመለከተ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣  በወንጀል ጉዳይ አንድ ንብረት (ሀብት) እንዲወረስ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ሊወሠን የሚችለው ንብረቱ (ሀብቱ) አንድን ሰው ለወንጀል ሥራ እንዲያነሳሳ ወይም ወንጀሉን ለመስራት እንዲረዳው ወይም ደግሞ ወንጀሉን ለፈፀመበት ዋጋ እንዲሆነው የተሰጠው ወይም ሊሠጠው የታቀደን ማንኛውም ጥቅም የተመለከተ ንብረት (ሀብት) ስለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለመሆኑ ወይም ንብረቱ (ሀብቱ) የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም ያገለገለ ወይም ሊያገለግሉ የሚችሉ ወይም የወንጀል ተግባር ፍሬ የሆኑ ማናቸውም ነገሮች ጋር የተያያዘ ወይም የተመለከተ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 98,100,140, 2(1) (2)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰን ሰው የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈፀሙ ለማስረዳት መቅረብ የሚገባው የማስረጃ አይነት ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተዛማጅነት ያላቸው ፍሬ ነገሮች ለማስረዳት የሚችልና ድርጊቱ ሲፈፀም አይቻለሁ ወይም/እና ሰምቻለሁ የሚል ቀጥተኛ ማስረጃ ብቻ ነው ለማለት የሚያስችል የህግ መሠረት የሌለ ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 137, 141, 149

    Download Cassation Decision