192732 tax law-tax free privilege-priority of creditors

ማንኛውም አካል ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ባስገባቸው እቃዎች በአንዱም ሆነ በሌሎቹ ወይም በሌላ ምክንያት የሚፈለግበት መክፈያ ጊዜው የደረሰ የታክስ እዳ መኖሩን የኢትየጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ያረጋገጠ እንደሆነ እዳው ተከፍሎ እስኪያልቅ በታክስ ከፋዩ ሀብት ላይ የቀዳሚነት መብት ስላለው በታክስ አስተዳደደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41(4) (ለ) መሰረት በማናቸውም የፍርድ ሂደት ዕገዳ በተደረገበት ወይም የአፈፃፀም ትዕዛዝ የተሰጠበት ንብረትን ባለስልጣኑ የመያዝ ስልጣን የሌለው መሆኑ የተመላከተ ቢሆንም ድንጋጌው ንብረትን የመያዝ ሁኔታን ብቻ የሚከለክል እንጂ ባለስልጣኑ የግብር እዳውን ለማስከፈል የሚኖረውን የቀደምትነት መብት የሚያሳጣ ስላለመሆኑ 
የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀፅ 73(3)፣ እና 130፣122(1)፣ 6 እና  የታክስ አስተደዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንቀፅ 39(1 እና 2) 

ከቀረጥ ነጻ የገባ ንብረት ተመልሶ እስካልወጣ ድረስ ተገቢው የግብር እዳ ተከፍሎበት ሀገር ውስጥ የሚቀር በመሆኑ ለግብር እዳ በዋስትና ሊያዝ የሚችል ስለመሆኑ 

Download