109441 evidence law/ circumstantial evidence

የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ የአስረጅነት ብቃት ያለው ተአማኒነት ያለው ማስረጃ ተደርጎ እንዲወስድ ሚዛን ላይ ሊቀመጡ ስለሚገባቸው ነገሮች

 

የሰ/መ/ቁ. 109441 ቀን 17/05/2008 ዓ/ም

ዳኞች፡- አልማው ወሌ

 

ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንደሻው አዳነ ቀንዓ ቂጢታ

አመልካች፡- ፈይሳ ማም ማሩ የቀረበ የለም ከተበለ በኃላ አዲስ መሀመድ ቀረቡ

 

ተጠሪ፡-   የፌዴራል   ዐቃቤ  ህግ  -  የቀረበ   የለምመዝገቡን   መርምረን  የሚከተለውን  ፍርድ ተሰጥተናል፡፡

 

 ፍ ር ድ

 

1. ጉዳዩ የቀረበው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች የወንጀል ህግ አንቀጽ  540 የተመለከተውን በመተላለፍ ሟች ቁምቢ በዳሳን የመግደል ወንጀል ፈጽሟል በማለት የሰጡት የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በህግ አግባብ የተሰጠነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው፡፡ ጉዳዩ በመጀመሪያ  የተያው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ተጠሪ አመልካች በወንጀል ህግ አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ/ም ሰዓቱ በውል ተለይቶ በውል ባልታወቀ ጊዜ በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 20/21 ሃያት ኮንደሚኒያም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ አብሮት ከኦሮሚያ ክልል ሰንደፈ ወረዳ ቀርሳ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ወደ አዲስ አበባ የመጣውን ሟች ቁንቢ በዳሳ ምንነቱ ባልታወቀ ነገር ጭንቅላቱን በመምታት በደርሰበት ጉዳት ህክምና ሲከታተል ቅይቶ ሀምሌ 18 ቀን 2003 ዓ/ም ህወይቱ እንደያልፍ በማድረጉ ተራ የሰው መግደል ወንጅ ፈጽሟል በማለት የወንጀል ክስ አቅርቧል፡፡


2. አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክሯል፡፡ ተጠሪ ክሱን ያስረዳልኛል በማለት የሰውና የጽሁፍ ማስረጃ አቅርቧል፡፡ የተጠሪ የሰው ምስክሮች ቃል በተመለከተ ፤ አንደኛ የተጠሪ ምስክር ሟች አጎቷ መሆኑን ገልጻ ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት አከባቢ ሟች እና ተከሳሽ ከሰንደፋ ወደ አዲስ አበባ ስሄዱ አግኝቻቸው የት ልትሄድ ብየ ሟችን ስጠየቀው ልጄን ለመጠየቅ ወደ አዲስ አበባ እሄዳለሁ አለኝ፡፡ ሟች አዲስ አበባ ከተከሳሽ ጋር ከሄደ በኃላ በዚያው ሳያመለሰ ቀረ፡፡ ከዚያ ሟች ወድቋል ተብሎ እንደተነገራቸውና ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ሄደን ስናየው ጭንቅላቱ ቅስሎና ተፈንክቶ ነበር፡፡ በመጨረሻም ወደ ቤት የመጣና ያስታመመችው መሆኑን ሟች ወደ ቤት በመጣ ጊዜ መናገር ማይችል እንደነበር፣ ይህንን የፈጸመብህ ተከሳሽ ነወይ ብየ ሰጠይቀው በሟች በምልክት በአዎት መልስ ሰጥትኛል ምስክር ተከሳሹን የጠረጠረችው በመጀመሪያ ከሟች ጋር አዲስ አበባ አብሮ በመሄደና ተከሳሽም ሲሞት ለቀበር ያልመጣ በመሆኑ ምክንያት መሆኑን፤ ሟች በምልክት ለምስክር ምላሽ ከሰጠ ከአምስት ቀን በኃላ ህይወቱ ያለፈ መሆኑን የመሰከረች መሆኑን ከስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተረድተናል፡፡

3. ሁለተኛ የተጠሪ ምስክር የሟች እህት መሆኗን ገልጻ፣ ተከሳሽ ሟችን አዲስ አበባ ልጅህንና ሚስትህን ያሉበት ቦታ አሳይለሁ ብሎ ከቤት ይዞት  እንደወጣ አብረው እንደሄዱ የሰማች መሆኑን፤ ሟች ከቤት ከወጣ በኃላ ሳይመለስ እንደቀረና ከሁለት ሳንምንት በኃላ ዳግማዊ ሚኒሊክ የተኛ መሆኑ አንደወቁ ሟች  እግሩ፣ አንገቱና ጭንቅላቱ ተጎድቶ እንደነበር፤ ሟች ወደ ቤት ከመጣ በኃላ መልስ መስጠትና ከሰው ጋር መግባባት የማይችል መሆኑንና የሚገባባውም በምልክት እነደነበርና ሟች እሺ የሚል መልስ ብቻ ይሰጥ እንደነበር ተከሳሽን የጠረጠሩት አብርው ከቤት ወጥተው የት ጣለው በሚልና ሟች ከጠፋና ከታመመ ጊዜ ጀምሮ ተከሳሽ ፍለጋ አለማድረጉ ሟችንም አለመጠየቁን ሟችና ተከሳሽ ጠብ የሌላቸው መሆኑንና አንደኛ ምስክር ሟችን ድርጊቱ የፈጸመብህ ተከሳሽ ነዎይ ብያ ስጠይቀው በምልክት አዎ ብሎ መልሶልኛል ብላ እንደነገራቻትና ነግራኛለች፣ እኔ ሟች በምልክት ተከሳሽ ነው ብሎ መልስ ሲሰጥ አልሰማሁም፡፡ ሟች ብር 5000 (አምስት ሺ ብር) ይዞ ስለነበር ለብሩ ስል ገድሎታል ብላ እንደምታሰብ የመሰከረች መሆኑን ከስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተረድተናል፡፡

4. ሶስተኛው የተጠሪ ምስክር ሀምሌ 23 ቀን 2003 ዓ/ም ተከሳሽን ሲይዘው ተከሳሽ ለማምለጥ መከራ ያለማድረጉን እንደመሰከር በስር ፍርድ ቤት በውሳኔው አስፍሯል፡፡ በችሎት ያልቀረበው የተጠሪ ምስክር በበኩሉ ግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ/ም ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል አከባቢ በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ አያት ኮንደሚኒየም አከባቢ ሰው ተሰብስቦና ሟችን ውድቆ እንዳየና ከሟች አጠገብ ሁለት ዱላዎች እንደነበሩና


ሟችን ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የተወሰደ መሆኑን ገልጻ ለፖሊስ ቃሉን ያስመዘገበ መሆኑን እንደተረዳ የስር ፍርድ ቤት በውሳኔው ገልጿል፡፡ ተጠሪ ስለ ሟች አሞሞት የሚገልጽ የአስክሬን ምርምራ ውጤት የቀረበ መሆኑና ማስረጃው ሟች የሞተው በድብደባ ምክንያት ሁለቱም ሳንባዎቹና ጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት መሆኑን የሚገልጽ እንደሆነ ተረድተናል፡፡

5. የስር ፍርድ ቤት አመልካች መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ ብይን ሰጥቶ ሟች በምልክት ፈይሳ ነው ብሏል በተባለው መሰረት ሌለ ፈይሳ የተባለ ሰው ተይዞ እንደነበርና   ግንቦት 3 ቀን ስራ ስሰራ ወየ ማታ አስራ አንድ ሰዓት አከባቢ ባለቤቴ ስራ ቦታ መጥታ ተያይዘን ከአበልጃችን ጋር ሄደን እዚያ አድርን ግንቦት 4 ቀን 2030 ዓ/ም ወደ ቤታችን መመለሳችን ያስረደልናል በማለት ጭብጥ አስይዞ አራት መከላከያ ምስክሮችን ቃል አስምቷል፡፡ የስር ፍርድ ቤት የተከሳሽ መከላከያ ምስክሮች የሰጡት ቃል ተከሳሽ በጉዳዩ ተጠርጥሮ ሲያዝ ጳግሜ 3 ቀን 2003 ዓ/ም ለፖሊስ ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ/ም ከሟቸው ጋር ቀርስ ምላስ ሰንበር በልተን ማወራረጃ አንድ አንድ ብርሌ ጠጅ ጠጥተው እንደተለያዩና ፤ ከሟች ጋር ከተለያዩ በኃላ ተከሳሽ በኮንትራት ጭቃ የመለጠፍ ስራ ሲስራበት ወደ ነበረው ጠጅቱ ቤት በመሄድ ጭቃ ሲለጥፍ ወሎ፣ ስራው ስላለቀለት ወ/ሮ ጠጀቱ ቤት አድሮ በማግስቱ ግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ/ም አምስት ሰዓት አከባቢ ወደ ቤቱ እንደተመለሰ በመግልጽ ከሰጠው ተከሳሽነት ቃል ጋር የሚቃረንና ታዓማኒነት የሌለው መሆኑን ገልጻ የአመልካችን የመከላከያ ምስክሮች ቃል ውድቅ አድርጎታል፡፡

6. የስር ፍርድ ቤት የተጠሪ ማስረጃ አመልካች በወንጀል ክሱ የተጠቀሰውን የህግ ድንጋጌ መተላለፍ ሟችን የገደለ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ተጠሪ ያቀረባቸው የመከላከያ ምስክሮች ቃል ተዓማኒነት የሌለውና የዐ/ህግን ማስረጃ የሚያስተባብል አይደለም  በማለት አመልካች (ተከሳሽ) በወንጀል ህግ አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ ሟችን በመደብደብ ህይወቱ እንደያልፍ ያደረገና ተራ የሰው መግደል ወንጀል የፈጸመ ጥፋተኛ ነው ብሎ ፤ አመልካች በአሰር አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡ አመልካች የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በመቃወም፤ ይግባኝ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቧል፡፡ ይግባኝ ሰሚው ችሎት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 195 ንዑስ አንቀጽ 2(ለ)2 መሰረት አጽንቶታል፡፡

7. አመልካች ጥር 20 ቀን 2007 ዓ/ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ አመልካች የወንጀል ድርጊቱን የፈጸምኩ ስለመሆኑ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት አቅርቦ የሰማቸው ምስክሮች አላስርዱም፡፡ የተጠሪ ምስክሮች የሰጡት ቃልም ሰፊ ልዩነት ያለበት የተጠሪ ምስክሮች በአከባቢው ከእኔ ሌላ ፈይሳ ቡሻ የሚባል ሰው እንዳለና ሟች ከሟች ፈይሳ ቡሻና ከአንድ


ልጅ ጋር ቁማር ስጫወት እንደነበር መስክረዋል፡፡ በመሆኑም አመልካች ወንጀሉን የፈጸምኩ ስለመሆኑ የቀረበብኝ በቂ ማስረጃ ሳይኖር፣ የሰው መግደል ወንጀል ፈጽመሀል ተብሎዬ የ ተወሰነብኝ የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት አመልክቷል፡፡ ተጠሪ ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ/ም በተጻፈ መልስ አመልካችና ሟች አንድ ላይ ወደ አዲስ አበባ የመጡ መሆኑንና ሟች ወደ ቤቱ ሳይመለስ መቅረቱና ሟች ህይወቱ ያለፈው በደብደባ በደረሰበት ጉዳት መሆኑ የተጠሪ ማስረጃ ተደጋጋፊ በሆነ ሁኔታ ያስረዳ በመሆኑ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት መልስ ሰጥቷል፡፡ አመልካች ታህሳስ 1 ቀን 2008 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል፡፡

8. ከስር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ ለዚህ ሰበር ችሎት ያቀረቡት የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ተጠሪ አመልካች ሟችን ሆነ ብሎ ባደረሰበት ድብደባ ህይወቱ እንዲያልገፍ ያደረግ መሆኑን የማስረዳት ግደታውን (Burdon of proof) የተወጣ መሆኑን መርምረናል፡፡ አመልካች የተከሰሰበትን ተራ የሰው መግደል ወንጀል እንዳለፈጸመ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ የሚገመት በመሆኑ አመልካች በህገ መንግስቱ የፀና ነው ተብሎ የመገመተ መብት ጠቃሚ ከማስረጃ የማፍረስና አመልካች ወንጀል የፈጸመ መሆኑን የማስረዳት ህጋዊ  ግደታ (Legal Burdon of proof) ያለበት አመልካችን በወንጀል የከሰሰው ተጠሪ ነው፡፡ ተጠሪ ይህንን የተጠሪን ጥፋተኝነት ማለትም ተጠሪ ወንጀል የፈጸመ መሆኑን የማስረዳት በህግ የተጣለበትን የማስረዳት ግደታውን የሚወጣው፣ አመልካች ወንጀሉን የፈጸመ መሆኑን በምን ደረጃ ማስረጃ በማቅርብ (Standard of proof) ሲያስረዳ እንደሆነ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 141 እና በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 149 ተደንግጓል፡፡

9. ከላይ ከተጠቀሱት የህገ መንግስቱና የወንጀል መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ድንጋጌዎች ይዘት ለመረዳት የሚቻለው፣ አመልካች ሟችን ሆነ ብሎ የገደል ስለመሆኑ ተጠሪ በበቂና አሳማኝ ማስረጃ የማስረዳትና የማረጋገጥ ግደታ አለበት፡፡ ተጠሪ ይህንን የማስረዳት ግደታውን በአግባቡ ካልተወጣ፣ መልካች የተጠሪን ማስረጃ የመከለካልም ሆነ የማስተባበል ግደታ አንደሌለበት የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 141 ድንጋጌ ይዘትና መሰረታዊ አላማ በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡ ከዚህ አንጻር ሲታይ፣ ተጠሪ ሟች ቁንቢ በዳሳ፣ ግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው አያት ኮንደሚኒየም አካባቢ፣ ግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ/ም ከጧቱ አንድ ሰዓት ተኩል ሲሆን ለጊዜው ማንነቱ ባልታወቀ ሰው ጭንቅላቱንና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ተደብደቦ ወድቆ መገኘቱ፣ ሟችን ወድቆ ያገኙት ሰዎች የህክምና እርዳታ እንደያገኝ


ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የወሰዱት መሆኑን፣ ሟች ከሆስፒታል እርዳታ ስደርግለት ከቆየ በኃላ ወጥቶ ወደ ቤቱ መሄዲን፣ ሟች ቤቱ ውስጥ በህመም ላይ ቆይቶ፣ ሀምሌ 18 ቀን 2003 ዓ/ም ከዚህ አለም ህይወቱ ያለፈ መሆኑን፤ ሟች የሞተው በድብደባው ምክንያት በጭንቅላቱና በሁለት ሳንባዎቹ ላይ በደረሰበት ጉዳት መሆኑን ተጠሪ ባቀረበው የሰውና የጽሁፍ ማስረጃ ተረጋግጧለው፡፡

10. ይህም ሟች ቁንቢ በዳሳ ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆነው ማንነቱ ባልታወቀ ወይም ባልታወቁ ሰዎች ትክክለኛ ሰዓቱ ተለይቶ ባልታወቀበት ሰዓት በተፈጸመበት ደብዳብ ምክንያት የደረሰበት ጉዳት መሆኑን የወንጀል ህግ አንቀጽ ት  24  በሚደነግገው መሰረት ተጠሪ የማስረዳት ግደታውን የተወጣ መሆኑን ከስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተርድተናል፡፡ ተጠሪ በህግ የተጣለበትን የማስረዳት ግዴታ የተወጣ መሆኑ አከራካሪ የሚሆነው ሟችን ደብዱቦ በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ አያት ኮንደሚኒየም ከሚባለው ልዩ ቦታ የጠለው ተከሳሽ (አመልካች) መሆኑን፣ በበቂ ሁኔታ አረጋግጧል ወይስ አላረጋገጠም? የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ነው፡፡

11. ተጠሪ አመልካች ሟችን ስደበድብ አይቻለሁ የሚል ቁጥተኛ ማስረጃ  (direct evidence) አላቀረበም፡፡ ተጠሪ ሟችን የገደለው አመልካች ነው በማለት ያቀረበውን የወንጀል ክስ ለማስረዳት የሞከረው ሟች ተደብድቦ ወድቆ ከመገኘቱ በፊትና ሟች ተደበድቦ ወድቆ ከተገኘ በኋላ የነበሩትን የአካባቢ ሁኔታ ነገሮች በማስረዳት፣ ፍርድ ቤቱ ሟችን የገደለው ተከሳሽ (አመልካች) ነው ወይም አይደለም ከሚለው ሎጅካል መደምደሚያ ላይ ለመድረስ የሚያስችሉ የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃዎችን ከማቅረብ ነው፡፡ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሰጠው አንደኛ የተጠሪ ምስክር አመልካችና ሟች ግንቦትን 3 ቀን 2003 ዓ/ም አንድላይ ወደ አዲስ አበባ ስሄዱ ማየቷን፣ አመልካች ሟች ጠፍቶ ስፈለግም ሆነ ታሞ እቤት በነበረበት ሰዓት ያልጠየቁ መሆኑን፣ አንደኛ ተጠሪ ሟች በምልክት የደበደበህ ተከሳሽ ነወይ? ብየ ስጠይቀው ተከሳሹ መሆኑን በምልክት መልስ ሰጥቶኛል በማለት የሰጠችውን የምስክርነት ቃል እና የስር ፍርድ ቤት በተጨማሪ ማስረጃነት ባስቀርበው የፖሊስ መርመራ መዝገብ ውስጥ አመልካች በወንጀለኛ መቀጫ ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር 27 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ለፖሊስ 3-13-2003 በሰጠው የተከሳሽነት ቃል “ተከሳሽ ከሟች ጋር ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ አብረው መጥተው አዲስ አበባ ከደርሱ በኃላ ቁርሳቸውን ምላስ  ሰንበር በልተው ማወራረጃ አንድ አንድ ብርሌ ጠጅ ጠጥተው የተለያዩ መሆኑን ተከሳሽ ከሟች ጋር ከተለያየ በኃላ ኮንትራት ጭቃ የመለጠፍ ስራ ይሰራበት ወደነበረው ወ/ሮ ጠጅቱ ቤት የሄደ መሆኑንና ከሳሽ የጭቃ ልጠፋው ስራ ያላለቀለት በመሆኑ ከወ/ሮ ጠጅቱ ቤት አድሮ በማግስቱ ግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ/ም ከቀኑ አምስት ሰዓት ወደ ቤቱ የተመለስ


መሆኑን በመግለጽ የሰጠውን የተከሳሽነት ቃል፤ እንድዚሁም የሟች እህት የሆነቸው ሁለተኛ ተጠሪ ምስክር ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ/ም አመልካች ከሟች ጋር ወደ አዲስ አበባ መሄዱን ሰዎች እንደነገሯት፣ ሟች ተከሳሽ ነው  የደበደበኝ  ብሎ በምልክት ነግሮኛል ብላ አንደኛ ተጠሪ የነገረቻት መሆኑን ሟች በምልክት  ይህንን ሲናገር እንዳላየች የሰጠችውን የምስክርነት ቃልና አንደኛ ሁለተኛ የተጠሪ ምስክሮች ተጠሪዎችን ታሞ በነበረበት ጊዜ ያልጠየቀው መሆኑንና በሟች ቀብር ስነ ስርዓት ላይ አመልካች ያልተገኛ መሆኑን በመግልጽ የሰጡት የምስክርነት ቃል አመልካች  ሟችን የገደለ መሆኑን የሚያረጋግጡ የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃዎች ናቸው በማለት እንደሆነ በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተረድተናል፡፡

12. የአከባቢ ሁኔታ ማስረጃ ወንጀሉን የፈጸመው ተከሳሽ መሆኑንና ከተከሳሽ ውጭ ሌላ ሰው ወንጀሉን ሊፈጽመው አይችልም በሚል መደምደሚያ ላይ ለማድረስ በቂና አሳማኝ በሆነ ሁኔታ የሚያስርዳ ሆኖ ሲገኝ የአስረጅነት ብቃት ያለው ማስረጃ ተደርጎ እንደሚወስድ የማስረጃ ብቃት መስፈርትና የማስረጃ አመዛዘን መርሆች ያሳያሉ፡፡ የአከባቢ ሁኔታ አንድን የተፈጸመ ወንጀል ለማስረዳት የአሰረጅነት ብቃት ያለው ማስረጃ የሚሆነው ወንጀሉ ከመፈጸሙ በፊት ወንጀሉ ከተፈጸመ በኃላ ስላላው ሁኔታ የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች (የአከባቢ ሁኔታዎች) ተከሳሽ ወንጀሉን ፈጽሞታል ከሚል እርግጠኛ መደምደሚያ ለመድረስ የሚያስችል ይዘትና ባህሪ ያላቸው ሲሆን፣ የአከባቢ ሁኔታ ማስረጃዎቹ ተያያዥነት ያላቸውና ክፍተት የሌለባቸው ሲሆኑ፤ የአከባቢ ሁኔታ ማስረጃዎቹ የተከሳሹ ጥፋተኝነት ወንጀል መምራት የሚያረጋግጡ አንጅ በተቃራኒው ተከሳሹ ንጸህ ነው ወንጀሉን አልፈጸመም ወደሚለው ሎጅካል መደምደሚያ የማይወሰደ ሲሆኑና የቀረቡት የአከባቢ ሁኔታ ማስረጃዎች በማናቸውም የሞራልና የህሊና መመዘኛ ወንጀሉ በተከሳሹ ሳይሆን በሌላ ሰው የመፈጸም እድልና አግጣሚ የሌለ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ለማስረዳት የሚችሉ ሆነው ሲገኙ እንደሆነ ተቀባይነት ያላቸው የማስረጃ ህግ መርሆች ያሳያሉ፡፡

13. ከዚህ አንጻር ሲታይ አመልካች ሟች አዲስ አበባ አብረው ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ/ም የወጡ መሆኑን፣ አመልካች ግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ/ም ወደ ቤቱ መመለሱና ሟች ሳይመለሰ መቅረቱ፣ ሟች በአዲስ አበባ የካ ከተማ አያት ኮንደሚኑየም ከተባለው አከባቢ ደብደባ ተፈጽሞበት ግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ/ም አንድ ሰዓት ተኩል አከባቢ ውድቆ መገኘቱ ሟች ላይ የሞት ጉዳት የደረሰበትን ድበዳቤ የፈጸመው አመልካች ስለመሆኑና ከአመልካች ውጭ ሟችን ሌላ ማን ሰው ሊደበድበው የማይችል ስለመሆኑ ሎጅካል መደምደሚያ ላይ የሚያድረሱ፣ ተያያዥነት ያላቸውና ክፍተቶ የማይፈጥሩ የአከባቢ ሁኔታ ማስረጃዎች ናቸው ብሎ ለመደምደም የሚያስችል አይደለም፡፡


14. ከላይ ከተገለጸው በተጨማሪ የስር ፍርድ ቤት ዕወነትነት ያለው ማስረጃ እንደሆነ በመውሰድ የአመልካችን የመከላከያ ምስክሮች ቃል ውድቅ ለማድረግ  አመልካች በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 27 ንዑስ አንቀጽ 2 የሰጠው የተከሳሽነት ቃል፣ አመልካችና ሟች ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ/ም አዱስ አበባ አብረው ከመጡ በኃላ ከሟች ጋር ምላስ ሰንበር ቀርሳቸውን በልተውና ማወራረጃ አንድ አንድ ብርሌ ጠጅ ጠጥተው የተለያዩ መሆኑን፣ አመልካች ከሟች ጋር ቀርስ በልተው ከተለያዩ በኃላ ኮንትራት ሲሰራው ጭቃ የመልጠፍ ስራ ሲሰራበት ወ/ሮ ጠጁቱ ቤት መሄዱን ከዚያ በኃላ ጭቃ የመለጥፈ ስራው ስላልተጠናቀቀለት ከወ/ሮ ጠጅቱ ቤት አድሮ ግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ/ም ብቻውን ወደ ቤት መመለሱን የሚገለጽ ማስረጃ ነው፡፡ የስር ፍርድ ቤት በተጨማሪ ማስረጃነት የቀር በትዕዛዝ ያስቀረበው ይህ አመልካች ለፖሊስ የሰጠው የተከሳሽነት ቃል፣ የአስርጅነት ብቃት እና ተዓማኒነት ያለው መሆኑን የስር ፍርድ ቤት በማረጋገጥ ለፍርድ ግበዕት አድርጎ ተጠቀሞበታል፡፡ ይህ ከሆነ የስር ፍርድ ቤት ለፖሊስ ከሰጠው የተከሳሽነት ቃል ውስጥ አመልካቹን የሚግዳውን ማለትም ከሟች ጋር ወደ አዲስ አበባ አብረው መምጣታቸውንና ቁርስ አብረው መብላታቸውን የሚገልጸውን የማስረጃነት ክፍል ለማስረጃነት ከያዘ በኃላ አመልካች ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ/ም አዲስ አበባ ከደርስንና ቁርስ ከባለን በኃላ እኔና ሟች ተለያይተናል፡፡ ከዚያ በኃላ እኔ በኮንትራት ጭቃ ወደምለጥፍበት ወ/ሮ ጠጅቱ ቤት ሄጄ፣ ወ/ሮ ጠጅቱ አድሬ በማግስቱ ብቻየን ወደ ቤት ተመልሻለሁ በማለት አመልካችን የሚጠቅመውን የማስረጃ ክፍል በማስረጃነት አልያዘለትም፡፡ ይህም የስር ፍርድ ቤት በትዕዛዝ ባስቀርበው የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ውስጥ ተይይዞ ያገኘውንና አመልካች በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 27(2) የሰጠውን የተከሳሽነት ቃል ከነሙሉ ይዘቱ ሳይሆን አመልካች ጥፋተኛነው ለማለት  የሚጠቅመውን የማስረጃውን ክፍል ብቻ ለፍርድ ግብዓት ያዋለና መሰረታዊ የማስረጃ አመዛዘን መርህ በመጣስ መሰረታዊ የህግ ስህተት የፈጸመ መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

15. እንደዚሁም ከላይ በተገለጸው በተጨማሪ አንደኛ ተጠሪ ሟች በምልክት ተከሳሽ እንደደበደበው ገልጾልኛል በማለት የምስክርነት ቃል የሰጠች ቢሆንም ሟች በምልክት ይህንን ሲገልጽ ከምስክር ውጭ ሌሎች ሰዎች ያላዩ መሆኑና የሟች የምልክት ቋንቋ ትክክለኛ መልዕክት ለመረዳት አስቸጋሪ በመሆኑ፣ የተጠሪ አንደኛ ምስክር ሟች በምልክት ቋንቋው ስለገለጸው ትክክለኛ መልዕክት ሳይሆን እሷ ይህንን ማለቱ ነው ብላ የገመተችውን የመሰከረች መሆኑን ስለሚያሳይ፣ አመልካች በቁጥጥር ሲወል ለማምለጥ አለመምከሩና ሌሎች ባህሪያቶችን አለማሳያቱን የተጠሪ ሶስተኛ ምስክር የመሰከር በመሆኑና ሁለተኛ ተጠሪ የሰጠችው የምስክርነት ቃል የሰሚ ሰሚ ማስረጃ በመሆኑ ማስረጃው በወ/መ/ስ/ህግ ቁጥር 137 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት ተቀባይነት ያለው ማስረጃ


ቢሆንም አመልካች ሟችን ስለመግደሉ ለማረጋገጥ የሚያስችል ይዘት የሌለው በመሆኑ፣ የተጠሪ የአከባቢ ሁኔታ ማስረጃም ሟች ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ/ም ከአመልካች ጋር ወደ አዲስ አበባ መጥቶ፣ አዲስ አበባ ከአመልካች ጋር ቁርስ ከበሉ በኃላ አመልካችና ተጠሪ ወደ ተለያየ አቅጣጫ ሄደዋል ወይስ አብረው አንድ ላይ ዉለዋል፣ አመልካች ግንቦት 3 ቀን 2003 ዓ/ም አዲስ አበባ ከደረሰ በኃላ ወደየት ቦታ እንደ ሄደ፣ ምን ሲሰራና እነ ማን ጋር እንደዋል፣ የማያስረዳና ክፍተት ያለበት በመሆኑ፣ ሌላው ቀርቶ ሟች ግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ/ም ወድቆ ከተገኘበት የካ ክፍለ ከተማ አያት ኮንደሚኒየም ከተባለው ቦታ ላይ ሟች ከወደቀበት ጎን ወድቀው ከተገኙት ሁለት ብትሮች አንደኛው የአመልካች ስለመሆኑ ተጠሪ በሰው ምስክር ወይም በሳይንስ ምርመራ ያላረጋገጠ በመሆኑ፣ ተጠሪ ሟች ሰዓቱ በውል ባልተወቀበት ጊዜ ማንነቱ ወይም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተደብድቦ ግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ/ም አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ አያት ኮንደሚኒየም ከተባለው ቦታ ወድቆ መገኘቱንና በድበደባው በደረሰበትን ጉዳት ህይወቱ ያለፈ መሆኑን ከማስረዳት ውጭ ሟችን የደበደብ አመልካች ስለመሆኑ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 141 በሚደነግገው መሰረት በቂና አሳመኝ የሆነ ማስረጃ በማቅረብ የማስረዳት ግደታውን አልተወጣም፡፡ ተጠሪ  የማስረዳት ግደታውን ባልተወጣበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤት አመልካችን በወ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 141 መሰረት በነጻ ማሰናበት ሲገባው ተጠሪ መከላከያ ማስረጃ እንደያቀርብ የሰጠው ብይንና በአመልካች ላይ የሰጠው የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ከላይ በዝርዝር የገለጽናቸውን የህግ ድንጋጌዎችና የማስረጃ ህግ መርሆች የሚጥስ ነው ይግባኝ ሰሚው ችሎት የስር ፍርድ ቤት ስህተት ሳያርም ፍርዱን ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችሎት የሰጡትን የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 195 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ሽረነዋል፡፡

 

 ው ሳ ኔ

 

1. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 113102 የሰጠውን  የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 101772 የሰጠውን ፍርድ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 195 ንዑስ አንቀጽ 2(ለ-1) መሰረት ተሽሯል፡፡

2. አመልካች ከተከሰሰበት ወንጀል በነጻ የተሰናበት በመሆኑ ከእስር እንዲለቅቀው ለክፍሉ ማረሚያ ቤት ይጻፍ፡፡መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

 

 

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡