agency

 

 

ውክልና

ቅጽ 1

686

አንድ  ተወካይ  በወካዩ  ላይ  ባቀረበው      ክስ     ወካዩን  ወክሎ      መከራከር ስላለመቻሉ

የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2188,  2189,  22ዐ8,  22ዐ9, የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 57,58

14974

ወ/ት ማህሌት ገ/ስላሴ

እና

እነ አቶ መንግስቱ (ሁለት ሰዎች)

ሐምሌ 28/1997

43

ቅጽ 5

687

ንብረትን ለመሸጥ ለመለወጥ ብሎም ለሦስተኛ ወገን ለማስተላለፍ በሚል የተሰጠ ውክልና ንብረቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችል ስልጣን እና ችሎታን የሚያጐናጽፍ ስለመሆኑ

የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3ዐ49(2),2206(1)

17320

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና

ዶ/ር ሻውል ገብሬ (ሁለት ሰዎች)

መጋቢት 18/2000

2

688

ወኪል የሆነ ሰው ውክልናውን በሚገባ እስካሳየ ድረስ በማመልከቻው ላይ የራሱን ወይም የወካዩን ስም አስቀድሞ መፃፉ ወኪልነቱን ለውጦ ባለቤት የሚያደርገው ስላለመሆኑ

የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 58

23861

ሊቀ ስዩማን አሰፋ ባሻህውረድ

እና የሣህሊተ

ምህረትና ክርስቶስ ሣምራ ደብር አስተዳደር

ጥቅምት 14/2000

17


 

689

· እንደራሴ የሆነ ሰው የውክልና ስልጣኑን መሠረት  በማድረግ ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ተቃዋሚ ጥቅሞች (Conflict of interest) ማስወገድ ያለበት ስለመሆኑ

· ከእንደራሴው ጋር ውል የፈፀመው ሦስተኛ ወገን እንደራሴው የውክልና ስልጣኑን በሚያከናውንበት ጊዜ ተቃዋሚ ጥቅሞችን የማስወገድ ግዴታውን አለመወጣቱን ማወቁ  ወይም ማወቅ የሚገባው መሆኑ ያደረጉትን ውል ፈራሽ ስለማድረጉ

የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2187(1)

32241

ወ/ሮ ካሰች ተካልኝ እና

እነ አቶ ኃ/ማርያም አበበ

(ሁለት ሰዎች)

መጋቢት 9/2000

29

ቅጽ 9

690

መንግስታዊ የሆነ ተቋም በሚከሰስበትም ሆነ በሚከስበት ክርክር የሚቀርብ ሰነድ የኘሮቶኮል ቁጥር እንዲሁም ስለአቤቱታው ጽሁፍ ትክክለኛነት በሚመለከተው ኃላፊና በወኪሉ መፈረም ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 8ዐ,  92,  93 እና 92(3)

43875

በወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና

አቶ ወንድሙ ኃይሌ

ሐምሌ 16/2001

131

691

በወኪል  በኩል  የሚፈፀም  የመኪና        ጭነት  ውል      በአስጫኙ        እና በመኪናው ባለቤት መካከል እንደተደረገ የሚቆጠር ስለመሆኑ

የንግድ ህግ ቁ. 566 እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2251

34621

ኒያላ ኢንሽራንስ አ/ማ እና

አቶ ሐጎስ ገ/መድህን

ሐምሌ 3ዐ/2ዐዐ1

136

ቅጽ 10

692

ወኪል የሆነ ሰው የውክልና ሥራውን በሚሰራበት ጊዜ የራሱን ወይም ከራሱ ጋር ቤተሰባዊ ወይም ሌላ ጥብቅ ግንኙነትና ትስስር ያለው ሰውና የወካዩ ጥቅም ሊጋጭ የሚችልበት አጋጣሚ እንዳይፈጠር መከላከል ያለበት ወይም በተፈጠረ ጊዜ አስቀድሞ ለወካዩ ማሳወቅ ያለበት ስለመሆኑ

የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2187(1)2198,2208,2209

50440

አቶ ሃብቱ ወልዱ እና

እነ ወ/ሮ መሰሉ ደስታ (ሁለት ሰዎች)

ግንቦት 16/2ዐዐ2

371

ቅጽ 12

693

· አንድ ሰው ለሌላ ሰው በሰጠው ፍፁም የውክልና ስልጣን መሰረት የተከናወነውን ተግባር ለማፍረስና መከራከሪያው ሊያደርገው የሚችለው ወካዩ ራሱ ስለመሆኑ

· የወካይ ወራሾች ወኪሉ የውክልና ስልጣን ወሰኑን ሳያልፍ የስራውን ተግባር የሚቃወሙበት ህጋዊ መሰረት ስላለመኖሩ

የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2189/1/ እና /2/

38721

ካፕቴን ዮናስ ሕሉፍ እና

እነ አቶ እስጢፋኖስ ኪዳኔ /አራት ሰዎች/

ህዳር 27/2003

555


 

<![if !supportMisalignedColumns]><![endif]>

694

የውክልና ስልጣን መስጫ ሰነድ በህግ ስልጣን በተሰጠው አካል ቀርቦ ካልተረጋገጠና ካልተመዘገበ በስተቀር ህጋዊ ውጤት የማይኖረው ስለመሆኑ

አዋጅ ቁ. 334/95 አንቀጽ 5/1//ለ/

59568

አቶ ቴዎድሮስ ተስፋዬ እና

አቶ ሙሉ አርጌ

/ሁለት ሰዎች/

ሚያዝያ 05/2003

561

ቅጽ 13

695

· የውክልና ውሎች በጠባቡ ሊተረጐሙ የሚገባ ስለመሆኑ

· “በስማችን  ውል  እንዲዋዋል”  በሚል  በደፈናው  የተሰጠ ውክልና ሊተረጐም የሚችልበት አግባብ

የፍ/ብ/ህ/ቁ.2181(3), 2205, 2204

50985

እነ አቶ ስሻህ ክፍሌ (ሁለት ሰዎች)

እና ወ/ሮ አፀደ ዱቤ (ሁለት ሰዎች)

ህዳር 05/2004

544

696

· ልዩ የውክልና ስልጣን ለመስጠት በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ልዩ ውክልና ስለመስጠት በተመለከተ አግባብነት ያላቸው የህግ ድንጋጌዎች ያለመጠቀስ ልዩ የውክልና ስልጣን እንዳልተሰጠ የሚያስቆጥር ስላለመሆኑ

· የአስተዳደር አካል የሆነ ተቋም በአንድ ወቅት የሰጠውን የፅሁፍ ማስረጃ በሌላ ጊዜ ማስተካከሉ በአንድ ጉዳይ ላይ ሁለት የተለያዩ ሰነድ ቀርቧል በሚል እንደማስረጃ ሰነድ ዋጋ የሚያጣበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣

· በውክልና ሰነድ ላይ ለተወካይ የተሰጠው ስልጣን በይዘቱ ልዩ ውክልና የሚያመለክት ሆኖ ሰነዱ ስለ ልዩ ውልክና አስፈላጊነት የተቀመጠውን የፍ/ብ/ህ/ቁ 2208 ያለመጥቀሱ ብቻ ለተወካዩ ልዩ የውክልና ስልጣን እንዳልተሰጠ የሚያስቆጥር ስላለመሆኑ፣

· ከሰነድ ማስረጃ ተቀባይነት ጋር በተያያዘ የሚነሣ ጥያቄ የህግ ጥያቄ በመሆኑ በሰበር ችሎት ሊስተናገድ የሚችል ስለመሆኑ

የፍ/ብ/ህ/ቁ 2205, 2005(1), 2179, 2199, 2203, 2204

72337

ወ/ሮ ንግስቲ እምነት

እና ቴዎድሮስ ተክሌ

የካቲት 26/2004

549

697

አንድን ተቋም ወክሎ ውል ለመዋዋል በህግ ስልጣን የተሰጠው ሥራ አስኪያጅ ስልጣኑን ለሌላ ሰው በህግ ተቀባይነት ባለው  ሁኔታ አስተላልፎ ውል የተደረገ እንደሆነ ተቋሙ በሥራ አስኪያጁ በራሱ

68498

አቶ ገብረ ክርስቶስ ገብረ እግዛብሔር

እና

ሰኔ 07/2004

553

               


 

 

በመፈረም ውል አላደረገም በሚል ምክንያት ብቻ በውሉ አንገደድም ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣

በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1731 2274 2214(1 2215(3),2180)

 

ሳባ እምነበረድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

 

 

798

የፀና የውክልና ስልጣን ከሌለው ሰው ጋር የተደረገ ውል ከጅምሩ ፈራሽና ህጋዊ ውጤት የሌለው ስለመሆኑ ፣

የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2232(2),2015(ሀ),2005(2),1204

73291

እነ አቶ አፅብሃ ወልዳይ (ሁለት ሰዎች)

እና

ወ/ሮ ዙሪያሽ አሰግድ የክልሉ ፍትህ ቢሮ

ሐምሌ 04/2004

559

799

· የውክልና ውል ሳይኖር ወኪል ነኝ በሚል የሚደረግ ውል ህጋዊ ውጤት አግኝቶ የሚፀናበት አግባብ ስላለመኖሩ፣

· የውክልና ሥልጣኑ ከመሰጠቱ በፊት የተደረገ ውል ውክልና ከተሰጠ በኋላ ሊፀና ይችላል ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ  የሌለ ስለመሆኑና ወካይ የሆነ ሰው የወካዩን ድርጊት እንደተቀበለ ሊቆጠር የሚችለው በህግ የሚፀና የውክልና ውል ኖሮ ነገር ግን  ወኪሉ ከተሰጠው ስልጣን በላይ ሰርቶ የተገኘ እንደሆነ  ወይም የውክልና ስልጣኑ ካበቃ (ከተቋረጠ) በኋላ ወካዩን በመወከል የሰራቸውን ሥራዎች በተመለከተ ብቻ ስለመሆኑ፣

የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2190, 1678 (ሐ),1719(2),1723

74538

ወ/ሪት አሊያት ይማም ሙዘይን

እና

አቶ እምነቴ እንደሻው

ሐምሌ 20/2004

563

700

ወካይ የሆነ ወገን በተወካይ አማካኝነት የተደረገን ህገ ወጥ ውል እንዲፈርስ በሚል የሚያቀርበው አቤቱታ በአሥር አመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ

በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2187(1)(2),2198,1810,1808(1),1845

67376

እነ ወ/ሮ ንግስት ኪዳኔ (ሁለትሰዎች)

እና

እነ አቶ በለጠ ወልደሰማያት(ሁለት ሰዎች)

ሐምሌ 30/2004

567