Draft Custom Amendment Proclamation

Amharic

English

በጉምሩክ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ከ-ease of doing business አኳያ

የተደረጉ ለውጦችን የሚያሳይ ማብራሪያ

  • ነባሩ አዋጅ ዕቃ ከተለቀቀ በኋላ ዲክላራሲዮን እንዲሻሻል አይፈቅድም ነበር፡፡  በማሻሻያው አሳማኝ በሆነ ምክንያት ዲክላራሲዮን እንዲሻሻል ሊፈቀድ ይችላል፡፡  ይህ ዕቃ ከተለቀቀ በኋላ የሚቀርቡ የዲክላራሲዮን  ማሻሻያ ጥያቄዎች ለማስተናገድ ዕድል ይሰጣል፡፡
  • በነባሩ አዋጅ ቀረጥና ታክስ ከተከፈለ በኋላ ዲክላራሲዮን እንዲሰረዝ ህጉ አይፈቅድም ነበር፡፡  በማሻሻያው ኮሚሽኑ አሳማኝ ምክንያት ሲኖረው ቀረጥና ታክስ ከተከፈለ በኋላም ቢሆን ዲክላራሲዩን እንዲሰረዝ ሊፈቅድ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡  ይህ በተለይ የቀረጥ ነፃ መብት እያላቸው ቀረጥና ታክስ በስህተት የከፈሉ ሰዎችን ወይም ዕቃው በተሳሳተ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት /customs procedure code/ የተስተናገደ በሚሆንበት ጊዜ  ለማስተካከል ዕድል ይሰጣል፡፡
  • የ cargo trucking ኘሮጀክት አጓጓዦች በተሽከርካሪዎቹ ላይ ሊገጠም የሚገባውን የማጓጓዢያ እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ መሣሪያ ለመግጠም ፍላጎት ስለሌላቸው /እስከ 2ዐ,ዐዐዐ ብር ስለሚያስወጣቸው/ ኘሮጀክቱ የታለመለትን ዓላማ ሳያሳካ ቆይቷል፡፡  በነበሩ አዋጅ የማጓጓዢያ ባለንብረቶች መሣሪያውን በማጓጓዢያዎቻቸው ላይ እንዲገጥሙ የሚያስገድድ ስላልነበረ ማሻሻያው የማጓጓዢያ ባለንብረቶች መሣሪያውን ገዝተው በማጓጓዣው ላይ እንዲገጥሙ የሚያስገድድ ሆኖ ተቀምጧል፡፡  ከዚህም በተጨማሪ መሣሪያውን ያልገጠመ የመጓጓዣ ባለንብረት የወጭና ገቢ ዕቃ ትራንስፖርት አገልግሉት መስጠት እንደማይችል በግልጽ ተደንግጓል፡፡
  • አስመጪው ወይም ላኪው ዕቃ ወደ አገር ውስጥ ሲያስገባና ከአገር ሲያስወጣ የጉምሩክ ትራንዚት የሚፈፀመው ወደ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ግቢ በመምጣት ነበር፡፡  በማሻሻያው እንደአስፈላጊነቱ የላኪዉ ወይም የአስመጪው ዕቃ ወደ ጉምሩክ ግቢ መግባት ሳያስፈልገው በቀጥታ ወደ አስመጪው የሥራ ቦታ ወይም መጋዘን እንዲያመራና የጉምሩክ ትራንዚት አገልግሎትም እዚያው በራሱ መጋዘን ወይም ግቢ ውስጥ እንዲፈፀምለት የሚያስችል ማሻሻያ ተደርጓል፡፡  ላኪዎችም በተመሣሣይ መልኩ ከራሳቸው መጋዘን ወይም የሥራ ቦታ የጉምሩክ ትራንዚት ፈጽመው በቀጥታ ዕቃቸውን ወደ ውጭ መላክ እንዲችሉ በማሻሻያው ሁኔታዎች ተመቻችተዋል፡፡
  • ቀረጥና ታክስ ሳይከፈል  ዋስትና በመቀበል ዕቃ የሚለቀቅበት ሁኔታ በገንዘብ ሚኒስቴር ሴርኩላር ባልተብራራ ሁኔታ ሲሠራበት የቆየ  ሲሆን አሁን የቀረጥና ታክስ መክፈያ ጊዜ ለአስመጪዎች በመመሪያ ከዝርዝር አፈፃፀም ጋር በመደንገግ  የdiffered payment  አሠራር ተመቻችቷል፡፡
  • ተመልሶ ከአገር እንዲወጣ የሚደረግ ዕቃ ሲኖር በምትኩ ሌላ ዕቃ ወደ አገር ውስጥ ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት ሊገባ የሚችለው ዕቃው ምንም ይሁን ምን ወደ ውጭ ተመልሶ መላኩ ሲረጋገጥ ወይም ለጉምርክ ዋስትና ሲያቀርብ ወይም ዕቃውን ለጉምርክ ሲያስረክብ ብቻ ነበር፡፡  ይህ አሠራር ለተበላሹና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማይሰጡ ዕቃዎች ጭምር ተፈፃሚ ይሆን ስለነበረ  በአፈፃፀም በተገልጋዮች ላይ ከፍተኛ ችግር ይፈጥር ነበር፡፡  በማሻሻያው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የማይሰጡና መወገድ ያለባቸው ዕቃዎች ወደ ውጭ ተመልሰው መውጣት ሳያስፈልጋቸው ወይም ዋስትና ማስያዝ ሳያስፈልጋቸው የዕቃው ባለቤት ራሱ  ማስወገድ እነዲችል እና ይህንኑ አረጋግጦ በምትኩ ቀረጥና ታክስ ሳይከፍል ዕቃ እንዲያስገባ ተፈቅዶለታል፡፡
  •  መንገደኞች በካርጎ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡት ዕቃ በመንገደኞች የጉምሩክ  ማስተናገጃ ሥርዓት ወይም በሌላ መልኩ እንደሚስተናገድ በህጉ በግልጽ ስላልተቀመጠ መንገደኞች የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ጓዛቸውን  ለመረከብ  ይቸገሩ ነበር፡፡  በማሻሻያው በካርጎ የመጣ የመንግደኛ ዕቃ መደበኛ የካርጎ ዕቃዎች በሚስተናገዱበት ሥርዓት እየተስተናገዱ እንዲለቀቁ ሁኔታዎች  ተመቻችተዋል፡፡  ይህ ችግር በተለይ የሳውዲ መንግስት በቅርቡ በወጣው ህግ መሠረት በሳውዲ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በብዛት እንዲመለሱ ሲደረግ ጓዛቸው በካርጎ የተላከበት ሁኔታ ስለነበረ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ለማከናወን  ጉምሩክ ስለተቸገረ መንግኞች ለወሰነ ጊዜም ቢሆን ተጉላልተዋል፡፡ 
  • የውጭ አገር ማጓጓዣ ወደ ኢትዮጵያ መግባት የሚችለው ዋስትና በማስያዝ ብቻ እንደሆነ   ነባሩ አዋጅ ስለሚደነግግ ይህ ቅድመ ሁኔታ በ reciprocity መርህ መሠረት በእኛ ላይ ጎረቤት አገሮቻችን ተግባራዊ ቢያደርጉት የበለጠ የምትጎዳው ኢትዮጵያ ስለሆነች ህጉን እስካሁን ተግባራዊ አላደረግንም፡፡  በዚሁ መሠረት የውጭ አገር የንግድ ማጓጓዣዎች  ወደ አገር ውስጥ የሚገቡት ትራንስፖርት ሚኒስቴር ከአገሪቱ ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሠረት እንደሆነ በመደንገግ የዋስትናውን አስፈላጊነት እንዲቀር አድርገናል፡፡
  • ዕቃዎች በጉምሩክ ጊዜያዊ ዕቃ ማከማቻ መጋዘን የሚቆዩበት ጊዜ ለንግድ ዕቃ ከአንድ ወር እስከ ሁለት ወር ይቆይ የነበረው  ወደ 15 ቀን ዝቅ የተደረገ ሲሆን በቦንድድ መጋዘን የገባ የንግድ ዕቃ የሚቆይበት የአራት ወር ጊዜ ቆይታ በዚያው እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡  ለምርት ግብዓት ወደ አገር ውስጥ የገቡ ዕቃዎች በቦንድድ መጋዘን የገቡ ከሆነም ቀደም ሲል ይፈቀድ የነበረው የ12 ወር ጊዜ ቆይታ በዚያው እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡
  • በዋስትና ሊለቀቁ የማይችሉ ዕቃዎች  በፍ/ቤት ወይም በአስተዳደር በክርክር ላይ ቆይተው ለባለንብረቱ እንዲመለሱ ሲፈረድ በክርክሩ ወቅት በመጋዘን ለቆዩበ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ እንዳይከፈል ህጉ ይደነግግ ስለበረ የመጋዘን ባለንብረቶች በተለይ ባትሎአድ በዚህ ጉዳይ ከፍተኛ ቅሬታ ያደረበት መሆኑን ስለገለጸ እና ከጉምሩክ ጋር ከፍተኛ አለመግባባት ስለተፈጠረ በክርክር ላይ የቆዩ ዕቃዎች ኪራይ እንዲከፈልባቸው ነገር ግን ወጪውን መንግስት እንዲሸፈን ማሻሻያ ተደርጓል፡፡
  • በጊዜያዊነት አገር ውስጥ የገቡ ዕቃዎች ሁሉም ዋስትና እንደሚጠየቅባቸው ነባሩ ህግ ያስገድዳል፡፡  ሆኖም ቱሪስቶች ዋስትና ማስያዝ ስለማይችሉ በአፈፃፀም የተከስተውን ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት የአገሪቱ የቱሪስት ኢንዱስትሪም እንዳይጎዳ በማሰብ ቱሪስቶች  ተሽከርካሪን ጨምሮ በጊዚያዊነት ለሚያስገቡትን ዕቃ በዋስትና እያሲያዙ እንዲያስገቡ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡
  • በዉጭ አገር ኘሮጀክት ያላቸው የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ወይም ለጉብኝት ወደ ጎረቤት አገር ወጣ ብለው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን ወይም የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ተሽከርካሪን ጨምሮ በጊዜያዊነት ዕቃ ይዘው እንዲወጡ ነባሩ ህግ አይፈቅድም ነበር፡፡ ይህ በተለይ በውጭ አገር  የኘሮጀክት ጨረታ በሚያሸነፉ ባለሀብቶች ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥሮ ነበር፡፡  በማሻሻያው  በውጭ አገር ኘሮጀክት ያላቸው የኢትዮጵያ ነዋሪዎች እና ለጉብኝት የሚሄዱት ጭምር ተሽከርካሪን ጨምሮ ዕቃ  በጊዜያዊነት ይዘው መውጣት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡
  • የቱሪስት ዕቃዎችን ጨምሮ በጊዜያዊነት ወደ አገር ውስጥ የገቡ ዕቃዎች ወደ ውጭ ተመልሰው መውጣት የማያስፈልጋቸው ወይም የማይችሉ ሆነው በሚገኙበት ጊዜ ዕቃዎቹ ቀረጥና ታክስ ተከፍሎባቸው አገር ውስጥ ሊቀሩ የሚችሉበት አሠራር በነባሩ አዋጅ ግልጽነት የጎደለው ስለበር ይህ አሠራር በማሻሻያው ግልጽ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
  • ወደ አገር ውስጥ የገባ ዕቃ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ከመጠናቀቁ በፊት ተመልሶ እንዲወጣ ጥያቄ በሚቀርብበት ጊዜ በዕቃው ላይ 5% ቀረጥና ታክስ /በአገልግሎት ክፍያ መልክ/ በማስከፈል ዕቃው ተመልሶ እንዲወጣ ነባሩ አዋጅ  ይፈቅድ ነበር፡፡  ነገር ግን የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት አጠናቅቀው ግን ከጉምሩክ ባልወጡ ዕቃዎች ላይ የሚቀርበውን ተመሣሣይ ጥያቄ ለማስተናገድ ስላልተቻለ በማሻሻያው የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ከመጠናቀቁ ወይም ዕቃው ከመለቀቁ በፊት የሚል ማሻሻያ በማድረግ  ዕቃ መልሰው ለሚልኩ ተገልጋዮች ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡
  • ነባሩ አዋጅ ጉምሩክ የዕቃዎችን የታሪፍ አመዳደብ በሚመለከት አስገዳጅ መረጃዎችን እንደሚሰጥ ሲደነግግ አስገዳጅ የስሪት አገር መግለጫ መስጠት እንደሚችል ባለመደንገጉ ይህ አስገዳጅ መግለጫ /አስገዳጅነቱ በጉምሩክ ላይ ነው/ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ለሚያቀርቡ ተገልጋዮች በወቅቱ ምላሽ እየሰጠን አልነበረም፡፡   በማሻሻያው ጉምሩክ  የዕቃዎችን የስሪት አገር በሚመለከትም አስገዳጅ መረጃ ለተገልጋዮች  መስጠት እንዲችል ተደርጓል፡፡
  • ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ ዕቃዎች በቀላሉ በማይፋቅ ሊነሳና ሊለወጥ በማይችል ማሸጊያ የታሸጉ መሆን እንዳለባቸው ነባሩ ህግ ይደነግጋል፡፡  ከዚህ ጋር አያይዞ ነባሩ ህግ ይህን ሁኔታ የማያማሉ ዕቃዎች ወደ መጡበት ይመለሳሉ  ስለሚልና አብዛኛው ኢምፖርት ይህን ቅደመ ሁኔታ ስለማያሟላ ህጉን ተግባራዊ ለማድረግ ተቸግረን ቆይተናል፡፡ በዚሁ መሠረት  ይህን ችግር ለመቅረፍ ከላይ የተገለፀውን ሁኔታ /origin marking/ የማያሟሉ ዕቃዎች ወደ መጡበት መመለሳቸው ቀርቶ በቅጣት እንዲስተናገዱ ተደርጓል፣
  • ነባሩ አዋጅ በብልጫ የተከፈለ ቀረጥና ታክስ ተመላሽ የሚደረገው  የተመላሽ ጥያቄው ዕቃው ወደ አገር ውስጥ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ባለው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከቀረበ ብቻ ነው የሚል በመሆኑና ዕቃ ወደ አገር ውስጥ ገባ የሚባለው መቼ ነው? የሚለው እጅግ አካራካሪ ሆኖ በመገኘቱና  በተመላሽ ጠያቄዎች ላይ  መጉላላትን በማስከተሉ የአንድ ዓመት ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው ገቢ ዕቃዎች  ለነፃ ዝውውር ከተለቀቁ በኋላ ሰነድ ከተበተነበት ቀን ጀምሮ ነው የሚል ማሻሻያ  በማድረግ  ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል ሁኔታ ተመቻችቷል፡፡
  • ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ገደብ የተደረገበት ዕቃ ከተቆጣጣሪ መ/ቤቶች ፈቃድ ያልተሰጠው በሆነ ጊዜ  ተመልሶ እንዲወጣ ነባሩ ህግ ይደነግጋል፡፡  በዚህ ጊዜ አስቀድሞ የተከፈለ ቀረጥና ታክስ ተመላሽ እንደሚደረግ ህጉ ሳይገልጽ በዝምታ ያለፈው በመሆኑ በዚህ ዓይነት ዕቃ ላይ ቀረጥና ታክስ የከፈሉ አስመጪዎች ዕቃውን ወደ ውጭ መልሰው ሲልኩ ለሚያቀርቡት የተመላሽ ጥያቄ  አጥጋቢ ምላሽ እየሰጠን አልነበረም፡፡  በማሻሻያው ወደ አገር እንዳይገባ ገደብ በተደረገበት ዕቃ ላይ የተከፈለበት ቀረጥና ታክስ  ዕቃው ተመልሶ ከአገር እንዲወጣ ሲደረግ  ተመላሽ እንደሚሆን ተደንግጓል ፡፡  ይህም በተገልጋዩች ላይ ይከሰት የበረውን መጉላላት ያስቀራል፣ ፍትሐዊነትንም ያረጋግጣል፡፡
  • በተለየዩ ህጎች  የተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች የቀረጥ ነፃ መብት እንዲፈቅዱ የተደረገበት ሁኔታ ስለነበረ የቀረጥ ነፃ መብቱ ለታለመለት ዓላማ ማዋሉን ለመቆጣጠር እና  ለማረጋገጥ አዳጋች በመሆኑ በቀረጥ ነፃ መብቶችን አላግባብ በመጠቀም ባለመብቶቹ በመንግሥት ላይ ያደርሱት ከነበረው ከፍተኛ ኪሳራ በተጨማሪ የቀረጥ ነፃ መብት ለማግኘት ባለሃብቶች ወይም ግለቦች በየመ/ቤቱ በመንከራተት ያባክኑት የበረውን ጊዜ በመቆጠብ መብቱን ከአንድ መ/ቤት ብቻ ማግኘት እንዲችሉ ማሻሻያዎች ተደርገዋል፡፡  በዚሁ መሠረት በማሻሻያው የቀረጥ ነፃ መብት እንዲፈቅዱ ለሌሎች የመ/ቤቶች የተሰጠው ስልጣን ለንዘብ ሚኒስቴር የተላለፈ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ ይህም የመንግስትን ኪሣራና የባለመብቶችን ውጣ ውረድ ያስቀራል ፡፡
  • ሌሎቹ በርካታ ማሻሻያዎች ከህግ ማስከበር እና ከቁጥጥር ጋር የተያያዙ ስለሆነ ከ ease of doing business ጋር እምብዛም ግንኙነት ባይኖራቸውም የሚተሉትን ማሻሻያዎች ተደርገዋል፡-
  • ለኢንቨስትመንት በቀረጥ ነፃ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች ከተፈቀደላቸው ዓላማ ውጭ እየዋሉ /እየተሸጡ/ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሣራ እያደረሱ ስለሆነ የዕቃዎቹ መወረስ እንደተጠበቀሆኖ ይህ ተግባር በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑ በማሻሻያው ተደንግጓል፡፡
  • በነባሩ አዋጅ እና በማሻሻያው ግዴታ ለሚጥሉ ድንጋጌዎች በሙሉ ውጤታቸው አስተዳደራዊ መቀጫ እንደሚያስከትል እየተገለፀ መቀጫዎቹ በማሻሻያው እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡
  • ለዚህ አዋጅ መሻሻል ዋነኛ ምክንያት የሆነው ኮንትሮባንድ ዕቃ ጭኖ የተገኘ ማጓጓዥያ ስለሚወረስበት ሁኔታ የሚደነግገው ክፍል በረካታ ጥያቄ በማስነሳቱ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ አቅጣጫ መሰጠቱ ነው፡፡ በዚህ መሠረት የኮንትሮባንድ ዕቃ ጭኖ የተገኘ ማጓጓዥያ በዕቃው ዋጋ ልክ ወይም አንድ መቶ ሺህ ብር ከሁለቱ አነስተኛውን መቀጫ እንደሚቀጣ በማሻሻያው ተደንግጓል፡፡ ማሻሻያው በግመል የሚጓጓዘውን የኮንትሮባንድ ዕቃም ታሳቢ ያደርጋል፡፡
  • በነባሩ አዋጅ በገቢ ዕቃ ላይ የሚገኘው ልዩነት ከ10% የማይበልጥ ከሆነ አስመጪው በልዩነቱ ላይ ቀረጥና ታክሱን ያለቅጣት ከፍሎ እንዲስተናገድ ይደነግግ ነበር፡፡ ሆኖም አስመጪዎች ይህን አጋጣሚ ያላግባብ በመጠቀም ሆን ብለው ዕቃ ባስመጡ ቁጥር በሚያስመጡት ዕቃ ላይ ዲክሌር ያልተደረገ 10% ዕቃ እየጨመሩ በማስመጣት ከፍራንኮ ቫሎታ ጋር በተያያዘ ችግር ያስከተሉ በመሆኑ ይህ ልዩነት ወደ 5% ዝቅ እንዲልና አስመጪው በልዩነቱ ላይ ያለቅጣት ቀረጥና ታክስ ብቻ የሚከፍለው ድርጊቱ በዓመቱ ውስጥ ለአንድ ጊዜ ብቻ የተፈፀመ እንደሆነ መሆኑ በማሻሻያው ተካቷል፡፡