73514 criminal law/ criminal procedure/ constitution/preliminary objection

ተከሳሽ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በተመለከተ በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት ሊያቀርባቸው ስለሚችላቸው መከራከሪያዎች  ተከሳሽ በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት የሚያቀርባቸው መቃወሚያዎች በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130 ላይ የተመለከተቱት ጉዳዬች ጋር ብቻ በተገናኘ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  ማንኛውም ሰው የወንጀል ክስ ሲቀርብበት የተከሰሰበት የወንጀል ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈፀሙ ወይም አለመፈፀሙ ወንጀል መሆኑ ካልተደነገገ በስተቀር ሊቀጣ የማይችልና ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ተፈፃሚ በነበረው ህግ ከተመለከተው የቅጣት ጣሪያ በላይ ሊቀጣ የማይችል ስለመሆኑ፣  የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራ ስለመሆኑና ዳኞች ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ክስ የቀረበበት ድርጊት ወንጀል ስለመሆኑ የሚደነግገው ህግ ፀንቶ በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት መሆኑን ከተረዱ በማናቸውም ጊዜ አንስተው ውሣኔ ለመስጠት የሚችሉ ስለመሆኑ፣  ፍ/ቤቶች በዐ/ህግ የቀረበ የወንጀል ክስ በህገ-መንግስቱና በወንጀል ህጉ የሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር የተቀመጡ መርሆዎችና ድንጋጌዎችን የሚያሟሉ መሆን አለመሆኑን በመመርመር የመወሰን ግዴታ ያለባቸው ስለመሆኑ፣ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 5(2) ,13(1), 22(1 ) የወ/ህ/አ. (414/96)3,402,419,5(2) የወ/ህ/ቁ.(214/74) አለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ስምምነት (ICCPR) አንቀጽ 15(1) የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130(2)(1)

Download Cassation Decision