የመጥፋት ውሣኔ የተሰጠበት ሰው ቀደም ሲል ጋብቻ የነበረው እንደሆነ የጠፋው ሰው መመለስ በመጥፋት ውሣኔው የፈረሰውን ጋብቻ እንደገና ተመልሶ ህይወት እንዲዘራ (እንዲፀና) የማድረግ ውጤት አለው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ በፍ/ቤት የተሰጠ የመጥፋት ውሣኔ መሻር በመጥፋት ውሣኔው መሠረት የፈረሰን ጋብቻ ከፈረሰበት ቀን ጀምሮ (ግለሰቡ ከተመለሰበት ቀን ጀምሮ) መልሶ እንዲቋቋም (እንዲፀና) ለማድረግ የሚያስችል ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.170,171