78398 contract law/ written contract/ form/ sale of immovable property/ notorized contract/ parole evidence rule

በተዋዋይ ወገኖች በተደረገ የጽሁፍ ሰነድ ላይ የሚገኝ የስምምነት ቃል እንዲሁም በሰነድ ላይ ስለተመለከተው (ስለተፃፈው) ቀን በተፈራራሚዎቹ መካከል ውሉ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ነው በሚል ለመደምደም የሚቻለው እንደ ውለታው አይነት የጽሁፉ ውል አደራረግን በተመለከተ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ በተሟላ ሁኔታ የተዘጋጀና የያዘ እንደሆነ ስለመሆኑ፣  የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ጋር በተገናኘ ውሉ በውል አዋዋይ ፊት በህጉ አግባብ ባልተደረገበት ሁኔታ በውሉ ላይ የሠፈሩት ማናቸውም የውል ቃሎች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዳሉ የሚታመኑና በማናቸውም የሰው ምስክርነት ቃል ማስተካከል አይቻልም ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  አንድ ውል በህግ ፊት የፀና ነው እንዲባል በህግ ውሉ የሚደረግበትን አግባብ በተመለከተ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን በተመለከተ የተደረገ ካልሆነ በቀር ውሉን መሠረት በማድረግ እንደውሉ ይፈፀምልኝ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ2005(1),1678(ሐ),1719(2,1723)

Download Cassation Decision