78856 Criminal law/ sentencing/ pension/ effect of sentencing on pension

ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተገናኘ በወንጀል ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ የተጣለበትን ቅጣት ፈጽሞ ያጠናቀቀ ሰው በፍርድ ቤት መሰየም በግለሠቡ የጡረታ መብት ላይ ስለሚኖረው ውጤት  በመሰየም ሊገኝ የሚችለው መብት ግለሰቡ ከመሰየሙ አስቀድሞ በቅጣት ቀሪ ሆኖበት የነበረውን መብት ሳይሆን ግለሰቡ ከተሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ፊት ሊጠበቅለት የሚገባውን መብት በተመለከተ ብቻ ስለመሆኑ፣  የመንግስት ሰራተኛ የነበረና የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነ ሠው በወንጀል ጉዳይ ተከስሶና ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ በፍ/ቤት ቢያንስ የ3 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት የተወሰነበት በመሆኑ የጡረታ መብቱን እንዲያጣ የተደረገ ሠው ከቅጣቱ በኋላ በፍ/ቤት መሰየሙ አስቀድሞ በቅጣት ቀሪ ሆኖበት የነበረውን የጡረታ መብቱን መልሶ ለማግኘት የማያስችል ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 231,235(1),232 አዋጅ ቁ. 209/55 አዋጅ ቁ. 5/67 አዋጅ ቁ.345/95 አንቀጽ 52/1/

Download Cassation Decision