81081 property law/ unlawful enrichment/ undue expenses/ good faith

አንድ ሰው የሌላ ሰው ንብረት ይዞ ሲጠቀም ከቆየና ንብረቱን በሚጠቀምበት ጊዜ ንብረቱን ከጥፋት ወይም ከብልሽት ለማዳን ሲል ተገቢውን ወጪ ያወጣ እንደሆነ ይኸው ወጪ በህጋዊ ባለሀብቱ እንዲተካለት ለመጠየቅ የሚችለው ወጪው የግድ አስፈላጊ ከሆነና በቅን ልቦና የተደረገ መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለመሆኑ፣  ወጪው በክፉ ልቦና የተደረገ ስለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ግን እቃውን (ንብረቱን) እንዲመልሰ የተደረገው ሰው እንዲተካለት የጠየቀውን ወጪ መጠን ዳኞች ሊቀንሱት ወይም ጭራሹንም ሊያስቀሩት የሚችሉ ስለመሆኑ፣  በንብረቱ (እቃው) ላይ የተደረገው ወጪ «በክፉ ልቦና የተደረገ ነው» የሚባለው ወጪው በተደረገበት ጊዜ (ወቅት) ወጪው እንዲተካለት የሚጠይቀው ሰው ንብረቱን (እቃውን) ለባለቤቱ ለመመለስ ግዴታ ያለበት መሆኑን ያወቅ እንደነበር ወይም ማወቅ ይገባው የነበረና ርትዕም ሲያስገድድ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2172(1),2171(1),2168,2169

Download Cassation Decision