የመኪና ሽያጭ ውል መደረጉን (መኖሩን) ለማስረዳት ሊቀርብ ስለሚገባው የማስረጃ አይነት፣ የመኪና /ተሽከርካሪ/ ባለሀብትነት (ስመ ሀብት) እንዲተላለፍለት የሚጠይቅ ሰው ሊያቀርባቸው ስለሚገቡና ተቀባይነት ስላላቸው ማስረጃዎች አንድ ግዴታ እንዲፈፀምለት የሚጠይቅ ሰው የግዴታውን መኖር የማስረዳት ሸክም ያለበት ስለመሆኑ፣ አከራካሪ ሆኖ የቀረበን አንድ ፍሬ ነገር ማስረዳት ስለሚቻልበት የማስረጃ አይነት አግባብነት ባለው ህግ በተለይ የተቀመጠ ግለጽ ድንጋጌ እስከሌለ ድረስ ማናቸውንም ዓይነት ማስረጃ አቅርቦ ጉዳዩን ለማስረዳት ስለመቻሉ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1186(1),(2),2001(1) ስለ ተሽከርካሪ መለያ መመርመሪያና መመዝገቢያ አዋጅ ቁ.681/2002 አንቀጽ 6(3)(4)