ከፍርድ አፈፃፀም ጋር በተገናኘ በአንድ በቀረበ የዋና ጉዳይ ክርክር ሒደት የእግድ ትዕዛዝ የተሰጠበት ንብረት በተመሳሳይ ተከራካሪ ወገኖች ጥያቄ በአፈፃፀም ደረጃ በተጠቃሹ ንብረት ላይ አፈፃፀም እንዲቀጥል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ ቀደም ሲል በዋና ጉዳይ ክርክር በፍ/ቤት ትእዛዝ እንዲታገድ የተደረገ መሆኑ የታወቀ ንብረት ላይ በድጋሚ በተመሳሳይ ንብረት ላይ መብትን ለማስከበር በሚል በሌላ ጊዜ በአፈፃፀም ደረጃ የሚቀርብ ጥያቄ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፣