ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በተገናኘ ከሚመለከተው የገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ፈቃድ ሳያገኝ ተገቢ ያልሆኑ ፓዶችን (የVAT ደረሰኞችን) ማሳተምና መገልገል በወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑና የድርጅቱ ባለሀብት (ሥራ አስኪያጅ) ድርጊቱ ሲፈፀም በቦታው ያልነበረ መሆኑን በመግለጽ የሚያቀርበው መከራከሪያ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው ማንኛውም በጐ አሳቢ ሰው ሊያደርገው የሚችለውን ጥንቃቄ ያደረገና ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ ድርጅቱን በመምራት ኃላፊነቱን የተወጣ መሆኑን ማስረዳት የቻለ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 56(3),(ለ), 3(1)(ለ), 2(11), 3(1)(ሀ) አዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀጽ 2, 19(50) (ሐ)