88867 civil procedure/ execution of judgment/ priority of creditors

በአንድ የፍርድ ባለእዳ ንብረት ላይ ፍርድ እንዲፈፀምላቸው የሚጠይቁ የፍርድ ባለገንዘቦች ያሉ እንደሆነ አፈፃፀሙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403 መሠረት ሊስተናገድ የሚገባ እንጂ በሌላ የፍ/ባለመብት ምክንያት በሌላ የአፈፃፀም መዝገብ ላይ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቶ የአፈፃፀም ጥያቄው ካልቀረበ በስተቀር ሊቀጥል አይችልም ለማለት የማይችል ስለመሆኑ፣  አፈፃፀሙ በሚካሄድበት ወቅት በንብረቱ ላይ የመያዣ ውልን መነሻ በማድረግ የቀዳሚነት መብት አለን የሚሉ ወገኖች ያሉ እንደሆነም ጥያቄው በቀረበ ጊዜ እንደየአግባብነቱ ታይቶ ሊወሰን የሚገባው ስለመሆኑ፣  አፈፃፀሙን የያዘው ፍ/ቤት በንብረቱ ባለቤት ላይ የገንዘብ ክፍያ ፍርድ አሰጥተው እና ገንዘቡም እንዲከፈላቸው ጥያቄ ያቀረቡ የፍርድ ባለገንዘቦችን አስቀርቦ ጥያቄያቸውን በመመርመር ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ አኳያ አገናዝቦ በመመልከት አፈፃፀሙ ሊመራ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403, 378

Download Cassation Decision