family law

  • በባል ወይም በሚስት ለጋራ መተዳደሪያቸው በሚል ከሚካሄድ የንግድ ሥራ ማስኬጃ ጋር በተያያዘ የተገባ ዕዳ የተጋቢዎች የጋራ እዳ እንደሆነ የሚቆጠር ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ.19 የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92, አንቀፅ 70

    Download Cassation Decision

  • አንድን ተቋም ወክሎ ውል ለመዋዋል በህግ ስልጣን የተሰጠው ሥራ አስኪያጅ ስልጣኑን ለሌላ ሰው በህግ ተቀባይነት ባለው ሁኔታ አስተላልፎ ውል የተደረገ እንደሆነ ተቋሙ በሥራ አስኪያጁ በራሱ በመፈረም ውል አላደረገም በሚል ምክንያት ብቻ በውሉ አንገደድም ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1731 2274 2214(1 2215(3),2180)

    Download Cassation Decision

  • የጋብቻ ፍቺ ውጤት በስምምነት በሚያልቅበት ወይም በሽማግሌዎች ወይም በባለሞያዎች በሚወሰንበት ጊዜ ውሣኔው ተፈፃሚነት የሚኖረው ለፍ/ቤት ቀርቦ ተቀባይነትን ሲያገኝ ብቻ ስለመሆኑ ፍቺን እና የፍቺን ውጤት በተመለከተ ውሣኔ የመስጠትና የማፅደቅ ስልጣን የፍ/ቤት ብቻ ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 83(3), 117 የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.69/95 እና አዋጅ ቁ.83/96 አንቀፅ 110(5)

    Download Cassation Decision

  • ከባልና ሚስት የጋራ ንብረት ጋር በተገናኘ በጋብቻ ወቅት በአንደኛው ተጋቢ አማካኝነት ከባንክ ወጪ ተደርጐ ለ3ኛ ወገን የተላለፈ (የተሰጠ) ገንዘብ ለትዳር ጥቅም እንደዋለ የሚገመትበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 85-93

    Download Cassation Decision

  • የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ጋር በተገናኘ አንድን የጋራ ንብረት በዓይነት ለመካፈል ተጋቢዎቹ ከስምምነት ላይ ለመድረስ ያልቻሉ እንደሆነና ሁለቱም የቅድሚያ ግዢ መብት ጥያቄ ያቀረቡ እንደሆነ ንብረቱ ለጨረታ ቀርቦ እንዲሸጥ በማድረግ ገንዘቡን መካፈል ያለባቸው ስለመሆኑ፣ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ብ/መ/ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 75/96 አንቀጽ 103(1)

    Download Cassation Decision

  • በንብረት ላይ በፍ/ቤት የተሰጠን የእግድ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 158 መሠረት መልሶ ለማንሳት ስለሚቻልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 158

    Download Cassation Decision

  • ከባልና ሚስት ጋብቻና ፍቺ ጉዳይ ጋር በተገናኘ የቀረበን ጉዳይ ስልጣን ያለውና ተከራካሪዎቹ ለመዳኘት ፈቃዳቸውን የገለፁለት የሽሪአ ፍ/ቤት ለመዳኘት ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጽ መዝገቡን የዘጋው እንደሆነ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን ማስተናገድ የሚገባው ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. አንቀጽ 37(1), 34(5), 78(5),

    Download Cassation Decision

  • ፍቺን በስምምነት ለመፈፀም ለፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረቡ ባል እና ሚስት የፍቺ ውጤትን በተመለከተ ያደረጉትን ስምምነት ፍ/ቤት ለህግና ለሞራል የማይቃረን መሆኑን በማረጋገጥ ያፀደቀው እንደሆነ ስምምነቱ ተፈፃሚ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 80,83(3) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 277(2)

    Download Cassation Decision

  • የኮንዶሚኒየም ቤትን በጋብቻ ወቅት እያሉ የደረሳቸው ባልና ሚስት የቤቱ ቅድመ ክፍያ በጋብቻ ወቅት ከተፈራ የጋራ ሀብት የተከፈለ እንደሆነና ቤቱን ለማሳመርና ለሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከጋራ ሀብቱ ወጪ በማድረግ ጥቅም ላይ በዋለበት ሁኔታ ጋብቻው በፍቺ የፈረሰ እንደሆነ ቤቱ ለተጋቢዎቹ፣ ሊከፋፈል ስለሚችልበት አግባብ፣ እንዲሁም በፍቺ ጊዜ እኩል መብት የሚኖራቸው ስለመሆኑ፣ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 35(1)  በህገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸውን ቤተሰብ የመመስረት መብት በመጠቀም ጋብቻ የፈፀሙ ወንዶች እና ሴቶች በጋብቻው አፈፃፀም፣ በጋብቻው ዘመን

    Download Cassation Decision

  • የመጥፋት ውሣኔ የተሰጠበት ሰው ቀደም ሲል ጋብቻ የነበረው እንደሆነ የጠፋው ሰው መመለስ በመጥፋት ውሣኔው የፈረሰውን ጋብቻ እንደገና ተመልሶ ህይወት እንዲዘራ (እንዲፀና) የማድረግ ውጤት አለው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  በፍ/ቤት የተሰጠ የመጥፋት ውሣኔ መሻር በመጥፋት ውሣኔው መሠረት የፈረሰን ጋብቻ ከፈረሰበት ቀን ጀምሮ (ግለሰቡ ከተመለሰበት ቀን ጀምሮ) መልሶ እንዲቋቋም (እንዲፀና) ለማድረግ የሚያስችል ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.170,171

    Download Cassation Decision

  • በጋብቻ ወቅት በአንደኛው ተጋቢ ስም የተመዘገበና በጋብቻ ወቅት ዕጣው የወጣ የኮንዶሚንየም ቤት ላይ ያለ መብት የቤቱ ውል ከጋብቻ መፍረስ በኋላ የተፈፀመና ቅድሚያ ክፍያ የተከፈለ መሆኑ (የንብረት ክፍፍል እስካልተፈፀመ ድረስ) ንብረቱን የግል የሚያስብል ስላለመሆኑ

    Download Cassation Decision

  • በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉ ውስጥ የተመለከቱት የይርጋ ድንጋጌዎች የሚታዩበት አግባብ በፍ/ብ/ህጉ በተመለከቱት የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ድንጋጌዎች ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78 መሠረት በሌለሁበት የተሰጠ ፍርድ ይነሳልኝ በሚል ጥያቄ በቀረበ ጊዜ በህጉ የተመለከተው የአንድ ወር ግዜ ገደብ በፍታብሔር ህጉ የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ስሌት መሠረት ሊሰላ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1848, 1856(2) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78, 195

    Download Cassation Decision

  • በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 41 የተመለከተው የጣልቃ ገብነት ሥርዓት አፈፃፀም እንደተሰጠ የማይቆጠርና ህጋዊ ውጤት ሊኖረው የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 73,337

    Download Cassation Decision

  • ሚስትነትን በተመለከተ የአመልካችን ማስረጃ ብቻ በመቀበል ሚስትነትን በማረጋገጥ በፍ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (Declaratory Judgment) በማናቸውም ጊዜ ተዓማኒነትና ክብደት የሌለው ማስረጃ መሆኑን ለማሳየት ክርክር ሊቀርብበትና ተቃራኒ ማስረጃ ተሰምቶ ውድቅ ሊደረግ የሚችል እንጂ ማስረጃውን በተሰጠው ፍ/ቤት ተቃውም በማቅረብ ያልተሻረ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣

    Download Cassation Decision

  • የቤተ ዘመድ ስም እንዲለወጥ በፍ/ቤት ጥያቄ ለማቅረብ የሚቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 42 , 33(1) , (2)

    Download Cassation Decision

  • ተጋቢዎች የጋብቻቸውን ፍቺ አስመልክቶ ጉዳዩ በመደበኛው ፍ/ቤት ቀርቦና ክርክር ተካሄዶ ውሣኔ ከተሰጠበት በኋላ በሌላ ጊዜ በተመሳሳይ ጉዳይ ሀይማኖታዊ ስርዓትን በመጠቀም በሸሪአ ፍ/ቤት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5(1)(2), 244(2)(ለ), 245(2) አዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀጽ 5(4), 6(2) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 34(5)

    Download Cassation Decision

  • የአባት ስም እንዲስተካከልልኝ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ የክስ ምክንያት የለውም ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣  አንድ ሰው አንድ የቤተዘመድ ስምና አንድ ወይም ብዙ የግል ስሞችና የአባት ስም ሊኖረው ስለመቻሉና የአንድ ልጅ የአባት ስም የሚሆነው የአባቱ የግል ስም ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 231 (1)(ሀ) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 32(1)፣ 36(1)

    Download Cassation Decision

  • የቀለብ ገንዘብ መጠን ስለሚወሰንበት አግባብ፣ የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 197 አንቀጽ 2

    Download Cassation Decision

  • a-manual-on-family-law-clinic

  • When Globalization Hits Home: International Family Law Comes of Age

    Intercountry Adoption: Policies, Practices and Outcomes (Foreword)