criminal law

  • የንግድ ሥራ ፈቃድ ኖሮት ነገረ ግን በህግ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ፈቃዱ ሳይታደስ በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የተገኘ ሰው የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ እንደሌለው ተቆጥሮ በወንጀል ኃላፊነት ጥፋተኛ ተደርጐ ሊያስቀጣው የሚችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 2(10), 36, 60(1)

    Download Cassation Decision

  • ህጋዊ መከላከል (Legitimate self-defense) በወንጀል የማያስቀጣው የራስን ወይም የሌላን ሰው መብት ህገ ወጥ ከሆነ ጥቃት ወይም በቅርብ ከሚደርስ ህገ ወጥ ጥቃት ለማዳንና ጥቃቱ እንዳይደርስ ከማድረግ ሌላ አማራጭ (መንገድ) ሣይኖር ከሁኔታው መጠን ባለማለፍ የተፈፀመ ስለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 78 ,79

    Download Cassation Decision

  • ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በተገናኘ ከሚመለከተው የገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ፈቃድ ሳያገኝ ተገቢ ያልሆኑ ፓዶችን (የVAT ደረሰኞችን) ማሳተምና መገልገል በወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑና የድርጅቱ ባለሀብት (ሥራ አስኪያጅ) ድርጊቱ ሲፈፀም በቦታው ያልነበረ መሆኑን በመግለጽ የሚያቀርበው መከራከሪያ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው ማንኛውም በጐ አሳቢ ሰው ሊያደርገው የሚችለውን ጥንቃቄ ያደረገና ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ ድርጅቱን በመምራት ኃላፊነቱን የተወጣ መሆኑን ማስረዳት የቻለ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 56(3),(ለ), 3(1)(ለ), 2(11), 3(1)(ሀ) አዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀጽ 2, 19(50) (ሐ)

    Download Cassation Decision

  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ነጋዴ (ሠው) ያለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሽያጭን አከናውኗል በሚል በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን ስለሚችልበት አግባብ፣ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 11(1)(2)፣ 22(1)(3) አዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀጽ 11(1) የወንጀል ህግ አንቀጽ 23(2)፣ 58(3) ደንብ ቁጥር 139/1999

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በስራው ስልጣን መሠረት በአደራ የተሰጠውን ወይም ሊጠብቀውና ሊከላከለው የሚገባውን የህዝብ ወይም የመንግስት ጥቅም የሚጐዳ ተግባር የፈፀመ እንደሆነ በወንጀል ህግ አንቀጽ 411 መሠረት በወንጀል ሊጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 411(ሐ), 407Download Cassation Decision

  • ፍ/ቤቶች የገንዘብ መቀጫን ሲወስኑ ከግምት እና ግንዛቤ ውሰጥ ሊያስገቡዋቸው የሚገቡ የተከሳሽ ግላዊና የወንጀሉን ሁኔታዋችን በማገናዘብና ፤ በወንጅል ህጉ እና በቅጣት መመሪያው ላይ የተቀመጡ መሰፈርቶችን መሰረት በማድረግ መወሰን ያለባቸው እንጂ በደፈናው የገንዘብ መቀጮ መወሰን ተገቢ ሰላለመሆኑ ፤ የወ/ሕ/ቁ 88 /2/ እ 90 90 (2)፤ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2000

    Download Cassation Decision

  • ነፍሰጡር (እርጉዝ) የሆነች ሴትን ሆዷ ላይ በመምታት ጽንሱ እንዲሞት ማድረግ ድርጊቱን በፈፀመው ሰው ላይ በግድያ ሙከራ የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 27(1), 581(ለ), 540

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሠው ወንጀል አደረገ የሚባለው ህገ ወጥነቱ እና አስቀጪነቱ በህግ የተደነገገን ድርጊት ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ ስለመሆኑና አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለውም ወንጀሉን የሚያቋቁሙት ህጋዊ፣ ግዙፋዊና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ስለመሆኑ፣  ማንም ሰው በዋና ወንጀል አድራጊነት ወንጀል እንዳደረገ ተቆጥሮ የሚቀጣው በቀጥታ ወይም በእጅ አዙር ወንጀሉን ያደረገ በሆነ ጊዜ ወይም ወንጀሉን እርሱ በቀጥታ ባያደርገውም እንኳን በሙላ አሳቡና አድራጐቱ በወንጀሉ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆኑ ድርጊቱን የራሱ ያደረገ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 2፣23(1)፣ 32(1) የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 111፣112፣141፣142

    Download Cassation Decision

  • አንድ የትራፊክ ባለሙያ የሚሰጠው ሙያዊ አስተያየት የማስረጃ ዋጋ
    የማይሰጠው አስተያየቱ ተገቢውን የሙያ ደንብ ተከትሎ ያልተሰጠና
    ያልቀረበ፣በጊዜውና በቦታው ከነበሩት የአይን ምስክሮች ቃል ጋር
    ተነፃፅሮ ሲታይ በመሰረታዊ ነጥቦች ላይ ልዩነት ያለበት መሆኑ
    ሲረጋገጥ እንጂ በጭፍጫፊ ነጥቦች ላይ ልዩነት ተከስቷል ተብሎ
    ሊሆን እንደማይገባ፣
    የልዩ አዋቂዎች ምስክሮች ቃላቸውን ገለልተኛ ሆነው መስጠት እንደ
    አለባቸውና ቃላቸው ያለበቂ ምክንያት ልዩ አዋቂ ያልሆኑ ሰዎች
    በሚሰጡት የምስክሮች ቃል ውድቅ መሆን የሌለበት መሆኑን
    ተቀባይነት ያላቸው የማስረጃ ህግ ደንቦች የሚያስገነዝቡ ስለመሆኑ
    የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141፣142፣194
    የወንጀል ህግ ቁጥር 24፣59፣239(2)፣57፣543(2)

    ፈቃድ የሌላቸው የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶችን በቤቱ ውስጥ አከማችቶ የተገኘ ሰው መሣሪያዎቹን ለመነገድ በሚል ሀሳብ የያዘ መሆኑ የተረጋገጠ ካልሆነ በስተቀር ግለሰቡ በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን የሚገባው በወንጀል ህግ አንቀጽ 481(1)(ሀ) ሣይሆን በአንቀጽ 809(ሀ) ሥር በተመለከተው ድንጋጌ መሠረት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 481(1)(ሀ), 809(ሀ)

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል የተከሰሰ ሰው ጉዳዩን በሌለበት ለማየት ፍ/ቤቱ በመጀመሪያ
    ለተከሣሹ ህጉ ያስቀመጠውን ጥብቅ መስፈርት በተከተለ መልኩ
    በአግባቡ ጥሪ ሊያደርግለት የሚገባ ስለመሆኑ፣
    የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ቁጥር 161(1)(2) እና 162

    የሰ/መ/ቁ. 93577

     

    ህዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም.

    ...
  • አንድ ሰው በቸልተኝነት ወንጀል ፈጽሟል ሊባል የሚችለው የድርጊቱን ውጤት እያወቀ ውጤቱ አይደርስም ከሚል መነሻ ድርጊቱን የፈፀመ እንደሆነ ወይም ድርጊቱ የወንጀል ውጤት የሚያስከትል መሆኑን ባያውቅም ውጤቱን ማወቅ ነበረበት ወይም ጥረት ቢያደርግ ማወቅ ይችል ነበረ ለማለት የሚቻል እንደሆነ ስለመሆኑ፣  አንድ ሰው የፈፀመው ድርጊት በቸልተኛነት ነው ለማለት በመስፈርትነት ሊወሰድ የሚገባው የድርጊቱ ፈፃሚ በድርጊቱና በውጤቱ መካከል ያለውን ግንኙነት አስመልክቶ ያለው ወይም ሊኖረው የሚገባው ግንዛቤ ስለመሆኑና ይህም የድርጊቱ ፈፃሚ የነበረው እውቀትና ግንዛቤ ወይም ሊኖረው የሚገባውን እውቀትና ግንዛቤ መመዘን ያለበት ከግለሰቡ እድሜ፣ ያለው የኑሮ ልምድ የትምህርት ደረጃ ሥራውና የማህበራዊ ኑሮ ደረጃውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 59(1), 543(2), 57

    Download Cassation Decision

  • በወንጀል ጉዳይ ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ ተከሳሹን ጥፋተኛ ሆኖ ያስገኘው ሕግ በፍርዱ ውስጥ መገለጽ እንደሚገባውና የጥፋተኝነት ውሳኔው የሚሰጥበት ድንጋጌ መፈጸሙ ከተረጋገጠው የወንጀል ፍሬ ነገር ጋር በጥንቃቄ መነጻጸር የሚገባው ስለመሆኑ፣ ወ/መ/ሕ/ስ/ስቁ. 149

    Download Cassation Decision

  • አንድ ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠበት ውሣኔ እንዲነሳለት የሚያቀርበውን ማመልከቻ በመቀበል ከሚቻልባቸው ምክንያቶች አንዱ መጥሪያ ለተከሳሹ ያለመድረስ ጉዳይ ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሕ/ሥ/ ሥ/ቁ. 199ሀ

    Download Cassation Decision

  • አንድ በወንጀል ድርጊት ቅጣት የተጣለበትን ተከሳሽ ቅጣቱ እንዳይፈፀም ፍርድ ቤቱ ለማድረግ የሚችለው ጥፋተኛው በመልካም ጠባይ እንደሚመራ ፣ እንዲፈፅም የተሰጠውን ግዴታ እንደሚቀበል ፣ በሚቻለው መንገድ ሁሉ በጥፋቱ የደረሰውን ጉዳት እንደሚክስ ወይም ለተበዳዩ እንደሚከፍል እና ለዚሁ ጉዳይ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የፍርድ ቤቱን ወጪ እንደሚከፍል ማረጋገጫ ከሰጠ ስለመሆኑ፣ ከዚህም በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው ለገባበት ግዴታ አፈጻፀም መተማመኛ ዋስትና የሚጠይቅ ስለመሆኑ፣ አንቀጽ 197/1/ እና/2/

    Download Cassation Decision

  • በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ በሠራተኛ ዕድገት ዝውውርና ሥልጠና በሚመለከት አሠሪው የሚወስዳቸው እርምጃዎች በፍርድ ሊታዩና ሊያልቁ የሚችሉ ጉዳዮች እንደሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገመንግስት አንቀፅ 37፣ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 138፣142 ንዑስ አንቀጽ 1/ሰ/ እና ከአንቀጽ 147 ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ/

    Download Cassation Decision

  • አንድ ድርጅት ወንጀል እንዳደረገ የሚቆጠረው ከኃላፊዎች አንዱ ወይም ከሠራተኞች አንዱ ከድርጅቱ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የድርጅቱን ጥቅም በሕገ ወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም የድርጅቱን ሕጋዊ ግዴታ በመጣስ ወይም በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት ወይም አነሳሽነት ወይም አባሪነት ወንጀል ሲፈጸም ብቻ ስለመሆኑ፣ የወ/ሕግ አንቀጽ 23 እና አንቀጽ 34/1/ ጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 93/1ሀ/ እና 93/2/

     

    የሰ//.94913

    የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ከመውጣቱ በፊት በተፈፀመ ወንጀል ከተፈረደበት እና ሆኖም ግን ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ስራ ላይ ከነበረው የቅጣት አወሳሰን ይልቅ የተሻሻለው መመሪያ ለተከሳሹ ቅጣትን የሚያቀልለትና ተከሳሹን የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ ይሄው የተሻሽለው መመሪያ ላይ ያለው ቅጣት የሚፈጽምበት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ የወንጀል ህግ አተረጓጓም መርሆን መከተል ያለበት ስለመሆኑ፣ ወንጀል ህጉ ቁ 6

    Download Cassation Decision

  • አንድ ሰው በወንጀል ተከሶ በሌለበት የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በኃላ ጥፋተኛ የተባለው ስው ቀርቦ በሌለበት የተሰጠውን ውሳኔ ለማስነሳት ሳይሆን በዋናው ጉዳይ ላይ በቀጥታ ይግባኝ ከጠየቀ በኃላ በሌለሁበት የተሰጠው ውሳኔ ይነሳልኝ ብሎ ቢያመለክት በፊት የጠየቀው ይግባኝ በህጉ ላይ የተቀመጠውን የ30 ቀን የጊዜ ገደብ የሚያቋርጥ ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.198

    Download Cassation Decision

  • የቲ.ኦቲ /ተርን ኦቨር ታክስ/ ተመዝጋቢ የሆነ ሰው በህግ ፊት እንደ መረጃ /ማስረጃ / ሊያቀርብባቸው የሚገቡ ደረሰኞች ከቫት በተቀበለው የቲ.ኦ.ቲ ደረሰኝ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ /ታክስ የቲ.ኦቲ አዋጅ ቁጥር 285/194 አንቀጽ 21/