• በፍ/ብ/ህ/ቁ. 842/3/ መሰረት የተተኪ ወራሽነት ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝ ሊሟሉ ስለሚገባቸው ጉዳዮች፣

  Download Cassation Decision

 • ተተኪ ወራሽ ለመሆን ሊሟሉ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች የፍ/ሕ/ቁ. 842(3)

  የሰ/መ/ቁ/ 110040

   

  የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ/ም

   

   

  ...
 •  

  ከሳሽ በተከሳሽ ላይ ለሚደርሰው ኪሳራ ዋስ እንዲያሲዝ የሚጠየቀው ከሳሽ በክሱ ምክንያት በተከሳሽ ላይ የሚደርሰውን ኪሳራ ለመክፈል የሚያስችሉ ሁኔታዎች የሚያጠራጥር ሲሆንና ኪሳራውንም ለመክፈል የሚያስችል ሃብት ወይም ገንዘብ የሌለው በሆነ ጊዜ ስለመሆኑ

  የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 200

   

  የሰ/መ/ቁጥር 110150

  በትግራይ ክልል ገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ መሰረት ባለይዞታ አርሶ አደር ይዞታውን የመሸጥ መብት የሌለውና የኸው ተፈፅሞ ሲገኝ ይህ ውል እንዳይረጋ በማንኛውም ጊዜ ተቃውሞ ሊነሳና ጉዳዩ የቀረበለትም ፍ/ቤትም ውሉ ከጅምሩ ህገወጥ መሆኑን አውቆ ውሉ ህጋዊና ተፈፃሚነት የለውም በማለት ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ የትግራይ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 55/1994፣ አዲሱ አዋጅ ቁ. 236/2006 የፍ/ሕ/ቁ. 1678፣1716፣1718፣1195 እና 1196

   

   

  የሰ/መ/ቁ 110549

   

  የካቲት 16 ቀን 2008 ዓ.ም

  የአንድ ሰው መብትና ግዴታ ለተወላጆቹ በውርስ ሊተላለፍ የሚችለው በሟቹ ምክንያት የሚቋረጡ ካልሆነ በቀር ሟቹ በሞተበት ቀን የነበሩት መብቶችና ግዴታዎች ስለመሆናቸው፣ የፍ/ሕ/ቁ. 826/2/ ሟች የድርሻ መልቀቅ ውል ፈጽሞ ከዚያም ኑዛዜ ቢያደርግና ይኽው ኑዛዜ የድርሻ መልቀቁን ውል እስካልነካ ድረስ የውሉን ተፈጻሚነት ሊያስቀር የማይችል ወይም በአዲሱ ኑዛዜ ተተክቷል ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 900 እና 901

  Download Cassation Decision

 • በአፈጻጸም ወቅት አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት በሐራጅ ተሸጦ ከእዳ መክፈያ /ከግራ ቀኙ/ ይካፈሉ በተባለበት ጊዜ የሐራጅ ማስታወቂያ የፍ/ባለመብትን ጥቅም ላይ በቀጥታ ጉዳት እስካላደረሰ ወይም የሚያደርስ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የሐራጅ ማስታወቂያው ተገቢ ለሆነ ቀን በአየር ላይ አልዋለም ወይም በጨረታው ለሚሳተፉ ሰዎች በቂ ጊዜ አልተሰጠም የሚባልበት ሁኔታ አለመኖሩ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. አንቀጽ 445

   

  የሰ/መ/ቁ.114043

  የካቲት 18 ቀን 2008 ዓ/ም

  ዳኞች፡-

  "

  የአዲስ አበባ ከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የቤት ባለቤትነት ክርክርን አጣርቶ የመወሰን ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ፣

  Download Cassation Decision

  "
 • በቀድሞ ህግ እንደ ወንጀል የሚቆጠር ድርጊት በአዲሱ ህግ የወንጀል ድርጊት መሆኑ ቀሪ ከሆነ ጉዳዩ በወንጀል የሚታይበት አግባብ ስላለመኖሩ በአዲሱ የገቢዎችና ጉምሩክ አዋጅ መሰረት ከቀረጥ በነፃ በገባ እቃ አላግባብ መገልገል የወንጀል ተጠያቂነት ሳይሆን አስተዳደራዊ ተጠያቂነት ብቻ የሚያስከትል ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 5(3) አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀፅ 98(1)(ሀ)(ለ) የጉሙሩክ አዋጅ ቁ.859/2006 አንቀፅ 163(1)(ሀ)(ለ)
 • የሟች ንብረት (የውርስ ሃብት) ወደ ወራሾች የሚተላለፈው በመጀመሪያ የሟች እዳ ከተከፈለ ብቻ ስለመሆኑ፤- ሟች ከሞተ በኋላ ለቀብር ማስፈፀሚያ የሚወጡ ወጪዎች ከውርሱ ክፍፍል በፊት መከፈል ያለባቸው ስለመሆኑ፡- የፍ/ሕ/ቁ.1014

   

  የሰ/መ/ቁ.111216 ቀን የከቲት 15/2008 ዓ/ም

  ዳኞች፡-አልማው ወሌ

   

  ዓሊ መሀመድ

  ማንኛውም ሰው አግባብ ካለው አካል ፈቃድ ሳያገኝ በህጋዊነት ከያዘው ይዞታ ጎን ያለን የከተማ ቦታ አስፋፍቶ መከለልና መጠቀም የማይቻል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 5(2)

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ክርክር ሂደት ፍ/ቤት በማስረጃ አቀራረብና አቀባበል ሂደቶች ውስጥ ሊኖረው(ሊያደርገው) ስለሚችለው ሚና የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 136(4)፣137፣138፣143(1)፣145፣194

   

  የሰ/መ/ቁ. 111498

   

  የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም

   

  የዋስትና ውል በግልፅ መደረግና ዋሱ ለግዴታው ዋስ የሆነበት የገንዘብ ልክ በዋስትናው ውል መገለጽ ያለበት ስለመሆኑ ለዋስትናው መሠረት የሆነው ዋናው ጉዳይም ሕጋዊና ግራ ቀኙን የተስማሙበትና የሚታወቅ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፡- ፍ/ሕ/ቁ 1928፣1922 አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2/1/

   

   

  የሰ/መ/ቁ. 111778

  ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም.


  አመልካች፡- ወ/ሪት ገንዘብ ስጦታው

  ...
 • የተሻረው ህግ ይሰራ በነበረበት ጊዜ የተፈጸመ ወንጀል ሲኖርና በዚህ ህግ ግን እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ሊያስከስስም ሆነ ሊያስቀጣ አይችልም ፣ ክሱም ተጀምሮ እንደሆነ የሚቋረጥ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 5/3/ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 99፣ አዋጅ ቁ. 859/2006

  Download Cassation Decision

 • ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ተከስቷል ሊባል የሚችለው በባለእዳው በምንም መልኩ በቅድሚያ ሊያስበው ወይም ሊገምተው የሚያስችል ክስተት ሲፈጠር ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 1792 በየብስ የእቃ ማጓዝ ስራን ለመደንገግ ተሻሽሎ የወጣው አዋጅ ቁ. 547/1999

   

  የሰ/መ/ቁ. 112168

   

  የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም

   

  ...
 • በመንግስት የተወረሰን ቤት የባለቤትነት መብት ከሌለው ሰው/አካል/ መግዛት የማይንቀሳቀስ ንብረትን በቅን ልቦና ባለሀብትነትን የሚያጎናጽፍ ስላለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 47/67

  Download Cassation Decision

 • አንድን ንብረት የሸጠ ሰው የሸጠውን ንብረት ባለሃብትነት ለገዥው የማዛወር ግዴታ ያለበትና ይህንን ለመፈፀም አስፈላጊ የሆኑ ተግባራቶችን የማከናወን ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ.2273፣2281፣1771(1)፣1757

   

  የሰ/መ/ቁጥር 112328

   

  የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ/ም

   

  ዳኞች፡- አልማው ወሌ

  ...

 • አዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤት የጉዲፈቻ ስምምነትን ማስረጃን ተመልክቶ የወራሽነት ማስረጃን የመስጠት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 361/1995 አንቀፅ 41(ሸ)

   

  የሰ/መ/ቁ.112575 30/06/2008 ዓ.ም

  ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ

   

  ሙስጠፋ አህመድ ተፈሪ ገብሩ

  ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሠለ

  ...
 • አንድ ሠራተኛ ከአንድ ዓመት በታች አገልግሎት የሰጠ እንደሆነ
  ተመጣጣኝ የሆነ የረፍት ጊዜ በአገልግሎት ጊዜው ልክ
  (proportion to the length of his service) የሚሰጠው ስለመሆኑ
  አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 77(6)

   

  የሰ/መ/ቁ. 112583

   

  ...
 • አቃቤ ህግ በዋስትና መለቀቅ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ ፍርድ ቤት የዋስትና መብትን የሚከለከልበቻው ምክንያቶች ከተለየዩ ሁኔታዎች በመመልከት ሊመዝናቸው የሚገባቸው ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር67፣75

   

  የሰ/መ/ቁ. 112725 ቀን 22/02/2008 ዓ/ም

  ዳኞች፡-ተሻገር ገ/ስላሴ

  አንድ አርሶ አደር የሚጠቀምበት ይዞታ (መሬት) በህግ ስልጣን በተሰጠው አካል የተሰጠው መሆኑን እስካላረጋገጠ ድረስ የመንግስትና የህዝብ መሬትን ለረዥም ዓመት ይዤዋለሁኝ ስለዚህ ይርጋ አይመለከተኝም ብሎ የሚያነሳው ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ

   

   

  የሰ/መ/ቁ. 112906

  ቀን የካቲት 16 ቀን 2008 ዓ/ም


 
 
 

Google Adsense