Federal supreme court of Ethiopia cassation decisions

 • በአቃብያነ ህግ ሙያ የተሰማሩ ሠዎች ላይ ከዲሲፒሊን ጉዳዬች ጋር በተያያዘ ክስ በቀረበ ጊዜ ጉዳዩ በተዋረድ በተቋቋሙትና ስልጣን በተሰጣቸው አካላት ታይቶ ሊወሰን ስለሚችልበት አግባብ፣ የአቃቤ ህግ መተዳደሪያ ደንብ ቁ. 44/1991 አንቀጽ 78, 79, 82(1)(2), 83(1)(3), 84(ሀ), 85, 86(ሀ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 25, 37

  Download Cassation Decision

 • ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ የመጀመሪያውን ደረጃ ፍርድ ቤት ፍርድን ካሻሻለው ወይም የለወጠው እንደሆነ በትችቱ ላይ ለይግባኝ ባዩ የሚገባውን ዳኝነት ዘርዝሮ መግለፅ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 182(1)፣348(1)

  Download Cassation Decision

 • ካሳ አነሰኝ ወይም ተከለከልሁ ካልሆነ በቀር በኢንቨስትመንት የሚቀርቡ የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር ክርክር ይግባኞች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠው ፍርድ ቤት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 138 አንቀጽ 6/5/

   

   

  የሰ/መ/ቁ. 92991

   

  ጥቅምት 1 ቀን 2008 ዓ.ም

  አንድ ሰው የሌላውን ሰው የሥራ ድካም ወይም በሌላው ሰው ሀብት በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ እንደሆነ አላግባብ ባገኘው ጥቅም መጠን ለባለሀብቱ ወይም በጉልበቱ ለደከመው ሰው የመመለስና የመካስ ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ፣ በፍ/ሕ/ቁ 2162፣2164(1)

  Download Cassation Decision

 • የዳግም ዳኝነት (Review of Judgment) ዓይነተኛ ዓላማ ተገቢ ሁኔታዎችና ፍሬ ነገሮች ተሟልተው መገኘታቸው ሲረጋገጥ በሀሰተኛ ማስረጃ፣ በመደለያና በመሰል ወንጀል ጠቀስ ድርጊቶች ምክንያት የተዛነፈን ፍትህ ወደ ነበረበት መመለስ ስለመሆኑ፣  የዳግም ዳኝነት ጥያቄ (አቤቱታ) ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ተግባራት የሚከናወንበት በመሆኑ ጥያቄው ለሰበር ችሎት በቀረበ ጊዜ ችሎት አቤቱታውን ፍሬ ነገር የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ላላቸው የስር ፍ/ቤቶች ሊመራውና ሊያስተላልፈው በሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6(1)(ሀ)(ለ) አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ)

  Download Cassation Decision

 • በውሳኔ በተቋጨ የክስ መዝገብ ላይ የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ ለማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 31

  Download Cassation Decision

 • ፈቃድ የሌላቸው የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶችን በቤቱ ውስጥ አከማችቶ የተገኘ ሰው መሣሪያዎቹን ለመነገድ በሚል ሀሳብ የያዘ መሆኑ የተረጋገጠ ካልሆነ በስተቀር ግለሰቡ በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን የሚገባው በወንጀል ህግ አንቀጽ 481(1)(ሀ) ሣይሆን በአንቀጽ 809(ሀ) ሥር በተመለከተው ድንጋጌ መሠረት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 481(1)(ሀ), 809(ሀ)

  Download Cassation Decision

 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰበር ሰሚ ችሎት ማስረጃ የመመዘን እና ፍሬ ጉዳይን የማጣራት ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ፣ የአ.አ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 42(2)

  Download Cassation Decision

 • ትዳር ያለው አንድ የመንግስት ቤት ተከራይ በሞት በተለየ ጊዜ የተከራይነት መብቱ ለሌላኛው ተጋቢ ሊተላለፍ የሚችለው አግባብነት ባለው መመሪያ ስለመሆኑ፣

  Download Cassation Decision

 • በመንግስት በጀት በከፊልም ሆነ በሙሉ የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚፈጠሩትን የመብት ጥያቄዎች መመራት ያለበት በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ መሆን አለበት፡፡ -በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 3 (2)(ሠ) ፣ አዋጅ 515/1999 አንቀጽ 3 በአዋጅ 65ዐ/2ዐዐ1፣ ደንብ ቁጥር 214/2ዐዐ3 እና 21ዐ/2ዐዐ3

  Download Cassation Decision

 • - አንድ የስራ ውል በሰራተኛው አነሳሽነት እንደነገሩ አግባብ በማስጠንቀቂያ ወይም ያለማስጠንቀቂያ ሊቋረጥ የሚችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 31 እና 32

  Download Cassation Decision

 • -በፍትሐ ብሔር ክርክር አንድ ግዴታ እንዲፈጸምለት የሚጠይቅ ሰው የግዴታውን መኖር ማስረዳት እንደሚጠበቅበት እና በአንፃሩም ግዴታ ፍርስ ነው ወይም ተለውጧል የሚለው ወገንም ይህንኑ የማስረዳት ግዴታ ስለመሆኑ፣ ሠራተኛው በራሱ ጉድለት ባልሆነ ምክንያት ላልሰራው ስራ ደሞዝ ስለሚጠይቅበት አግባብ፣ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 54(1)፣54(2) በፍ/ሕ/ቁ. 2001(1) እና(2)

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል የተከሰሰ ሰው ጉዳዩን በሌለበት ለማየት ፍ/ቤቱ በመጀመሪያ
  ለተከሣሹ ህጉ ያስቀመጠውን ጥብቅ መስፈርት በተከተለ መልኩ
  በአግባቡ ጥሪ ሊያደርግለት የሚገባ ስለመሆኑ፣
  የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ቁጥር 161(1)(2) እና 162

  የሰ/መ/ቁ. 93577

   

  ህዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም.

  ...
 • በወንጀል የተከሰሰ ሰው ጉዳዩን በሌለበት ለማየት ፍ/ቤቱ በመጀመሪያ
  ለተከሣሹ ህጉ ያስቀመጠውን ጥብቅ መስፈርት በተከተለ መልኩ
  በአግባቡ ጥሪ ሊያደርግለት የሚገባ ስለመሆኑ፣
  የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ቁጥር 161(1)(2) እና 162

  የሰ/መ/ቁ. 93577

   

  ህዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም.

  ...
 • አንድ ሰው በቸልተኝነት ወንጀል ፈጽሟል ሊባል የሚችለው የድርጊቱን ውጤት እያወቀ ውጤቱ አይደርስም ከሚል መነሻ ድርጊቱን የፈፀመ እንደሆነ ወይም ድርጊቱ የወንጀል ውጤት የሚያስከትል መሆኑን ባያውቅም ውጤቱን ማወቅ ነበረበት ወይም ጥረት ቢያደርግ ማወቅ ይችል ነበረ ለማለት የሚቻል እንደሆነ ስለመሆኑ፣  አንድ ሰው የፈፀመው ድርጊት በቸልተኛነት ነው ለማለት በመስፈርትነት ሊወሰድ የሚገባው የድርጊቱ ፈፃሚ በድርጊቱና በውጤቱ መካከል ያለውን ግንኙነት አስመልክቶ ያለው ወይም ሊኖረው የሚገባው ግንዛቤ ስለመሆኑና ይህም የድርጊቱ ፈፃሚ የነበረው እውቀትና ግንዛቤ ወይም ሊኖረው የሚገባውን እውቀትና ግንዛቤ መመዘን ያለበት ከግለሰቡ እድሜ፣ ያለው የኑሮ ልምድ የትምህርት ደረጃ ሥራውና የማህበራዊ ኑሮ ደረጃውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 59(1), 543(2), 57

  Download Cassation Decision

 • ተጋቢዎች የጋብቻቸውን ፍቺ አስመልክቶ ጉዳዩ በመደበኛው ፍ/ቤት ቀርቦና ክርክር ተካሄዶ ውሣኔ ከተሰጠበት በኋላ በሌላ ጊዜ በተመሳሳይ ጉዳይ ሀይማኖታዊ ስርዓትን በመጠቀም በሸሪአ ፍ/ቤት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5(1)(2), 244(2)(ለ), 245(2) አዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀጽ 5(4), 6(2) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 34(5)

  Download Cassation Decision

 • በአሰሪና ሰራተኛ መካከል በሚደረግ የስራ ግንኙነት የተነሳ ለተወሰነ ጊዜ ለፕሮጀክት ስራ መደብ የተቀጠረ ሠራተኛ ከአንድ የፕሮጀክት ወደ ሌላ የፕሮጅክት ስራ አዘዋውሮ ማሰራት በአሰሪውና ሰራተኛው መካከል ላልተወሰነ ጊዜ የስራ ግንኙነት ተፈጥሯል ለማለት የማያስችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ. 377/96 አንቀፅ 30፣ አንቀፅ 10

  Download Cassation Decision

 • አንድ ሰራተኛ ሲከፈለው የነበረው የደሞዝ መጠን ከፍተኛ መሆን የሥራ ስንብት ክፍያን ከመጠየቅ የሚያግደው ስላለመሆኑ፣ አዋጅ 377/1996 አንቀጽ 39 እና አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ 2(2)ሸ

  Download Cassation Decision

 • በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 358 መመዘኛ የሚያሟላ አቤቱታ አቅራቢ (ፍርድ ተቃዋሚ) የሚቃወመው ፍርድ በይግባኝ ያልተሻረ (ዋጋ ያለው) እና ያልተፈፀመ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣

  Download Cassation Decision

 • በወንጀል ጉዳይ ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ ተከሳሹን ጥፋተኛ ሆኖ ያስገኘው ሕግ በፍርዱ ውስጥ መገለጽ እንደሚገባውና የጥፋተኝነት ውሳኔው የሚሰጥበት ድንጋጌ መፈጸሙ ከተረጋገጠው የወንጀል ፍሬ ነገር ጋር በጥንቃቄ መነጻጸር የሚገባው ስለመሆኑ፣ ወ/መ/ሕ/ስ/ስቁ. 149

  Download Cassation Decision