volume 14

volume 14

 • 43511 civil procedure/ jurisdiction/ constitution/ constitutional interpretation/ administrative law/ privatization

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኢፌዴሪ ህገ መንግስትን ለመተርጐም ባለው ስልጣን ተጠቅሞ የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻና ጉዳዩ በሚመለከተታቸው አካላት መከበርና መፈፀም ያለበት ስለመሆኑ፣  የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ የሚቀርብለትን አቤቱታ ህጋዊነት መርምሮ በመወሰን ሂደት ከፊል የዳኝነት ስልጣን ያለው አካል (quasi judicial body) እንደመሆኑ መጠን በህገ መንግስቱ የተጠበቁትን ፍትህ የማግኘት፣ የመሰማትና በእኩል ሚዛን የመታየት (የመዳኘት) መብት በሚያስከበር መልኩ ክርክሮችን ሊያስተናግድና ሊወስን የሚገባ ስለመሆኑ፣ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 62(1),37 አዋጅ ቁ. 251/93 አንቀጽ 3(1),56(1) አዋጅ ቁ. 87/86 አንቀጽ 8,9 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 337, 336, 339 Download Cassation Decision

 • 63063 contract law/ formation of contract/ tacit acceptance/ variation of contract/ form/ contract of arbitration

  ከውል አመስራረትና መቋቋም ጋር በተገናኘ ዝምታ በመርህ ደረጃ ውልን እንደመቀበል ሊቆጠር የማይችል ስለመሆኑና አንድ ውል፣ ተሻሽሏል ለማለት የሚቻለው ማሻሻያው አስቀድሞ በተደረገው የአፃፃፍ ስርዓት አይነት የተከናወነ እንደሆነ ስለመሆኑ፣  የግልግል ጉባኤ አንድን ጉዳይ በማየት የዳኝነት መፍትሔ ሊሰጥ የሚችለው ተከራካሪ ወገኖች ከተስማሙበትና የሚፀና ወይም ዋጋ ያለው ግዴታ መኖሩን መሠረት በማድረግ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1682,1683,1684,1722,2001 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 356(ሀ) Download Cassation Decision

 • 69797 contract law/ nonperformance of contract/ damage/ performance bond/ inflation

  በተዋዋይ ወገኖች መካከል ውል ባለመፈፀሙ ምክንያት የጉዳት ኪሣራ እንዲከፈል በሚል ጥያቄ በቀረበ ጊዜ በውሉ ለዚሁ ዓላማ ተዋዋዮቹ ካመለከቱት የገንዘብ መጠን በላይ እንዲከፍል ለማስገደድ የማይቻል ስለመሆኑ፣  የመልካም ሥራ አፈፃፀም ቦንድ መሰረታዊ ዓላማ በውል የተመለከተው ጉዳይ እንደውሉ ስለመፈፀሙ (የሚፈፀም ስለመሆኑ) ለማረጋገጥ ስለመሆኑ፣  አንድን ዕቃ ማቅረብ ጋር በተያያዘ የተደረገ ውልን አስመልክቶ በአቅራቢው በኩል ከእቃው ዋጋ ጋር በተገናኘ በመንግስት የታወቀ የዋጋ ግሽበት መከሰቱ አቅራቢው ውሉን ሙሉ ለሙሉ ለማቋረጥ የሚያስችለው በቂ ምክንያት ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3183(2),3188(1),1731,1734,1732,1889 Download Cassation Decision

 • 71070 custom duty law/ tax law/ period of limitation/ tax rebate

  በብልጫ የተከፈለ ቀረጥና ታክስ ተመላሽ እንዲሆን የሚቀርብ ጥያቄ ተቀባይነት የሚኖረው ዕቃው የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት አጠናቅቆ ወደ አገር ውስጥ ከገባበት ወይም ወደ ውጪ አገር ከተላከበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወር ውስጥ የቀረበ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣  ""የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቀቀ"" ማለት ስለሚቻልበት አግባብ አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀጽ 66(1), 2(17),66(29),66(2) Download Cassation Decision

 • 71537 contract law/ donation/ sale/ ownership/ period of limitation

  ከውርስ ሽያጭና ከስጦታ ውል የመነጨን የባለቤትነት መብት አስመልክቶ በሚነሣ የንብረት ክርክር የይርጋ ጉዳይ በተነሣ ጊዜ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ ለጉዳዬቹ አግባብነትና ተፈፃሚነት ባለው የህግ ክፍል እና የህግ ይዘት ታይቶ ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 71972 contract law/ construction contract/ construction specification/ variations

  ከግንባታ ሥራ ውል ጋር በተገናኘ የሚከፈል ክፍያ የሥራው ባለቤት የሆነው አካል በግንባታው ሂደት የሥራ ትዕዛዞችን እየሰጠ የሥራውን አካሄድ የመወሰንና ሥራውን በሚፈቅደው አይነት እንዲፈፀም የሥራ ተቋራጩን የማዘዝ ስልጣን ያለው ስለመሆኑ፣  የሥራ ተቋራጩ ከሥራው ባለቤት ጋር የተደረገውን የግንባታ ሥራ ውል፣ በሥራው ባለቤት በተሰጡት ፕላኖች፣ ግንባታ ዲዛይን አይነቶችና የዋጋና የሥራ ማስታወቂያ መሠረት ግንባታውን የማካሄድ ግዴታ ያለበት በመሆኑ የሥራው ባለቤት በግንባታው ሥራ ውል ሰነዱ ላይ ከተመለከተው ክፍያ ውጪ በተጨማሪነት በባለቤቱ ፈቃድና ትዕዛዞች መሠረት ለተሠሩ ሥራዎች ክፍያ ለመክፈል አልገደድም በሚል የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑና በህጉ አግባብ በባለቤቱ የተሰጡ ተጨማሪ የሥራ ትዕዛዞች የሥራ ውሉ አካል ተደረገው የሚወሰዱ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.3244,3225,(1)(2),3152(1),3266(1),3263,3265(3) Download Cassation Decision

 • 72017 civil procedure/ execution of judgment/ public auction/ damage

  አንድ ለእዳ መክፈያነት በአፈፃፀም በጨረታ እንዲሸጥ በተደረገ ንብረት ጨረታ ላይ በመካፈል የጨረታው አሸናፊ ከሆነ በኋላ የጨረታ ሽያጬን ለመፈፀም ያልቻለ ወገን ንብረቱ በቀጣይ በወጣ ጨረታ ቀርቦ ሲሸጥ የተገኘው የሽያጭ ዋጋ ዝቅተኛ የሆነ እንደሆነ የመጀመሪያው ጨረታ አሸናፊ ለተከሰተው የዋጋ ልዩነት ለፍርድ ባለዕዳው በካሣ መልክ እንዲከፈል የሚገደድ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 429 Download Cassation Decision

 • 72341 public pension/ pension/ peroid of limitation

  የጡረታ አበል ተጠቃሚ የሆነ ሰው በሌላ የመንግስት ሥራ ተቀጥሮ ያለአግባብ የወሰደው የጡረታ አበል እንዲመለስ በሚል የሚቀርብ ጥያቄ በአሥር አመት ይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑና የይርጋ ጊዜውም ግለሰቡ በሌላ የመንግስት ሥራ ከተቀጠረበት ጊዜ ጀምሮ የሚቆጠር ስለመሆኑ፣  አንድ የመንግስት ሠራተኛ ጡረታ ከወጣ በኋላ መልሶ ደመወዝ በሚያስገኝ የመንግስት ስራ ከተቀጠረ የቅጥሩ ሁኔታ በቋሚነትም ይሁን በጊዜያዊነት እንዲሁም ደመወዙ ከጡረታ አበሉ ያነሰ ሆነም አልሆነ ከደመወዙና ከጡረታ አበሉ አንዱን መምረጥ ያለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.345/95 አንቀጽ 46(1) (2) አዋጅ ቁ.209/55 አንቀጽ 30(2) የፍ/ብ/ህ/ቁ.1677(1) Download Cassation Decision

 • 72928 civil procedure/ pension/ jurisdiction/ error of law/ appeal

  ከጡረታ መብት ጋር በተገናኘ በሠራተኞች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ለማየት ስልጣን ያለው አካል የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ተቋም ስለመሆኑና በኤጀንሲው ውሣኔ ቅር የተሰኘ ሠራተኛ ቅሬታውን ለማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ፣  የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሚሰጠው ውሣኔ በፍሬ ነገር ረገድ የመጨረሻ ስለመሆኑና በውሣኔው መሠረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ቅሬታ ያለው ሠራተኛ አቤቱታውን ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት በይግባኝ የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቀ. 714/2003 አንቀጽ 56(1) (4), 57 Download Cassation Decision

 • 73247 law of succession/ certificate of heir/ revocation of certificate of heir

  አንድ ወራሽ የወራሽነት መብት በሌለው ንብረት ላይ ከህግ ውጪ የወራሽነት ሠርተፍኬት መያዙ በተረጋገጠ ጊዜ ይኸው ማስረጃ እንዲሰረዝ አቤቱታ ሊቀርብ ስለመቻሉ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.998(1) Download Cassation Decision

 • 73514 criminal law/ criminal procedure/ constitution/preliminary objection

  ተከሳሽ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በተመለከተ በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት ሊያቀርባቸው ስለሚችላቸው መከራከሪያዎች  ተከሳሽ በመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያነት የሚያቀርባቸው መቃወሚያዎች በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130 ላይ የተመለከተቱት ጉዳዬች ጋር ብቻ በተገናኘ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  ማንኛውም ሰው የወንጀል ክስ ሲቀርብበት የተከሰሰበት የወንጀል ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈፀሙ ወይም አለመፈፀሙ ወንጀል መሆኑ ካልተደነገገ በስተቀር ሊቀጣ የማይችልና ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ተፈፃሚ በነበረው ህግ ከተመለከተው የቅጣት ጣሪያ በላይ ሊቀጣ የማይችል ስለመሆኑ፣  የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራ ስለመሆኑና ዳኞች ወንጀሉ በተፈፀመበት ጊዜ ክስ የቀረበበት ድርጊት ወንጀል ስለመሆኑ የሚደነግገው ህግ ፀንቶ በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት መሆኑን ከተረዱ በማናቸውም ጊዜ አንስተው ውሣኔ ለመስጠት የሚችሉ ስለመሆኑ፣  ፍ/ቤቶች በዐ/ህግ የቀረበ የወንጀል ክስ በህገ-መንግስቱና በወንጀል ህጉ የሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር የተቀመጡ መርሆዎችና ድንጋጌዎችን የሚያሟሉ መሆን አለመሆኑን በመመርመር የመወሰን ግዴታ ያለባቸው ስለመሆኑ፣ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 5(2) ,13(1), 22(1 ) የወ/ህ/አ. (414/96)3,402,419,5(2) የወ/ህ/ቁ.(214/74) አለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ስምምነት (ICCPR) አንቀጽ 15(1) የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 130(2)(1) Download Cassation Decision

 • 74036 civil society organization/ source of funding/ foreign source of funding

  አንድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የበጐ አድራጐት ድርጅት ወይም ማህበር ከውጭ ምንጭ በህጉ ከተመለከተው የገንዘብ መጠን በላይ እንዲሰበስብ ሊፈቀድ የማይችል ስለመሆኑ፡ አዋጅ ቁ. 621/2001 አንቀጽ 2(2),(3)(4),14(5), 14(2), 6, 90, 111(2), 112,108,110,  ደንብ ቁጥር 168/2001 አንቀጽ 18(3),10(2),36 Download Cassation Decision

 • 74237 Criminal law/ tax law/ value added tax (VAT)/ criminal liability of corporate bodies/ managers

  አንድ የንግድ ድርጅት (ማህበር) የተጨማሪ እሴት ታክስ ህግንና ማሻሻያውን ተላልፏል በሚል በወንጀል ጥፋተኛ ሊሰኝና ሊቀጣ ስለሚችልበት አግባብ፣  የህግ ሰውነት የተሰጠው (legal personality) ድርጅት የወንጀል ተካፋይ ሊሆን የሚችልበት አግባብ፣  የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት ወንጀል እንዳደረገ ተቆጥሮ የሚቀጣው ኃላፊዎቹ ወይም ከሰራተኞቹ አንዱ ከድርጅቱ ሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የድርጅቱን ጥቅም በህገ ወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም ህጋዊ ግዴታን በመጣስ ወይም ድርጅቱን በመሳሪያነት ያለአግባብ በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ በአነሳሽነት ወይም በአባሪነት ወንጀል ሲያደርግ ስለመሆኑና የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በወንጀል ተከስሶ የጥፋተኛነትና የቅጣት ወሣኔ እስከተሰጠበት ድርስ ድርጅቱ የወንጀሉ ተካፋይ እንደሆነ የሚቆጠር ስለሆነ ጥፋተኛ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 34(1),(2) አዋጅ ቁ. 285/95 አንቀጽ 56(1) Download Cassation Decision

 • 74451 Family law/ common property/ divorce/ condominium house/ constitution

  የኮንዶሚኒየም ቤትን በጋብቻ ወቅት እያሉ የደረሳቸው ባልና ሚስት የቤቱ ቅድመ ክፍያ በጋብቻ ወቅት ከተፈራ የጋራ ሀብት የተከፈለ እንደሆነና ቤቱን ለማሳመርና ለሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከጋራ ሀብቱ ወጪ በማድረግ ጥቅም ላይ በዋለበት ሁኔታ ጋብቻው በፍቺ የፈረሰ እንደሆነ ቤቱ ለተጋቢዎቹ፣ ሊከፋፈል ስለሚችልበት አግባብ፣ እንዲሁም በፍቺ ጊዜ እኩል መብት የሚኖራቸው ስለመሆኑ፣ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 35(1)  በህገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸውን ቤተሰብ የመመስረት መብት በመጠቀም ጋብቻ የፈፀሙ ወንዶች እና ሴቶች በጋብቻው አፈፃፀም፣ በጋብቻው ዘመን Download Cassation Decision

 • 74734 law of succession/ will/ form/ notorization

  በአንድ ቦታ ከተደረገ በኋላ በሌላ ጊዜ ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፊት ቀርቦ እንዲረጋገጥና ማህተም እንዲደረግበት የተደረገ የኑዛዜ ሰነድ በህጉ ዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት እንደተደረገ ኑዛዜ የማይቆጠር ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.881,882 Download Cassation Decision

 • 74791 Family law/ declaration of absence/ dissolution of marriage because of absence

  የመጥፋት ውሣኔ የተሰጠበት ሰው ቀደም ሲል ጋብቻ የነበረው እንደሆነ የጠፋው ሰው መመለስ በመጥፋት ውሣኔው የፈረሰውን ጋብቻ እንደገና ተመልሶ ህይወት እንዲዘራ (እንዲፀና) የማድረግ ውጤት አለው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  በፍ/ቤት የተሰጠ የመጥፋት ውሣኔ መሻር በመጥፋት ውሣኔው መሠረት የፈረሰን ጋብቻ ከፈረሰበት ቀን ጀምሮ (ግለሰቡ ከተመለሰበት ቀን ጀምሮ) መልሶ እንዲቋቋም (እንዲፀና) ለማድረግ የሚያስችል ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.170,171 Download Cassation Decision

 • 74890 civil procedure/ evidence law/ admissiblity of evidence

  አንድን ክርክር ለማስረዳት የቀረበን ማስረጃ ህጋዊነት አስመልክቶ የሚቀርብ ክርክር ሊቀርብና ታይቶ ሊወሰን የሚገባው በዚያው ዋናው ጉዳይ በቀረበበት ፍ/ቤት ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 74950 contract law/ loan/ consumer loan/ notice/ interest

  የአላቂ ነገር ብድር ውል ጋር በተገናኘ፣ የመመለሻ ጊዜው በግልጽ ተለይቶ የተሰጠን የገንዘብ ብድር በተመለከተ አበዳሪው በውሉ የተመለከተው ጊዜ ካለፈ በኋላ ተበዳሪው የብድሩን ገንዘብ እንዲመለስ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዴታ የሌለበት ስለመሆኑ፣  የብድሩ ገንዘብ መክፈያ ጊዜው በተወሰነ የብድር ውል ስምምነት ገንዘብ የተበደረ ወገን የመክፈያ ጊዜው ካለፈበት (ካበቃበት) ጊዜ ጀምሮ ወለድ ለመክፈል ስምምነት ያልተደረገ ቢሆንም፣ በድሩን ከነ ህጋዊ ወለዱ ለመክፈል የሚገደድ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.2482(2)(3),2483, 2489(1),1676, 2478 Download Cassation Decision

 • 75034 public service/ civil procedure/ jurisdiction/ administrative law/ prosecutors/

  የአቃቤ ህግ ሙያን በሹመት የሚያከናውኑ ሰዎች ጋር በተገናኘ ቅጥር፣ ዝውውርና የደረጃ እድገትን አስመልክቶ የሚቀርብ አቤቱታን አይቶ ለመወሰን ስልጣን የተሰጠው አካል የአቃቤያነ ህግ አስተዳደር ጉባኤ ስለመሆኑና መደበኛ ፍ/ቤቶች ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ፣ ደንብ ቁ.24/99 አንቀጽ 46(3), 41, 44, 2 (4) አዋጅ 568/2000 አንቀጽ 2(7),3,10(1),4,5 የአ/አ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁ.6/2000 አንቀጽ 2(5)(ሐ) Download Cassation Decision

 • 75343 property law/ constitution/ expropriation/ compensation

  በአንድ ወቅት የነበረን የተገነባ የመንገድ ደረጃ መነሻ (መሠረት) በማድረግ በመንገዱ ግራ ቀኝ አዋሣኝ በሆነ ይዞታ ላይ ተገቢውን ርቀት በመጠበቅ ንብረትን ያፈራ ሰው በሌላ ጊዜ የመንገዱ ደረጃ ከፍ እንዲል በመደረጉ የተነሣ በአዋሣኝ ይዞታው ላይ ግለሰቡ ያፈራቸው ንብረቶች ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ፣ ጉዳት ያደረሰው ወገን ካሣ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት (የሚኖርበት) ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 65/1936 አንቀጽ 2(ሀ) አዋጅ ቁ. 66/1936 አንቀጽ 1(ለ) አዋጅ ቁ. 455/1997,የኤ.ፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40(8) Download Cassation Decision

 • 75387 Criminal law/ principle of legality/ confiscation of property

  ፍ/ቤቶች በወንጀል ረገድ የሚሰጧቸው ማናቸውም ውሣኔ በወ/ህ/አ. 2 የተደነገገውን የህጋዊነት መርህ መሠረት በማድረግ መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ ፍ/ቤቶች በወንጀል ጉዳይ ንብረት ወይም ሀብት እንዲወረስ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዲሆን በሚል ውሣኔ ለመስጠት የሚችሉት በወንጀል ህግ በግልጽ የተደነገገ ድንጋጌ የተመለከተ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣  በወንጀል ጉዳይ አንድ ንብረት (ሀብት) እንዲወረስ ወይም ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ሊወሠን የሚችለው ንብረቱ (ሀብቱ) አንድን ሰው ለወንጀል ሥራ እንዲያነሳሳ ወይም ወንጀሉን ለመስራት እንዲረዳው ወይም ደግሞ ወንጀሉን ለፈፀመበት ዋጋ እንዲሆነው የተሰጠው ወይም ሊሠጠው የታቀደን ማንኛውም ጥቅም የተመለከተ ንብረት (ሀብት) ስለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለመሆኑ ወይም ንብረቱ (ሀብቱ) የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም ያገለገለ ወይም ሊያገለግሉ የሚችሉ ወይም የወንጀል ተግባር ፍሬ የሆኑ ማናቸውም ነገሮች ጋር የተያያዘ ወይም የተመለከተ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 98,100,140, 2(1) (2) Download Cassation Decision

 • 75414 property law/ immovable property/ title deed/ administrative law/ justiceable matter

  የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ህጋዊነትና ተቀባይነት ጋር በተናኘ የምስክር ወረቀቱ ሊሰጥ የቻለው የንብረት ባለሀብትነት መብትን ከአንዱ ወገን ወደ ሌላው እንዴት መተላለፍ እንዳለበት በህጉ የተመለከተውን ደንብና ሥርዓት ሳይከተል ስለሆነ የንብረቱ ባለሀብት ስለመሆን የህግ ግምት መውሰጃ የሆነው የባለቤትነት የምስክር ወረቀት ቀሪ ነው፣ ሊሰረዝ ይገባል በማለት የሚቀርብ አቤቱታ በፍ/ቤት ሊረጋገጥ የሚችል የዳኝነት ጥያቄ እንጂ ጉዳዩ በፍርድ ሊያልቅ የሚችል አይደለም ለማለት የሚያስችል ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1195,1196፣Download Cassation Decision

 • 75743 contract law/ mortgage/ registration of mortgage/ error

  የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ አመዘጋገብ ጋር በተያየዘ በተፈፀመ ስህተት ንብረቱን በመያዣ የያዘው ወገን የሚደርስበትን ጉዳትና ኪሣራ ኃላፊነቱን በአግባቡና በጥንቃቄ ባለመወጣት ስህተቱን የፈፀመው የሚመለከተው የአስተዳደር አካል ጉዳትና ኪሣራውን በመያዣ በተያዘው ንብረት ዋጋ መጠን ለመክፈል ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1640(2), 3052, 3053(1),3081 Download Cassation Decision

 • 75788 civil procedure/ jurisdiction/ local jurisdiction/ execution of judgment/ procedure in execution of judgment

  የፍ/ቤቶች የግዛት ስልጣን በዋነኛነት መሠረት የሚያደርገው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ጉዳይ የተፈጠረበት ቦታ ለተከራካሪ ወገኖች የሚኖረውን አመቺነት ሲሆን የሥረ ነገር ስልጣን መሠረት የሚያደርገው ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ይዘት፣ የተከራካሪ ወገኖችን መብትና ጥቅም ክብደትና መጠን እንዲሁም የጉዳዩን የውስብስብነት ደረጃ ስለመሆኑ፣  ፍርድን የማስፈፀም ጉዳይ በስረ ነገር ክርክር ተረጋግጠው የፍርድ ሀይል ያገኙትን የተከራካሪ ወገኖች መብቶችና ግዴታዎች በሥነ ሥርዓት ህጉ የተደነገገውን የአፈፃፀም ስርዓት ተከትለው እንዲፈፀሙ ከማድረግ ውጪ አዲስ መብትና ግዴታ የሚቋቋምበት ሂደት ስላለመሆኑና የማስፈፀም ስልጣን በመርህ ደረጃ የፍ/ቤቶች የሥረ ነገር ስልጣንን የሚከተል ስለመሆኑ፣  አስፈላጊ እና ተገቢ በሆኑ ሁኔታዎች ሥረ ነገሩን የወሰነ ፍ/ቤት በአፈፃፀም ጉዳዮችን በውክልና የሥረ ነገር ስልጣን ለሌለው ፍ/ቤት ሊያስተላልፍ ስለመቻሉ፡ አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 5(2) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 371, 372, 9, 10 Download Cassation Decision

 • 76394 commercial law/business organization/ joint venture/ partnership

  የእሽሙር ማህበር ህጋዊ ሰውነት የሌለው እንዲሁም በጽሁፍ መረጋገጥና ሌሎች የንግድ ማህበሮችን በተመለከተ የተደነገጉት የማስታወቅና የማስመዝገብ ሥርዓቶች የማይፈፀምበት ነው በሚል ምክንያት ብቻ የእሽሙር ማህበርን አስመልክቶ ማህበሩ እንዲፈረስ በሚልና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዬችን አስመልክቶ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ውድቅ በማድረግ የሚሰጥ ውሣኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፣  የእሽሙር ማህበር የንግድ ሥራ እንቅስቃሴ የሚያደርገው በሸሪኮቹ ስም ስለመሆኑና ሸሪኮቹም እንደተራ ተዋዋይ ወገኖች የሚታዩ ስለመሆናቸው የንግድ ህግ ቁ. 212(1),272 Download Cassation Decision

 • 76825 contract law/ fund raising/ tender

  ገቢ ለማስገኘት በተዘጋጀ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን በተደረገ ጨረታ ተሣታፊ በመሆን የጨረታውን ገንዘብ በመክፈል መሬት ተረክቦ ለልማት ለማዋል በሚል ጨረታው ተወዳድሮ የጨረታው አሸናፊ የሆነ ወገን ጨረታውን ካዘጋጀው አካል ጋር የውል ስምምነት እንዳደረገ የሚቆጠር በመሆኑ በጨረታ ያሸነፈበትን የገንዘብ መጠን ለአዘጋጁ ለመክፈል የሚገደድ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ፤ህ/ቁ.1771(1),1688(2),1757 Download Cassation Decision

 • 76976 custom duty law/ vehiecle/ ownership/ criminal law/ confisication/ fine

  የተሽከርካሪ ባለቤት የሆነ ሰው በተሽከርካሪው የተፈፀመ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ህግን የመጣስ ወንጀል ከራሱ እውቀት ወይም ፈቃድ ወጪ መሆኑን ማስረዳት የቻለ እንደሆነ የተፈፀመው ወንጀል ክብደት እየታየ የገንዘብ መቀጮ ከፍሎ ተሽከርካሪው ሊለቀቅለት (ላይወረስ) የሚችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀጽ 109(1) የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መመሪያ ቁ.50/2003 አንቀጽ 6(2) Download Cassation Decision

 • 76977 insurance law/ scope of liability of the insurer

  መድን ሰጪ የሆነ አካል በመድን ውሉ ለተመለከተው አደጋ ብቻ ለመድን ገቢው የመድን ሽፋን ለመስጠት የሚገደድ ስለመሆኑ፣ የንግድ ህግ ቁ. 663(1),665(1) Download Cassation Decision

 • 77097 Criminal law/ period of limitation/ interruption of counting of period of limitation

  በወንጀል ጉዳይ የወንጀል ክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን አቆጣጠር ጋር በተገናኘ ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱን ፈጽሟል በሚል የተጠረጠረ ሰው ላይ የሚያደርገው ምርመራ የይርጋ ጊዜውን የሚያቋርጠው ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ.221 106(1), 420(2), 271 (1) (ሠ) 219 (2) Download Cassation Decision

 • 77134 labor law dispute/ fault of worker

  ሠራተኛ ተቀጥሮ የሚሰራበትን አሰሪ ተቋም መልካም ስምና ዝና እንዲሁም ጥቅምና ህልውና አደጋ ላይ በሚጥሉ ተግባራት የሚፈጽመው ጥፋት መጠንና ደረጃ እና የሚወሰድበትን እርምጃ ለመወሰን ሠራተኛው ከሚሰራው የሥራ አይነትና ባህሪ እንዲሁም ከአሰሪና ሠራተኛ ህጉ መንፈስና ዓላማ አንፃር መታየት ያለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 27(1)(ሸ)(ረ) Download Cassation Decision

 • 77169 law of succession/ will/ form/ contestation of will/ disinhersion/ civil procedure/ splitting of claim

  የኑዛዜን ፎርማሊቲና የይዘቱን ህጋዊነት አስመልከቶ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ተቃውሞውን አቅርቦ ውድቅ የተደረገበት ወገን በሌላ ጊዜ በድጋሚ የኑዛዜው ይዘት ጋር በተገናኘ ተናዛዡ ከውርስ ነቅሎናል፣ እንዲሁም ሊደርሰን ከሚገባው ድርሻ ከ1/4ኛ በላይ ጉዳት ደርሶብናል በሚል ኑዛዜው እንዲሻር የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣  ኑዛዜ የህጉን ፎርማሊቲ የጠበቀ ነው በሚል በፍ/ቤት መጽደቅ ኑዛዜው መብታችንን ይነካል በማለት ክርክር የሚያቀርቡ ወገኖች ክርክራቸውን ለዳኝነት አካል ከማቅረብ የማይከለክል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.51, 216, 217 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1123 Download Cassation Decision

 • 77238 Extra contractual liability/ administrative law/ construction permit/ negligence/ damage/ compensation

  የፌዴራልና የክልል ከተማ አስተዳዳር አካላት የግንባታ ፈቃድ ከመስጠታቸው በፊት የቴሌኮሚኒኬሽን ወይም የኤሌክትሪክ ሀይል አውታር ስለመኖሩ እንዲሁም ፈቃድ ጠያቂው አካልም ግንባታን ከማካሄዱ በፊት በቴሌኮሚኒኬሽንና በኤሌክትሪክ ሀይል አውታር ላይ ጉዳት የማያደርስ መሆኑን በቅድሚያ የማረጋገጥ ግዴታ ያለባቸው ስለመሆኑና በዚህም የተነሳ በቸልተኝነት ግንባታ በማከናወን ጉዳት ያደረሰ ወገን በኃላፊነት የሚጠየቅ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.464/97 አንቀጽ 3(3) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2027(1),2035(1),2028(1),2091 አዋጅ ቁ.49/89 አንቀጽ 23(1) Download Cassation Decision

 • 77479 civil procedure/ jurisdiction/ constitution/ justiceable matter/ religious institutions/

  አንድ ሰው በፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ለማስወሰን የሚችለው ከህግ የመነጨ መብት ያለው መሆኑን በክሱ ውስጥ በዝርዝር በፍሬ ነገር ደረጃ ማመልከት የቻለ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣  ሀይማኖታዊ (መንፈሣዊ) ትምህርት ለመስጠትና ለማሰልጠን በሚል ከሚቋቁሙ ተቋማት ጋር በተገናኘ በተማሪነት ማን እንደሚመለመል፣ ምን ምን መስፈርቶች ሊሟሉ እንደሚገባ፣ የመሰፈርቶቹ መሟላትና አለመሟላት እንዲሁም በተቋሙ ትምህርት የሚከታተሉ ተማሪዎች ከትምህርት አቀባበል ሂደት ወቅት ሊገልጿቸው ስለሚገቡ የዲሲፕሊን ጉዳዬች ወዘተ በሀይማኖት ተቋማቱ የሚወሰን ስለመሆኑና ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ክርክሮችን መደበኛ ፍ/ቤቶች አይቶ ለመወሰን ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ፣  የግለሰብ ፍትህ የማግኘት መብት በፍ/ቤቶች ተግባራዊ ሊደረግ የሚችለው በፍርድ ሊያልቁ የሚባቸው ጉዳዬችን በተመለከተ ብቻ ስለመሆኑ፣ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37 Download Cassation Decision

 • 77842 Criminal law/ plea guilty/

  አንድ ተከሳሽ የተከሰሰበትን የወንጀል ክስ ይዘት በሚገባ ተረድቶና አድራጐቱን በተመለከተም እንደቀረበበት የወንጀል ክስ በዝርዝር መፈፀሙን ገልፆ በማመን የእምነት ቃሉን ሰጥቷል በሚል መነሻ በተከሣሹ ላይ የጥፋተኝነት ውሣኔ በአግባቡ ተሰጥቷል ለማለት ስለሚቻልበት አግባብ፣  ፍ/ቤቶች ተከሣሹ የቀረበበትን ክስ በተመለከተ በድርጊቱ አፈፃፀም ረገድ የገለፀውን ዝርዝር የአፈፃፀም ሁኔታ በመዝገብ ላይ ባለማስፈር በደፈናው ክሱን አምኗል በማለት የሚሰጡት የጥፋተኛነት ውሣኔ ተገቢ ስላለመሆኑ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ.134(1) የወ/ህ/አ.23 Download Cassation Decision

 • 78398 contract law/ written contract/ form/ sale of immovable property/ notorized contract/ parole evidence rule

  በተዋዋይ ወገኖች በተደረገ የጽሁፍ ሰነድ ላይ የሚገኝ የስምምነት ቃል እንዲሁም በሰነድ ላይ ስለተመለከተው (ስለተፃፈው) ቀን በተፈራራሚዎቹ መካከል ውሉ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ነው በሚል ለመደምደም የሚቻለው እንደ ውለታው አይነት የጽሁፉ ውል አደራረግን በተመለከተ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ በተሟላ ሁኔታ የተዘጋጀና የያዘ እንደሆነ ስለመሆኑ፣  የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ጋር በተገናኘ ውሉ በውል አዋዋይ ፊት በህጉ አግባብ ባልተደረገበት ሁኔታ በውሉ ላይ የሠፈሩት ማናቸውም የውል ቃሎች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዳሉ የሚታመኑና በማናቸውም የሰው ምስክርነት ቃል ማስተካከል አይቻልም ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  አንድ ውል በህግ ፊት የፀና ነው እንዲባል በህግ ውሉ የሚደረግበትን አግባብ በተመለከተ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን በተመለከተ የተደረገ ካልሆነ በቀር ውሉን መሠረት በማድረግ እንደውሉ ይፈፀምልኝ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ2005(1),1678(ሐ),1719(2,1723) Download Cassation Decision

 • 78414 labor law dispute/ evidence law/ criminal judgment as evidence

  የሥራ ግዴታን ካለመወጣት ጋር በተገናኘ ሠራተኛ የሆነ ሰው ከአሰሪው የተረከበው ንብረት ላይ ጉዳት እንዲከሰት በማድረጉ ወይም ንብረቱ እንዲጐድል (እንዲጠፋ) በማድረጉ ምክንያት በወንጀል ጉዳይ ክስ ቀርቦበት ጥፋተኛነቱ የተረጋገጠ እንደሆነ በተመሣሣይ ጉዳይ ሠራተኛው በአሰሪው ንብረት ላይ ባደረሰው ጉዳት መጠን በፍትሐብሔር ሊጠየቅ ስለመቻሉ፣  ከአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሠራተኛው በአሰሪው ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ በወንጀል ጉዳይ ተከስሶ ጥፋተኛ የተባለ እንደሆነ ጉዳት የደረሰበትን ንብረት በተመለከተ በፍትሐብሔር ተጠያቂ ሊደረግ የሚገባ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 515 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2149 Download Cassation Decision

 • 78444 contract law/ banking/ mortgage/ period of limitation/ lapse of mortgage

  የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት ውጤት የሚኖረው ከተፃፈበት ቀን አንስቶ እስከ አስር ዓመት ድረስ ነው በሚል የተደነገገው ድንጋጌ የይርጋ የጊዜ ገደብን የሚደነግግ ሣይሆን የመያዣ ውሉ ቀሪ የሚሆንበት ወይም በህግ ውድቅ የሚደረግበት (Lapse of Mortgage Right) ስለመሆኑ፣  የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘ ባንክ በመያዣው ላይ ያለው መብቱ በይርጋ ቀሪ የሚሆነው የመያዣ ውሉ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ አስር ዓመት ከማለፉ በፊት በመያዣ መብቱ መገልገል ያልጀመረ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3058 (1)(3) Download Cassation Decision

 • 78536 labor law dispute/ transfer/ promotion

  በአሰሪ ከተደረገ የሥራ ቦታ ዝውውር ጋር በተያያዘ ሠራተኛው ወደነበረበት ሥራ ቦታና መደብ እንዲመለስ በፍ/ቤት ሲወሰን አሰሪው ሠራተኛው የሥራ ዝውውሩ ከመከናወኑ በፊት ይሰራበት ወደነበረበት ቦታና የሥራ መደብ በትክክል መመለስ ያለበት ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 78856 Criminal law/ sentencing/ pension/ effect of sentencing on pension

  ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተገናኘ በወንጀል ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ የተጣለበትን ቅጣት ፈጽሞ ያጠናቀቀ ሰው በፍርድ ቤት መሰየም በግለሠቡ የጡረታ መብት ላይ ስለሚኖረው ውጤት  በመሰየም ሊገኝ የሚችለው መብት ግለሰቡ ከመሰየሙ አስቀድሞ በቅጣት ቀሪ ሆኖበት የነበረውን መብት ሳይሆን ግለሰቡ ከተሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ፊት ሊጠበቅለት የሚገባውን መብት በተመለከተ ብቻ ስለመሆኑ፣  የመንግስት ሰራተኛ የነበረና የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነ ሠው በወንጀል ጉዳይ ተከስሶና ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ በፍ/ቤት ቢያንስ የ3 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት የተወሰነበት በመሆኑ የጡረታ መብቱን እንዲያጣ የተደረገ ሠው ከቅጣቱ በኋላ በፍ/ቤት መሰየሙ አስቀድሞ በቅጣት ቀሪ ሆኖበት የነበረውን የጡረታ መብቱን መልሶ ለማግኘት የማያስችል ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 231,235(1),232 አዋጅ ቁ. 209/55 አዋጅ ቁ. 5/67 አዋጅ ቁ.345/95 አንቀጽ 52/1/ Download Cassation Decision

 • 78856 property law/ intellectual property/ three dimension (3D) work

  ባለ ሶስት አውታር (three dimention) ቅርጽ ሥራ ከባለቤቱ ፈቃድና ፍላጐት ውጪ በወረቀት ላይ እንዲታተሙና እንዲሰራጩ ማድረግ የቅጂ መብት ጥሰት የሚያስከትል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 410/96 አንቀጽ 34(4) Download Cassation Decision

 • 78865 labor law dispute/ individual labor dispute/ collective labor dispute

  ቀደም ሲል ስናገኘው የነበረው የደመወዝ መጠን የተቀነሠ ስለሆነ እንዲስተካከልልን በማለት በሠራተኞች የሚቀርብ ክስ የወል የሥራ ክርክር ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 78945 public service/ university professor/ appeal

  የመንግስት ዩኒቨርስቲ መምህራንን በተመለከተ ከዲሲፕሊን ግድፈት ጋር በተገናኘ የሚሰጥ ውሣኔ በአስተዳደር ፍ/ቤት በይግባኝ ሊስተናገድ ስለሚችልበት አግባብ፣ አዋጅ ቁ. 515 /99 አንቀጽ 2(8),22(3),32(3) አዋጅ ቁ. 650/2001 አፀከት 44(ኀ) Download Cassation Decision

 • 79212 labor law dispute/ unlawful termination of contract of employment

  ሥራና ሰራተኛን ከመምራት እና ከመቆጣጠር ባለፈ በሠራተኛ ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ለመውሰድም ሆነ ከሥራ ለማሠናበት ስልጣን በሌለው የቅርብ አለቃ ሠራተኛው ሥራ እንዲለቅ የተነገረ መሆኑ የሥራ ውል ተቋርጧል ወደሚል ድምዳሜ የሚያደርስ ስላለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 3(2)(ሐ) Download Cassation Decision

 • 79394 property law/ land law/ rural land/ law of contract/ object of contract unlawful/donation

  የመሬት ባለ ይዞታ የሆነ አርሶ አደር ይዞታውን ላለበት እዳ ለ3ኛ ወገን በመያዣነት ለመስጠት ወይም በስጦታ የቤተሰብ አባል ላልሆነ ሰው ለማስተላለፍ መብት የሌለው ስለመሆኑ፣  በህግ እንዲደረግ ያልተፈቀደ እና/ወይም የህግ ክልከላ ባለበት ጉዳይ ላይ የተደረገ ውል ህገ ወጥ ውል በመሆኑ ከመነሻው ውጤት የሌለውና ፈራሽ ስለመሆኑ፣  የውሉ መሠረታዊ ዓላማ በህግ ያልተፈቀደና የተከለከለ ሆኖ ሲገኝ ዳኞች ህገ ወጥ የሆነው ውል በቀረበላቸው ማንኛውም ጊዜ ህጋዊ ውጤትና ተፈፃሚነት የለውም በማለት ለመወሰን የሚችሉና ህገ ወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ በህጉ የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ሊሆን የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 130/99 አዋጅ ቁ.89/89 አንቀጽ 2(3) አዋጅ ቁ. 456./97 አንቀጽ 8(2),1) Download Cassation Decision

 • 79465 civil procedure/ third party intervention/ third party defendant

  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.43 መሠረት ወደ ክርክር እንዲገባ የተደረገ 3ኛ ወገን በክርክሩ ሂደት ሊያነሣ ስለሚችለው የክርክር አይነትና አድማስ፣  3ኛው ወገን ሊያነሣ የሚችላቸው የክርክር ፈርጆች በአንድ በኩል ከተከሣሽ ጋር ሆኖ ድርሻ ክፍያ ወይም ስለተከሣሽ ሆኖ የካሣ ክፍያ የመክፈል ግዴታ ያለበት መሆኑን ተቀብሎ በተከሣሽ እግር ተተክቶ ተከሣሽ ለከሣሽ ኃላፊነት የማይኖርበት መሆኑን፣ ኃላፊነት አለበት የሚባል ቢሆን እንኳን ሊከፈል የሚገባው የካሣ ክፍያ መጠን ላይ ከከሣሽ ጋር ንጽጽር በማድረግ መሟገት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ድርሻ ወይም ካሣ ለመክፈል ለተከሣሽ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ግዴታ የለብኝም በማለት መከራከር ስለመሆናቸው፤  3ኛ ወገን ጣልቃ ገብ በክርክር ሂደቱ መሟገት የሚችለው ከተከሣሽ ጋር ብቻ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 43 አስፈላጊነት ተከታታይ ክስ ሳይኖር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች በአንድነት እንዲታዩ በማድረግ የኃላፊነት መጠኑን እንዲሁም ከፋዩን ወገን በመለየት የመጨረሻ እልባት ለመስጠት ስለመሆኑ፣  በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 43 መሠረት ጣልቃ የሚገባ ወገን ከመነሻውም ከተከሳሹ ጋር የህግ ወይም የውል ግንኙነት የለኝም በማለት ክርክር ያቀረበ እንደሆነ በመካሄድ ላይ ባለው ክርክር ተሣታፊ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የማይኖር ስለመሆኑና ይህን መሰል ክርክር ራሱን በቻለ ሌላ መዝገብ ታይቶ ሊወስን የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 43(1),76 የፍ/ብ/ህ/ቁ.1896,1897,1908,1909 የንግድ ህግ ቁ.687,688,683 Download Cassation Decision...

 • 79555 civil procedure/ body corporate/ papuer/ bankruptcy

  በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው ተቋማት (ወገኖች) በድሀ ደንብ ዳኝነት ሳይከፍል በፍ/ቤት ለመስተናገድ የሚያቀርቡት ጥያቄ ተቋሙ ከሚገኝበት የገንዘብ አቋም አኳያ ተገናዝቦ መታየት ያለበት ስለመሆኑና ተቋሙ የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም (Financial status) ለመለየት ተቀባይነት ስለሚኖረው የማስረጃ አይነት፣  ለዳኝነት የሚከፈለውን ገንዘብ ለመክፈል አልችልም በሚል በድሀ ደንብ ለመስተናገድ የህግ ሰውነት የተሰጠው ተቋም የሚያቀርበው አቤቱታ ሊስተናገድ ስለሚችልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 467 Download Cassation Decision

 • 79853 labor law dispute/ period of contract of employment/ permanent position

  አንድ ሠራተኛ በባህሪው ቀጣይነት ባለው ሥራ ላይ መቀጠሩ መረጋገጡ ብቻ ሠራተኛው ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠረ የሚያስቆጥረው ስላለመሆኑ፡ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 24(1) Download Cassation Decision

 • 79860 criminal law/ execution of judgment/ confisication of property/ priority of purchase/ maintainance

  በወንጀል ጉዳይ የተከሰሰው ሰው ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ ንብረቱ በቅጣት ለመንግስት እንዲወረስ በተወሰነ ጊዜ በአፈፃፀም ደረጃ ከአጥፊው (ወንጀለኛው) ንብረት ውስጥ ለቤተሰቡ ህይወትና መተዳደሪያ ሊውል የሚገባውን ድርሻ ለመወሰን ስለሚቻልበት አግባብ፣  በውርስ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ከተወሰነው የአጥፊው (የወንጀለኛው) ሀብትና ንብረት ውስጥ ለቤተሰቡ ህይወት መተዳደሪያ ሊውል የሚገባው ድርሻ ሊሸፍናቸው የሚገባው የወጪ አይነቶችና መጠናቸው፣  የአጥፊው (ወንጀለኛው) ጋር ጋብቻ የመሠረተ ሰው እንዲወረስ ከተወሰነው ንብረት ግማሽ ድርሻ የነበረው መሆኑን መሠረት በማድረግ በአፈፃፀም የሚያነሣው የቅድሚያ ግዢ መብት ጥያቄ የህግ መሠረት የሌለው በመሆኑ ጥያቄው እንደ መብት አቤቱታ ሊቀርብበት የማይችል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 98(ለ)(መ), 98(3) (ለ) Download Cassation Decision

 • 79907 contract law/ surety/ written contract/ signature/ denial/ witnesses

  ከዋስትና ውል ጋር በተገናኘ ዋስ የሆነ ወገን በውሉ ላይ የተመለከተውን ፊርማ የእርሱ አለመሆኑን ወይም የውሉን ቃል በተመለከተ በመካድ በግልጽ ባልተከራከረበት ሁኔታ ውሉ በሁለት ምስክር ፊት የተደረገ አይደለም በሚል የሚቀርብ ክርክር የዋሱን ግዴታ ተፈፀሚነት የሚያስቀር ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1727(2) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.83,235 Download Cassation Decision

 • 80005 public service/ civil procedure/ jurisdiction/ source of funding

  በአዋጅ ቁ. 515/1999 መሠረት የተቋቋመና የሚተዳደር የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤት ሠራተኞች የሚያቀርቡትን ክርክር በተመለከተ ተቋሙ በራሱ ገቢ የሚተዳደር በመሆኑ ምክንያት አዋጅ ቁ. 377/96 ን መሠረት በማድረግ ጉዳዩን የመደበኛ ፍ/ቤቶች ለማየት ስልጣን አላቸው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አዋጁ ቁ. 515/99 አዋጅ ቁ. 553/99 አንቀጽ 6(1), 14(2)(ለ) አዋጅ ቁ. 545/99 Download Cassation Decision

 • 80079 labor law dispute/contract of employment/ pension/ collective agreement/

  የጡረታ መውጫ እድሜ ወሰንን በተመለከተ አሰሪው ከሠራተኛ ማህበር ጋር የሚያደርገው ስምምነት ተፈፃሚ ሊሆን የሚገባው በተመሣሣይ ጉዳይ ለሠራተኛ በህግ ከተደነገገው ይልቅ የህብረት ስምምነቱ የተሻለ (የበለጠ) ጥቅም የሚያስገኝ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 134(2),24(3) አዋጅ ቁ. 715/2003 አንቀጽ 17(1 Download Cassation Decision

 • 80296 criminal law/ custom law/ foreign currency/ ignorance of the law

  የውጭ ምንዛሬ ከአገር ውስጥ ወደ ውጭ አገር ያለህጋዊ እውቅናና ፈቃድ ማስወጣት የወንጀል ኃላፊነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ፣  የወንጀል ድርጊትን የፈፀምኩት ባለማወቅ ነው በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይነት የሌለውና ህግን አለማወቅ ይቅርታ የማያሰጥ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 99 አዋጅ ቁ. 591/2000 አንቀጽ 20(3) የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 22(1) የወንጀል ህግ አንቀጽ 2(2),25,23(2),81(1)(3) Download Cassation Decision

 • 80350 labor law dispute/ period of contract of employment/ permanent position

  ከሥራ ቅጥር ግንኙነት ጋር በተገናኘ አንድ ሥራ ""ቀጣይነት ያለው"" ነው ለማለት ስለሚቻልበት አግባብ፣  አንድ ሥራ በባህሪው ""ቀጣይነት ያለው"" ነው ለማለት ስራው ረዘም ላለ ጊዜ መስራቱን ብቻ ሣይሆን የሥራው ባህሪ ከአሠሪው ድርጅት (ተቋም) አይነተኛ ሥራ ጋር የሚሄድና በመደበኛነት የሚከናወን መሆኑን ጭምር ማረጋገጥ የሚያስፈልግ ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 80464 contract law/ administrative contract/

  አንድ ውል የአስተዳዳር ውል ነው ለማለት በህግ ወይም በተዋዋይ ወገኖች ግልጽ በሆነ ቃል የአስተዳደር መ/ቤት ውል ነው የተባለ እንደሆነ ወይም ደግሞ ተዋዋዮቹ ውል ያደረጉበት ጉዳይ ከህዝብ አገልግሎት ሥራ ጋር ተያያዥና ለሥራ ውሉ አፈፃፀም የአስተዳዳር አካልን (ፍ/ቤትን) ተካፋይነት ያለማቋረጥ የሚጠይቅ መሆኑን እንዲሁም በአጠቃላይ የውሉን አይነትና ባህሪ፣ የውለታውን አይነተኛ ጉዳይ ብሎም የተዋዋዮችን ማንነት መመልከት የሚያስፈልግ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.3132 አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 41(1)(መ) Download Cassation Decision

 • 80599 commercial law/ business organization/ article of association/ rent

  አንድ የንግድ ማህበር (ድርጅት) የሚጨበጥና የማይጨበጥ እንዲሁም የሚንቀሣቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት መብቶች ምን ምን እንደሆኑ በማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ የሚወሰን ስለመሆኑ  አንድ የንግድ ማህበር (ድርጅት) ሥራውን የሚያከናውንበት የንግድ ቦታ ኪራይ መብት የማህበሩ ህልውና ጋር የሚያያዝ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  የንግድ ድርጅቱ የፈረሰ ቢሆንም የንግድ ሥራውን ሲያከናውንበት የነበረውን ቦታ በሌላ ጉዳይ በፍርድ እንዲለቅ በተወሰነ ጊዜ የማህበሩ ሒሳብ ተጣርቶ አለመጠናቀቅ ቦታውን ላለማስለቀቅ ምክንያት ሊሆን የማይችል ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 80642 contract law/ novation/ maritime law/ contract of carriage/ period of limitation

  በአንድ ውል የተመለከተን እዳ ለማረጋገጥ ሲባል አዲስ ሰነድ በተዋዋይ ወገኖች የማደራጀት ተግባር የውል መተካት አድራጐት ነው ለማለት የሚቻለው በሁለተኛው ውል በግልጽ የተመለከተ እንደሆነ ስለመሆኑ፣  በባህር ላይ የሚደረግ የማጓጓዣ ውልን አስመልክቶ አጓዡ ለውሉ ምክንያት የሆነው እቃ (ንብረት) ጋር በተያያዘ የሚያቀርበው አቤቱታ ዕቃውን ከተረከበበት ቀን አንስቶ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በስተቀር በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ፣ የባህር ህግ ቁ.146,203 የፍ/ብ/ህ/ቁ.1826,1828,1829(ሀ) Download Cassation Decision

 • 80722 contract law/ arbitration/ civil procedure/ jurisdiction

  ተዋዋይ የሆኑ ወገኖች በመካከላቸው የሚነሣን አለመግባባት (ክርክር) በግልግል ዳኝነት እንዲያይ በሚል በውሉ የተሰየመ አካል በከሰመ ጊዜ ተዋዋዮች በጋራ ስምምነት ጉዳያቸውን በግልግል ዳኝነት የሚያይ አዲስ አካል ለመሰየም ከሚችሉ በቀር አስቀድሞ የተሰየመው አካል በመክሰሙ ምክንያት ፍ/ቤት ጉዳዩን በግልግል ለማየት የሚችል አካል ለመሰየም ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.3336(1),3328(2),3337,3331,3325-3344,3329 Download Cassation Decision

 • 80723 civil procedure/ joinder of defendants/ period of limitation/ basis of liability/ joint and several liability

  አንድ መዝገብ ላይ የተከሰሱ ሰዎች የኃላፊነት ምንጩ ከተለያየ የህግ ማዕቀፍ (ክፍል) በሆነ ጊዜ አንደኛው ወገን የተነሣው የይርጋ ክርክር በሌላኛው ወገን እንደተነሣ የማይቆጠር ስለመሆኑ፣  በአንድ ክስ (መዝገብ) ተጣምረው በአንድነት እና በነጠላ ኃላፊነት አለባችሁ ተብለው ከተከሰሱ ወገኖች መካከል አንደኛው ወገን የሚያነሣው የይርጋ መቃወሚያ ያለቅድመ ሁኔታ በሌላኛው ተጣምሮ የተከሰሰው ወገን ላይ ተፈፃሚነት አለው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  በፍ/ብሔር ጉዳይ የአንድነትና የነጣላ ኃላፊነት ከተለያዩ የህግ ክፍሎች እና ከተለያዩ ምክንያቶች ሊመነጭ የሚችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1852 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.244(3),36 Download Cassation Decision

 • 80964 Civil procedure/ jurisidiction/ pension/ age of pensioner/ appeal/ error of law

  ከጡረታ መብት አበል ተጠቃሚነት ጋር በተገናኘ የእድሜ አቆጣጠርና ውጤቱን በተመለከተ የሚቀርብ አቤቱታን አይቶ ለመወሰን ስልጣን ያለው የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ተቋም ስለመሆኑና በውሣኔው ቅሬታ ያለው ወገን ለኤጀንሲው ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የይግባኝ አቤቱታ ለማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ፣  በኤጀንሲው ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሚሰጥ ውሣኔ በፍሬ ነገር ደረጃ የመጨረሻ ስለመሆኑና በውሣኔው ላይ መሠረታዊ የህግ ስህተት አለው በማለት አቤቱታ ያለው ሠራተኛ ቅሬታውን ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 714/2003 አንቀጽ 4(1),54(3),56(4) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 343, 9, 231 Download Cassation Decision

 • 81081 property law/ unlawful enrichment/ undue expenses/ good faith

  አንድ ሰው የሌላ ሰው ንብረት ይዞ ሲጠቀም ከቆየና ንብረቱን በሚጠቀምበት ጊዜ ንብረቱን ከጥፋት ወይም ከብልሽት ለማዳን ሲል ተገቢውን ወጪ ያወጣ እንደሆነ ይኸው ወጪ በህጋዊ ባለሀብቱ እንዲተካለት ለመጠየቅ የሚችለው ወጪው የግድ አስፈላጊ ከሆነና በቅን ልቦና የተደረገ መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለመሆኑ፣  ወጪው በክፉ ልቦና የተደረገ ስለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ግን እቃውን (ንብረቱን) እንዲመልሰ የተደረገው ሰው እንዲተካለት የጠየቀውን ወጪ መጠን ዳኞች ሊቀንሱት ወይም ጭራሹንም ሊያስቀሩት የሚችሉ ስለመሆኑ፣  በንብረቱ (እቃው) ላይ የተደረገው ወጪ «በክፉ ልቦና የተደረገ ነው» የሚባለው ወጪው በተደረገበት ጊዜ (ወቅት) ወጪው እንዲተካለት የሚጠይቀው ሰው ንብረቱን (እቃውን) ለባለቤቱ ለመመለስ ግዴታ ያለበት መሆኑን ያወቅ እንደነበር ወይም ማወቅ ይገባው የነበረና ርትዕም ሲያስገድድ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2172(1),2171(1),2168,2169 Download Cassation Decision

 • 81215 banking law/ foreclosure/ pledge/ custom duty law/ confisication/ priority of creditors

  በባንክ በመያዣነት የተያዘ ተሽከርካሪ በሌላ በኩል የጉምሩክ ደንብ በመተላለፍ ወንጀል ባለቤቱ ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦበት ተሽከርካሪውም በመንግስት እንዲወረስ ውሣኔ የተሰጠበት እንደሆነ በህግ ፊት ቅድሚያ ተሰጥቶት ሊፈፀም ስለሚገባው ጉዳይ  በባንክ በመያዣነት የተያዘ ተሽከርካሪ ከመያዣው በኋላ በኮንትሮባንድ ወንጀል ምክንያት ለመንግስት ውርስ እንዲሆን በፍ/ቤት የመጨረሻ ፍርድ ባረፈበት ጊዜ ባለመያዣው በተሽከርካሪው ላይ ያለው የቀዳሚነት መብት እንዲሁም የውርስ ትዕዛዙ (ውሣኔው) ተፈፃሚ ሊደረጉ ስለሚችልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2828, 2857(1), 3059 አዋጅ ቁ. 97/90 አንቀጽ 3 የወንጀል ህግ አንቀጽ 98(1) Download Cassation Decision

 • 81405 labor law dispute/ independent contractor/ advocate

  የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ያለው የህግ ባለሙያ በሙያው አገልግሎት ለመስጠት ከ3ኛ ወገን ጋር በሚያደርገው ውል የሚፈጠረው ግንኙነት በእውቀት ሥራ ውል ላይ የተመሠረተ እንጂ ሠራተኛውን እንደ የስራ መሪ ወይም ተቀጣሪ የማያስቆጥረው ስለመሆኑ፡ በአዋጅ ቁ.377/96 የማይገዛ ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 81406 contract of sale/ transfer of ownership/vehicles/ property law/evidence law/ burden of proof/

  የመኪና ሽያጭ ውል መደረጉን (መኖሩን) ለማስረዳት ሊቀርብ ስለሚገባው የማስረጃ አይነት፣  የመኪና /ተሽከርካሪ/ ባለሀብትነት (ስመ ሀብት) እንዲተላለፍለት የሚጠይቅ ሰው ሊያቀርባቸው ስለሚገቡና ተቀባይነት ስላላቸው ማስረጃዎች አንድ ግዴታ እንዲፈፀምለት የሚጠይቅ ሰው የግዴታውን መኖር የማስረዳት ሸክም ያለበት ስለመሆኑ፣  አከራካሪ ሆኖ የቀረበን አንድ ፍሬ ነገር ማስረዳት ስለሚቻልበት የማስረጃ አይነት አግባብነት ባለው ህግ በተለይ የተቀመጠ ግለጽ ድንጋጌ እስከሌለ ድረስ ማናቸውንም ዓይነት ማስረጃ አቅርቦ ጉዳዩን ለማስረዳት ስለመቻሉ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1186(1),(2),2001(1) ስለ ተሽከርካሪ መለያ መመርመሪያና መመዝገቢያ አዋጅ ቁ.681/2002 አንቀጽ 6(3)(4) Download Cassation Decision

 • 81616 civil procedure/ execution of judgment/ injunction

  ከፍርድ አፈፃፀም ጋር በተገናኘ በአንድ በቀረበ የዋና ጉዳይ ክርክር ሒደት የእግድ ትዕዛዝ የተሰጠበት ንብረት በተመሳሳይ ተከራካሪ ወገኖች ጥያቄ በአፈፃፀም ደረጃ በተጠቃሹ ንብረት ላይ አፈፃፀም እንዲቀጥል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣  ቀደም ሲል በዋና ጉዳይ ክርክር በፍ/ቤት ትእዛዝ እንዲታገድ የተደረገ መሆኑ የታወቀ ንብረት ላይ በድጋሚ በተመሳሳይ ንብረት ላይ መብትን ለማስከበር በሚል በሌላ ጊዜ በአፈፃፀም ደረጃ የሚቀርብ ጥያቄ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 81857 contract law/ loan/ interest/ non performance/ damage

  በብድር የሚሰጥ ገንዘብ ላይ ተዋዋይ ወገኖች ሊያቋቁሙት ስለሚችሉት የወለድ ምጣኔ (መጠን)፣  የውል ግዴታውን ያልፈፀመ ወይም ያዘገየ ወገን ለሌላኛው ተዋዋይ ስለሚከፍለው የኪሣራ መጠን፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1803(2),1790(2),1800,2479(3),2488,2489 Download Cassation Decision

 • 81963 public service/ civil procedure/ jurisdiction/ temporary civil servants

  የፌዴራል መንግስት ጊዜያዊ (የኮንትራት) ሠራተኞች ቅጥር ጋር በተገናኘ በሠራተኛ እና በቀጣሪው መካከል የሚነሱ ክርክሮችን በተመለከተ የመደበኛ ፍ/ቤቶች ጉዳዩን በቀጥታ ክስም ሆነ በይግባኝ ለማስተናገድ ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.515/99 አንቀጽ 22(3) ,2(1) የፌዴራል መንግስት ጊዜያዊ የኮንትራት ሰራተኞች ቅጥር አፈፃፀም መመሪያ Download Cassation Decision

 • 82335 labor law dispute/ termination of contract of employment/ poor performance of worker

  አንድ ሠራተኛ በሥራው አፈፃፀም ምዘና ደካማ ነው በማለት የሥራ ውሉን ለማቋረጥ የሚቻለው ምዘናውን ሠራተኛው በተቀጠረበትና በተመደበበት የሥራ አይነት (መስክ) ላይ በማድረግ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 42, 43(1) Download Cassation Decision

 • 82336 labor law dispute/ industrial peace/ litigation

  አንድ ሠራተኛ መብቱን ለማስከበር በአሰሪው ላይ በፍ/ቤት ክስ መመስረቱ ብቻ ከአሠሪው ጋር ለወደፊት የሻከረ ግንኙነት ይፈጥራል የማያስብልና የስራ ውሉ እንዳይቀጥል ለማድረግ የሚያስችል ምክንያት ስላለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 43(3) Download Cassation Decision

 • 82427 civil procedure/ non appearance of parties/ default judgment/cooperative societies/ removal of chairperson

  አንድ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ ብይን መስጠቱ ፍርዱ ለከሣሽ በሚጠቅም መልኩ (መንገድ) የመወሰኑን ሁኔታ በአስገዳጅነት የሚያስከትል ነው ለማለት የማይችል ስለመሆኑ፣  የማህበር ሊቀመንበርን ከስልጣን ለማንሳት ስለሚቻልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 70(ሀ) Download Cassation Decision

 • 82572 Criminal law/ sentencing/ sentencing guideline/ mitigation

  በወንጀል ጉዳይ ተከስሶ ጥፋተኛ የተባለ ሰው ላይ የሚወሰነው ቅጣት በቅጣት አወሣሠን መመሪያው የተሸፈነ እንደሆነ ቅጣቱ በመመሪያው አግባብ ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ፣  በወ/ህ/አ 539(1)(ሀ) ድንጋጌ ክስ ቀርቦበት ጥፋተኛ የተባለ ሰው ለእያንዳንዱ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ሶስት እርከን ሊቀነስለት የሚገባ ስለመሆኑ፣ የወ/ህ/አ. 539(1)(ሀ) የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የቅጣት አወሣሠን መመሪያ ቁ.1/2002 አንቀጽ 16(7) Download Cassation Decision

 • 83012 labor law dispute/ unlawful termination of contract of employment/ reinstatement/ back pay

  የሥራ ክርክር ችሎት አንድን ሠራተኛ ያለአግባብ የተሰናበተ ነው በሚል ውሣኔ ከተሰጠበት ቀን ወደኋላ ቀደም ብሎ ካለ ጊዜ ጀምሮ አሰሪው ወደ ሥራ እንዲመልስ በሚል ውሣኔ የሰጠ እንደሆነ ሠራተኛው ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ ውዝፍ ደመወዝ ለማግኘት መብት የሚኖረው ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 83068 labor law dispute/ contract of employment/ transfer to sister company/

  የሥራ ውል ወይም በሌላ ሠነድ ሠራተኛው ስምምነቱን ባልሰጠበት ሁኔታ አሰሪ የሆነው አካል እህት ድርጅት ወደ ሆነ ተቋም (ድርጅት) ሰራተኛውን አዛውሮ ለማሰራት አሠሪ መብት የሌለው ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 83425 civil procedure/ jurisdiction/ private pension/ cassation/ constitution

  የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ መብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የሚቀርብ ክርክርን ለማየት ስልጣን ያለው አካል የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ስለመሆኑ፣  የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በህግ የዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው አካላት የቀረበላቸውን ጉዳይ በህጉ አግባብ ያስተናገዱና ውሣኔ የሰጡ መሆኑን የማረጋገጥና የመቆጣጣር ኃላፊነትና ስልጣን ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.9,231 አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 10(22) አዋጅ ቁ. 454/97 አንቀጽ 2(1) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 142, 147 አዋጅ ቁ. 345/95 አዋጅ ቁ. 209/55 አዋጅ ቁ. 715/2003 Download Cassation Decision

 • 83448 contract law/ government houses/ rent/ directive

  በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የመንግስት ቤቶች ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ከወጣው መመሪያ ቁ.3/2004 አፈፃፀምጋር በተገናኘ የንግድ ቤቱን በማከራየት ከሚያገኙት ገቢ ውጪ ሌላ ገቢ የሌለውና በእድሜ አዛውንት የሆነ ተከራይ የኪራይ ውል ሊቋረጥ የማይገባ ስለመሆኑ፣ መመሪያ ቁ.3/2004 አንቀጽ 6(1) Download Cassation Decision

 • 83701 civil procedure/ cost of litigation/ procedure of cost of litigation

  የወጪና ኪሣራ ክፍያ ጉዳይ ሊስተናገድ ሊወሰን የሚገባው በዋናው ጉዳይ ፍርድ (ውሣኔ) በተሰጠበት መዝገብ ስለመሆኑ፣  ወጪና ኪሣራ ክፍያን በተመለከተ ማን መክፈል እንዳለበት በዋናው ጉዳይ ላይ ተለይቶ ከተወሰነ በኋላ ምን ያህል መከፈል እንዳለበት በተመለከተ ደግሞ ዋናው ፍርድ ባረፈበት መዝገብ የወጪና ኪሣራ ዝርዝር ቀርቦ ሌላኛው ተከራካሪ ወገን ስለቀረበው የወጪና ኪሣራ አስፈላጊነት ስለመጠኑ እና በእርግጥም ወጪና ኪሣራ ስለመውጣቱ በተመለከተ የበኩሉን ክርክር ካቀረበ በኋላ የወጪና ኪሣራ ልኩ ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 183, 378, 462-464 Download Cassation Decision

 • 84353 civil procedure/ contract law/ loan /banking/public auction/cassation/ mortgage/ bankrupcy/

  ለተሰጠ የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣ የተያዘ በኪሣራ የፈረሰ ማህበር (ድርጅት) ንብረት በሀራጁ ጨረታ የተሸጠ በመሆኑ ሽያጩ ሊፈርስ ይገባል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ እና ፍ/ቤቶችም ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ፣  በመያዣ የተያዘውን ንብረት በባንኩ በሀራጅ የተሸጠ በመሆኑ በባለዕዳው በኩል ቢሸጥ የተሻለ ዋጋ ያስገኝ ስለነበረ ሽያጩ ሊፈርስ ይገባል በማለት የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣  በህግ የተቋቋመ ባንክ በብድር የሰጠው ገንዘብ በአዋጅ ቁ.97/90 እና 216/92 መሠረት አስቀድሞ ለብድሩ አመላለስ ዋስትና ይሆን ዘንድ ከያዛቸው መያዣዎች መካከል አንዱን በመምረጥ በሐራጅ ሊሸጥ ይገባል፣ ለመሸጥ የተንቀሳቀሰበትን የመያዣ ንብረት ከመሸጥ ድርጊት ይታቀብ ይህም በፍ/ቤት ትዕዛዝ ይሰጥልን በሚል የሚቀርብ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑና በአሻሻጡ ሂደት ባንኩ ህግን ባለመከተል የፈፀመው ስህተት ቢኖርና በባለዕዳው ላይ ጉዳት ቢደርስ ግን ለዚህ ጉዳት ባንኩ ለባለዕዳው ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርበት ስለመሆኑ እና ፍ/ቤቶችም ሀራጁን ለማስቆም ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ፣  የሰበር ችሎት የሚሰጠው አስገዳጅነት ያለው የህግ ትርጉም አንድ ክርክር የቀረበበት ጉዳይ (ድርጊት) ከተፈፀመ በኋላ ስለሆነ የተሰጠው የህግ ትርጉም በጉዳዩ ላይ ተፈፀሚነት የለውም በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 394-449,224 አዋጅ ቁ.97/90 አንቀጽ 3,4 አዋጅ ቁ.216/92 አዋጅ ቁ.98/90 አዋጅ ቁ.2584 Download Cassation Decision