volume 15

volume 15

 • 89276 criminal law/ breach of trust/ loan

  አንድ ሠው የአንድን ጉዳይ መከሰት በምክንያትነት በመግለጽ ከሌላ ሰው ገንዘብን ተበድሮ መውሰድ ተከስቷል የተባለው ጉዳይ ካለመከሰት ጋር በተገናኘ ተበዳሪው በእምነት ማጉደል ወንጀል ሊያስጠይቀው የሚችል ስላለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 675 Download Cassation Decision

 • 42501 civil procedure/cause of action/ law of property/ ownership/ title deed/ res judicata

  የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም ክስ ጋር በተያያዘ ክርክር ቀርቦ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በክርክሩ ተሣታፊ የነበረ ወገን ንብረቱን አስመልክቶ ተሰጥቶ የነበረው የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መክኗል በሚል የሚያቀርበው አዲስ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑና በፍርዱ መሠረት የተጀመረው አፈፃፀም ሂደትን ለማስቆም የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1195,1196 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6,358,378 የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 78(1), 79(1)(4) , 37 Download Cassation Decision

 • 72980 civil procedure/ power of court/ appeal

  ፍርድ ቤቶች ለቀረበላቸው ጉዳይ አወሣሠን የጠራ ፍሬ ነገር የሌለ መሆኑን የተገነዘቡ ከሆነ ይሄው ፍሬ ነገር እንዲጣራ ተገቢ ነው ያሉትን ማጣራት ሁሉ ለማድረግ ስለመቻላቸው፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 136, 137, 272, 327(3), 345 Download Cassation Decision

 • 75877 civil societies/ solicitation of foreign fund/

  አንድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም ማህበር ከውጭ ምንጭ በህጉ ከተመለከው የገንዘብ መጠን በላይ እንዲሰበሰብ ሊፈቅድ የማይችል ስለመሆኑ፡- አዋጅ ቁ. 621/2001 አንቀጽ2/2/፣3/4/፣14/5/፣14/2/፣6፣90፣111/2/፣112፣108፣110 ደንብ ቁጥር 168/2002 አንቀጽ 18/3/፣10/2/፣36 Download Cassation Decision

 • 77983 civil procedure/ evidence law/ relevant evidence/

  በፍ/ብሔር ክርክር ማስረጃ የሚሰማውና ፍሬ ነገሩ እንዲነጠር የሚደረገውም በማስረጃ የሚነጥረው ፍሬ ነገር ለዳኝነት አሰጣጡ እጅጉን አስፈላጊና የግድ ሆኖ ሲገኝ ስለመሆኑ፣  ማስረጃ እንዲሠማ የሚፈልግ ወገን ማስረጃው የሚሰማበትን ነጥብ ለይቶ የማስረጃውን አይነትና የሚገኝበትን ቦታ ሁሉ በመጥቀስና በእጁ ላይ ያለውንም አያይዞ ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.223¸234¸137(3)¸145¸256,136-138,246,248 Download Cassation Decision

 • 78180 Insurance/ formation of contract

  የመድን ዋስትና ሽፋን ውል ተደርጓል እንዲሁም ውሉ ተሻሽሏል ለማለት ስለሚቻልበት አግባብ፣ የንግድ ህግ፡ 657 Download Cassation Decision

 • 78206 civil procedure/ execution of judgment/ foreign judgment

  በውጭ አገር የተሰጠን ፍርድ በኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ለማስፈፀም ስለሚቻልበት አግባብ፣  በውጭ አገር የተሰጠ ፍርድን በኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ከማስፈፀም ጋር በተያያዘ በአፈፃፀም ሂደቱ ክርክር በተነሣ ግዜ የፍርድ አፈፃፀሙን በያዘው ፍ/ቤት ክርክሩ ታይቶ ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 458-460 Download Cassation Decision

 • 78470 criminal law/ extracontractual liability/ effect of civil liability on criminal liability

  አንድ ሠው በፍ/ብሔር ጉዳይ ተከስሶ ኃላፊነት የለበትም ተብሎ የመጨረሻ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በተመሳሳይ ማስረጃ በወንጀል ጉዳይ ተከስሶ ተጠያቂ ነው (ኃላፊነት አለበት) ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ ስላለመኖሩ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2149 የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 141 Download Cassation Decision

 • 79189 tax law/ capital gain tax/ transfer of ownership title

  ግብር የተጣለበትን የካፒታል ንብረት ዝውውር የመቀበል ወይም የመመዝገብ ወይም በማናቸውም መንገድ የማጽደቅ ስልጣን ያለው (የተሰጠው) የመንግስት አካል ግብሩ መከፈሉን ሣያረጋግጥ ዝውውሩን እንዲቀበል፣ እንዲመዘግብ ወይም እንዲያፀድቅ ሊገደድ የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 37(7) Download Cassation Decision

 • 79389 criminal law/ period of limitation/

  በሌላ ሰው ጥቅም የሥራ አመራር ላይ ወንጀል ተፈጽሟል ለማለት ስለሚቻልበት አግባብ፣  በተከታታይ ለተፈፀመ ወንጀል ይርጋ ስለሚቆጠርበት አገባብ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/፣702/3/፣219/2/ Download Cassation Decision

 • 79476 labor dispute/ salary/ part time/ calculation of period of limitation

  ከሥራ ጋር በተገናኘ እንዲከፈል በሚል የሚቀርቡ የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓት እና ሌሎች ክፍያዎች ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ሠራተኛው ክፍያዎቹን መጠየቅ ይችላል (ይገባዋል) ከሚባልበት ግዜ ጀምሮ እንጂ የሠራተኛው የሥራ ውል ከተቋረጠበት ግዜ ጀምሮ ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 162(1-4) Download Cassation Decision

 • 79561 commerical law/ lease of business/ sub lease

   የንግድ መደብር ኪራይ ከንግድ ቤት ኪራይ የተለየ ስለመሆኑ፣  የንግድ መደብር የተከራየ ሰው ያለአከራዩ እውቅና እና ፈቃድ መደብሩን ለ3ኛ ወገን በኪራይ አሳልፎ ለመስጠት ስለመቻሉ፣ የንግድ ህግ ቁ. 127 (ሐ),145(ለ), Download Cassation Decision

 • 79794 contract law/ non performance of contract/ damage assessment/

   ከውል አፈፃፀም ሂደት ጋር በተገናኘ በተዋዋይ ወገኖች ላይ ለሚደርስ ጉዳት ኪሣራ ሊሰላ ስለሚችልበት አግባብ፣  የኪሣራው ልክ ከውል ውጪ የሚደርስ ኃላፊነትን መሠረት በማድረግ በርትዕ ሊወሰን ስለሚችልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1790, 1800, 2102(1)(2) Download Cassation Decision

 • 79871 civil procedure/ interested party/ opposition/ law of succession/ certificate of inheritance

  ወራሽነትን በማረጋገጥ በተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ ላይ መብቴን ወይም ጥቅሜን ይነካል በሚል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የሚቀርብ የመቃወሚያ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ሥለመሆኑ እና ተረጋግጦ የተሰጠውን ማስረጃ በሌላ ክርክር መቃወም የሚችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 Download Cassation Decision

 • 80119 criminal law/ usury/ interest rate

  አንድ ሠው የአራጣ ወንጀል ድርጊት ፈጽሟል በሚል በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን ስለሚችልበት አግባብ፣  በወር 10% ወለድ ታስቦ እንዲከፈል በመስማማት ገንዘብ ማበደር በአራጣ የወንጀል ድርጊት የሚያስጠይቅ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ 667(1) Download Cassation Decision

 • 80202 civil procedure/ constitution/ right to access to justice/ justiceable matter

  አንድን ጉዳይ አስመልክቶ በፍርድ ሊወሰን የሚገባው እስከሆነና ጉዳዩን ለማየት በህግ በግልጽ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው ሌላ አካል እስከሌለ ድረስ ጉዳዩ በቀጥታ በፍ/ቤት ቀርቦ ሊስተናገድና ውሣኔ ሊሰጥበት የሚችልና የሚገባ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37(1), 79(1) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 4 Download Cassation Decision

 • 80241 property law/ possessory action/ contract of rent

  የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ የሚቻለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻ በሆነው ነገር በቀጥታ ወይም በጥበቃ ሥር የሆነ ይዞታ ሲኖረው ስለመሆኑ፣  የይዞታ ክስ የሚቀርበው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት በወቅቱ ለመያዝ ምንም አይነት መብት በሌለው ሰው ላይ ስለመሆኑ፣  የሁከት ይወገድልኝ ክስ የሚያቀርብ ሰው ንብረቱ በይዞታው ሥር የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚዉ የኃይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጥር ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን ማስረዳት ያለበት ስለመሆኑ፣ የሁከት ተግባር ተፈጥሯል ለማለት ባለይዞታ የሆነው ሰው በይዞታው ሥር በሚገኘው ንብረት እንዳይገለገልበት ሌላ ሰው ጣልቃ ገብቶበት መሰናክል ወይም ረብሻ የፈጠረበት ስለመሆኑ መረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ፣  በህግ አግባብ በተደረገ የኪራይ ውል መነሻነት ይዞታን በእጁ ያደረገ ሰው (ተከራይ) ላይ አከራይ የሚያቀርበው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 80301 public service/ arbitration/ crimial liability

  አንድ የመንግስት ሠራተኛ መ/ቤቱን በመወከል ተቋሙ ከ3ኛ ወገን ጋር ካለው አለመግባባት ጋር በተገናኘ በግልግል ዳኝነት ጉባኤ አባልነት በዳኝነት ተሰይሞ ለጉባኤው የሚከፈለውን አበል ክፍያ መወሰኑ የዲሲፕሊን ጥፋት ፈጽሟል ሊያስብለው የሚችል ስላለመሆኑ፣  በግልግል ዳኝነት ጉባኤ ዳኝነት የተሰየመ ዳኛ በህግ ስላለበት ኃላፊነት፣  የግልግል ዳኛ ሆኖ የተሰየመ ሰው በግልግል ዳኝነቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ካልተወጣ በወንጀል ተጠያቂነት የሚኖርበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 351(2)(መ), 317, 318(መ) የወንጀል ህግ አንቀጽ 399 የአ.አ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዋጅ ቁ. 6/2000 አንቀጽ 31 Download Cassation Decision

 • 80343 labor dispute/ occupational accident/ extra contractual liability/ civil procedure/ res judicata

   አንድ ሠራተኛ በሥራ ላይ እያለ የደረሰበትን የአካል ጉዳት በተመለከተ የጉዳት ካሣ ክፍያ እንዲከፈለው ለመጠየቅ የሚችለው በአማራጭ አንድም በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጁ መሠረት አሰሪውን ያለጥፋት በሥራ ክርክር ችሎት ከሶ በመጠየቅ ወይም የአሰሪውን ጥፋት መነሻ በማድረግ የጉዳት ካሣ ክፍያ ከውል ውጪ ኃላፊነትን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ በፍ/ሔር ችሎት በአሠሪው ላይ ክስ ለማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ፣  በሥራ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሠራተኛ የጉዳት ካሣን ለመጠየቅ በህጉ የተመለከቱትን መብቶች በአግባቡና በትክክል ተገንዝቦ እንደ ጉዳቱ ሁኔታ፣ አይነትና አግባብነት በተሻለ ሁኔታ የሚጠቅመውን የመብት አድማስ አውቆ በመለየት ተገቢው መብቱ ከመነጨበት የህግ አግባብ አንፃር ክሱን ሊያቀርብ የሚገባ ስለመሆኑ፣  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.5 ድንጋጌ ይዘት አድማሱ በግልጽ በተወሰኑ ጭብጦች ላይ ብቻ ሣይሆን በተከራካሪ ወገኖች ቢነሱ ኖሮ ሊወሰኑ ይችሉ የነበሩ ጭብጦችን ጭምር የሚያካትት ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 80920 succession law/ donation/ will/ collation

  ከሟች በስጦታ ወይም በኑዛዜ የተሰጠን ንብረት ወደ ውርስ መልሶ ማግባት (Collation) ስለሚከናወንበት ሥርዓት፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1065-1078 Download Cassation Decision

 • 81023 property law/ administrative law/ title deed

  የመሬት አስተዳዳር ጽ/ቤት ቀድሞ የተሰጠን የቤትና ቦታ ካርታና ፕላን ጠፍቷል በሚል ሲጠየቅ በምትኩ ሌላ ሊሠጥ የሚገባው በ3ኛ ወገኖች ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለማስወገድ በቅድሚያ ጠያቂው በቂ ዋስትና እንዲሰጥ በማድረግ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1197(2) Download Cassation Decision

 • 81163 contract law/ rent/ renewal of contract of rent

  አስቀድሞ በተደረገ የኪራይ ውል መነሻነት አንድን የአከራይ ንብረት ይዞ ሲጠቀም የቆየ ተከራይ የኪራይ ውል ግዜው ካለቀበት ጊዜ ጀምሮ አከራዩ የኪራዩን ዋጋ በመጨመር አዲስ የኪራይ ዋጋ እንዲከፈል ገልፆ እያለ ተከራዩ በቀረበው አዲስ የኪራይ ዋጋ ሳይስማማ ወይም እየተቃወመ በንብረቱ መገልገሉን በቀጠለ ጊዜ ተከራይ ለአከራዩ ሊከፍለው የሚገባውን የኪራይ ዋጋ ለመወሰን የሚቻልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2950(1) (2), 1687 Download Cassation Decision

 • 81178 criminal law/ criminal procedure/ charge/ criminal act/ elements of crime/

  የአንድ ደርጊት ወይም ግድፈት ወንጀልነት በህግ በግልጽ ተደንግጐ በማይገኝበት ሁኔታ የድርጊቱን ወይም የግድፈቱን ፈፃሚ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የማይቻል ስለመሆኑ፣  በወንጀል ጉዳይ የሚቀርብ ክስ ስለ ድርጊቱና አፈፃፀሙ የሚሰጠው መግለጫ ድርጊቱን ወንጀል ከሚያደርገው ህግ አነጋገር በጣም የተቀራረበ መሆን የሚገባው ስለመሆኑ፣  በንግድ ሥራ ለተሰማሩ ወይም ሌሎች ሰዎች በግለሰብ ደረጃ መጠኑ በርካታ የሆነ ገንዘብን በተደጋጋሚ በብድር የመስጠት ተግባር በህግ የተከለከለ ወይም በወንጀል የሚያስቀጣ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 2, 23(2), 3, 61 የወ/መ/ህ/ሥሥ/ቁ. 112 አዋጅ ቁጥር 83/86 አንቀጽ 59(1), (ሸ), 2(ሀ), Download Cassation Decision

 • 81275 civil procedure/ consolidation of suits

  አንድን ጉዳይ በተመለከተ ተከራካሪ ወገኖች በየበኩላቸው በተለያዩ ፍ/ቤቶች (ችሎቶች) አንድ አይነት ወይም ተመሳሳይ የሆኑ ክሶች ባቀረቡ ግዜ (የክርክሮቹ ደረጃ ምንም ይሁን ምን) ክሶቹ ተጣምረው ታይተው ሊወሠኑ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 8(1),11,244, 245 Download Cassation Decision

 • 81814 labor dispute/ contract of employment

  የስራ ውል የሚመሠረተው ማንኛወም ሰው ደመወዝ እየተከፈለው በአሰሪው መሪነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለተወሰነ ወይም ላልተወሠነ ጊዜ ወይም የተወሰነ ሥራ ለአሰሪው ለመስራት የተስማማ እንደሆነ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 2(3), Download Cassation Decision

 • 81934 Civil procedure/ jurisdiction/ commerical law/ business registation/

  ከንግድ ምዝገባ ፈቃድ ጋር በተገናኘ የሚነሱ የፍሬ ነገር ክርክሮችን የመደበኛ ፍ/ቤቶች አይተው ለመወሰን ስልጣን የሌላቸው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 686/2002 አንቀጽ 61 Download Cassation Decision

 • 82061 tax law/ Value added tax (VAT)/ registration for VAT

  አንድ በንግድ ሥራ የተሰማራ ሰው (ድርጅት) በተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ከፋይነት የመመዝገብ ግዴታ አለበት ለማለት የሚቻልበት እንዲሁም መመዝገብ ሲኖርበት ሳይመዘገብ ቀርቶ ግብር ሊጣልበት ስለሚችልበት አግባብ፣ አዋጅ ቁ.285/94 አንቀጽ 3(1)(3), 16(1)(ለ) Download Cassation Decision

 • 82091 labor dispute/ termination of contract of employment/ absence from work/ duty to assign job

  አሠሪ ሠራተኛውን እንደ ሠራተኛ በመቀበል የሚሰራውን ሥራ ባልሰጠበት ሁኔታ ሠራተኛውን ከሥራ ገበታው ቀርቷል በሚል ያለ ማስጠንቀቂያ ለማሰናበት የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27(1) ለ Download Cassation Decision

 • 82154 extracontractual liability law/ vicarious liability/ vicarious liability of employer

  አንድ የመንግስት መ/ቤት በሠራተኛው ተግባር በኃላፊነት ሊጠየቅ የሚችለው በሠራተኛው የተፈፀመው ጥፋት የሥራ ጥፋት ሆኖ ሲገኝ ስለመሆኑ፣  አንድ ጥፋት የሥራ ጥፋት ነው ተብሎ የሚወሰደው ጥፋት አድራጊው በጥፋቱ ላይ የወደቀው በቅን ልቦና በስልጣኑ ለሥራው ክፍል መልካም ያደረገ መስሎት የፈፀመው መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑና ከዚህ ውጪ በሆነ ጉዳይ ግን ጥፋቱ እንደ ግል ጥፋት የሚቆጠር ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2126, 2127 (1)(2)(3) Download Cassation Decision

 • 82234 civil procedure/ law of property/ sale of immovables/ cause of action/ transfer of title of ownership

  የማይንቀሣቀስ ንብረት (ቤት) ሽያጭ ውል ጋር በተገናኘ ሻጭ በውሉ መሠረት የቤቱን ስመ-ንብረት የሚመለከተው አካል ወደ ገዢው ለማዞር እንዲችል በሚመለከተው ክፍል ቀርቦ ተገቢውን እንዲፈፀም በማለት ገዥ የሚያቀርበው ክስ የክስ ምክንያት የለውም ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 231(1)(ሀ), 33(2-3), 222, 224 Download Cassation Decision

 • 82503 commerical law/ private limited company/ dividend

  የንግድ ማህበር ሒሣብ ከተጣራና ትርፍና ኪሣራው ተለይቶ ከቀረበ በኋላ የማህበር አባል (ባለአክሲዮን) የሆነ ሰው ከትርፍ ሊደርሰው የሚገባውን የድርሻ ክፍያ በመለየት ክፍያ እንዲፈፀምልኝ በማለት የሚያቀርብው ጥያቄ ህጋዊ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ፣ የንግድ ህግ ቁጥር 211, 517, 518, 532(1) Download Cassation Decision

 • 82585 succession law/ will/ invalidation of will/ period of limitation

  ኑዛዜ ፈራሽ ነው በሚል ስለሚቀርብ ክስ እና ክሱ ሊቀርብ ስለሚገባበት የጊዜ ገደብ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 973, 974 Download Cassation Decision

 • 82670 contract law/ rent/ government owned houses/ renting to third party

  የንግድ ቤትን ከመንግስት የተከራየ ተከራይ ከአከራዩ እውቅና ውጭ ለ3ኛ ወገን የንግድ ቤቱን ማስተላለፉ አከራዩ የመጀመሪያውን የኪራይ ውል ለማቋረጥ የሚያስችለው ስለመሆኑ፣ በዚሁ መሠረትም አከራዩ ቤቱን ለማስለቀቅ የሚያያደርግው እንቅስቃሴ ሁከት ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣ መመሪያ ቁጥር 4/2004 አንቀጽ 6 የፍ/ብ/ህ/ቁ.1140, 1149 Download Cassation Decision

 • 82679 civil procedure/ declatory judgment/ family law/ marriage

  ሚስትነትን በተመለከተ የአመልካችን ማስረጃ ብቻ በመቀበል ሚስትነትን በማረጋገጥ በፍ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (Declaratory Judgment) በማናቸውም ጊዜ ተዓማኒነትና ክብደት የሌለው ማስረጃ መሆኑን ለማሳየት ክርክር ሊቀርብበትና ተቃራኒ ማስረጃ ተሰምቶ ውድቅ ሊደረግ የሚችል እንጂ ማስረጃውን በተሰጠው ፍ/ቤት ተቃውም በማቅረብ ያልተሻረ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 83007 law of succession/ contract law/ surety/ execution of judgment/ civil procedure

  ከውርስ ሀብት ክፍፍል ጥያቄ ጋር በተገናኘ መብቱን ለማስፈፀም ጠይቆ በአፈፃፀም በገባበት የዋስትና ግዴታ መሰረት ተጠያቂ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1827(1) Download Cassation Decision

 • 83060 property law/ sale of immovble property/ agency/ unauthorized agency

  የማይንቀሣቀስ ንብረት ሽያጭ ጋር በተገናኘ ንብረትነቱ ከአገር የወጡ ኤርትራዊያን የሆነ ቤትን ለማስተዳደር ውክልና የተሰጠው ሰው የመሸጥ ውክልና በባለቤቱ ያልተሰጠ ቢሆንም እንኳን በሚመለከተው የመንግስት አካል በተሰጠ (በተላለፈ) መመሪያ መሠረት ከተወካዩ ቤቱን የገዛ ገዥ ተወካዩ ቤቱን የሸጠለት በሌለው የውክልና ስልጣን ነው በሚል ገዝቶ ስመ ንብረቱ ከተላለፈለት በኋላ የሽያጭ ውሉ ፈርሶ ቤቱ ለባለቤቱ ሊመልስ ይገባል ለማለት የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 334/1995 አንቀጽ 2(1), 4(1), 5(1)(ሀ) Download Cassation Decision

 • 83169 civil procedure/ jurisdiction/ counter claim/ splitting of claim

  በአንድ ጉዳይ ተከሣሽ የሆነ ወገን የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ካቀረበ ፍ/ቤቱ ከቀረቡት ክሶች መካከል በሥረ-ነገር ስልጣኑ ሥር ያሉትን መርጦ ለማየትና ከሥረ-ነገር ስልጣኑ በላይ የሆነውን ጉዳይ ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ይቅረብ በማለት የከሣሽን ክስና የተከሣሽን የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ ተነጣጥለው እንዲታዩ በማድረግ የሚሰጠው ትዕዛዝ ተገቢ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 30(1)¸324(1) (ሀ),215(2)¸17(3) Download Cassation Decision

 • 83489 commerical law

  አበዳሪ የሆነ ባንክ ለተበዳሪው ላበደረው ገንዘብ በመያዣነት ለያዘው ንብረት የመድን ሽፋን የገባለት እና የአርቦን ክፍያን ለመክፈል የተስማማ እንደሆነ ለመድን አስገቢው ተቋም የአረቦን ክፍያውን ለመክፈል የሚገደድ ስለመሆኑ፣  የንግድ ህግ ቁጥር 657, 675 Download Cassation Decision

 • 83582 civil procedure/ compromise agreement/ opposition by third party

  በፍ/ቤት በመካሄድ ላይ ከነበረ ክርክር ጋር በተገናኘ በተከራካሪዎቹ ወገኖች አመልካችነት ጉዳይ በእርቅ በማለቁ የተከራካሪዎቹን የእርቅ ስምምነት ተቀብሎ በማጽደቅ እንዲመዘገብ በማለት በፍ/ቤት የተሰጠ ትእዛዝ ላይ መብቴ ወይም ጥቅሜ ተነክቷል የሚል ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የሚያቀርበው የመቃወሚያ አቤቱታ ህጋዊና ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ትእዛዙን የሠጠው ፍ/ቤት አቤቱታውን ተቀብሎ ሊያስተናግደው የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358,360,277(1)(2) Download Cassation Decision

 • 83665 property law/ law of succession/ liquidation of property/ ownership

  የውርስ ሀብትን እንዲያጣራ የተመደበ የውርስ ሀብት አጣሪ የንብረትነቱ የሟች የግል ሀብት መሆን በተመለከተ በሪፖርቱ ገልጿል በሚል ምክንያት ከንብረቱ ጋር በተገናኘ የባለሀብትነት ክርክር ያቀረበውን ወገን ጥያቄ በአግባቡ ባለማስተናገድ ውሣኔ ላይ መድረስ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መግስት አንቀጽ 40(1), 37 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 1206 Download Cassation Decision

 • 83674 contract law/ rent/ renewal of contract of rent

  አንድ ውል (ስምምነት) ህግ በጽሑፍ እንዲሆን ሲያስገድድ ውሉ በጽሁፍ መደረግ ያለበት እና በተዋዋይ ወገኖችና በሁለት ምስክሮች ፊርማ ሊረጋገጥ የሚገባ ስለመሆኑና መሀይማንና ማየት የተሳናቸው ሰዎች የሚያደርጉት ውል በአዋዋይ ወይም በዳኛ ፊት የተደረገ ካልሆነ በቀር በውሉ የማይገደዱ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1727, 1728(3), 2005 Download Cassation Decision

 • 83771 civil procedure/ injunction/ cash in bank/ interest

  በተከራካሪ ወገኖች ክርክር በሚካሄድበት ወቅት በፍ/ቤት ትእዛዝ በተከራካሪ ወገን ስም በባንክ የሚገኝ ገንዘብ ታግዶ እንዲቆይ ተደርጐ ትእዛዙ ፀንቶ በነበረበት ግዜ በገንዘቡ ላይ ወለድ ሊታሰብ ይገባል ወይስ አይገባም በሚል ክርክር የተነሣ እንደሆነ ከጉዳዩ ልዩ ባህሪ ጋር በተገናኘ ፍ/ቤቶች የልዩ አዋቂ ምስክርነትና የባለሙያ ማብራሪያን አስቀርበው በማጣራት ሊወሰኑ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 136 Download Cassation Decision

 • 83915 civil procedure/pleading/ statement of claim/ form of statement of claim/ power of court/

  የክስ አቀራረብ ሥርዓቱን አሟልቶ ያልቀረበ ክስን ፍ/ቤቶች ሌላኛውን ወገን ሳይጠሩ ለመዝጋት ስለመቻላቸው፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 33, 80, 222, 225, 226 እና 231 83915 አቶ ዩሐንስ በቀለ እና የቦንጋ ከተማ ማዘጋ Download Cassation Decision

 • 84330 contract law/ evidence law/ proof of contract/ parole rule of evidence

  አንድን በጽሁፍ የተደረገ ውል ዋና ሰነድ ጠፍቷል በማለት ክርክር በቀረበ ጊዜ ፍ/ቤት በማስረጃነት በቀረበው የውሉ ሰነድ ኮፒን ተቀብሎ በውሉ የተመለከቱትን ምስክሮች ሊሰማ የሚገባው ጠፍቷል የሚለው ወገን ዋናው ሰነድ ስለመጥፋቱ በተመለከተ በአግባቡ ያስረዳ እንደሆነና የውሉንም ኮፒ አግባብነት ያለው አካል ዋናው የውል ሰነድ ጋር ትክክለኛነቱን ያረጋገጠው እንደሆነ ስለመሆኑ፣  የምስክሮቹ ቃል ሊሰማ የሚገባውም የውሉ ቃል ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2011(1),2003 ,1730(1) Download Cassation Decision

 • 84446 civil procedure/ res judicata/ execution of judgment

  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5 ተፈፃሚነት በተከራካሪ ወገኖች መካከል በዋናው ጉዳይ ላይ ከላይ ወደ ታች በተዋቀሩት ፍ/ቤቶች ከተደረገ ክርክርና ከተሰጠ ውሣኔ ጋር በተገናኘ እንጂ በአፈፃፀም ከተሰጠ ትእዛዝ (ውሣኔ) ጋር በተያያዘ ተፈፃሚ ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5, 32 Download Cassation Decision

 • 84623 tax law/ criminal law/ criminal liability/ civil liability/ default of payment of tax

  አንድ ሰው ለመንግስት ሊከፍል የሚገባውን ግብር ባለመክፈሉ በወንጀል ተግባር ሊጠየቅና ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ የሚችለው ግብሩን ላለመክፈል በማሰብና ግብር አስገቢው መ/ቤትም ንብረቶቹን በመያዝና በመሸጥ የግብር ገንዘቡን ገቢ እንዳያደርግ ለማድረግና ግብር የመክፈል ኃላፊነቱን ለማምለጥ ንብረቶቹን ለማሸሽ፣ የመሰወር ወይም ሌሎች ተገቢነት የሌላቸው ህገ ወጥ ተግባራትን በመፈፀም ግብርን ያልከፈለ መሆኑ ሲረጋገጥ እንጂ በሌሎች በህግ ተቀባይነት ባላቸው ምክንያቶች ግብሩን ለመክፈል ሳይችል የቀረ እንደሆነ ስላለመሆኑ፣  ማንኛውም ሰው በፍ/ብሔር ጉዳይ ያለበትን እዳ ለመክፈል ባለመቻሉ ምክንያት ብቻ በወንጀል ጉዳይ ጥፋተኛ ተብሎ ሊቀጣ የማይገባ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 285/94 አንቀጽ 49 አዋጅ ቁ. 286/94 አንቀጽ 96, 162 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 13(2) ደንብ ቁጥር 78/94 ICCPR- አንቀጽ 11 Download Cassation Decision

 • 84661 labor dispute/ scope of application of labor proclamation/ manager/ work rules

  የሥራ መሪ የሆነ ሠራተኛ ያለ አግባብ ከሥራ መሰናበቱ ተረጋግጦ ሲወሰንና የአሰሪው የመተዳደሪያ ደንብ የሚፈቅድለት ከሆነ በአዋጅ ቁ. 377/96 መሠረት ኪሣራ ታስቦ ሊከፈለው የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.2574(2) አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 43(4) (ሀ Download Cassation Decision

 • 85009 commerical law/ property law/ cooperative society/ joint ownership

  የህብረት ሥራ ማህበራት ንብረት እንደ የአባለቱ የጋራ ሀብት (ንብረት) ተቆጥሮ ንብረቱን ለመሸጥ የሁሉም አባላት ስምምነት ያስፈልጋል ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  የህብረት ሥራ ማህበራት አሰራር ጋር በተያያዘ ውሣኔ ለማሳለፍ የሚችለው የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 147/91 አንቀጽ 21, 18, 32, 19 ደንብ ቁጥር 106/96 አንቀጽ 20(2) 123 Download Cassation Decision

 • 85102 civil procedure/ law of sucession/ will/ res judicata/ power of appellate court

  የኑዛዜ ህጋዊነት ጋር በተያያዘ በተካሄደ ክርክር ተሣታፊ ሆኖ ተቀባይነት ያጣና ኑዛዜው በፍርድ ቤት የፀደቀበት ሰው በሌላ ጊዜ የኑዛዜውን ህጋዊነት አስመልክቶ በመቃወሚያነት የሚያቀርበው ክርክር ወይም አዲስ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣  የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በቀረበለት ጉዳይ ላይ ዳኝነት መስጠት የሚገባው በስርዓቱ መሠረት የቀረበለትን የይግባኝ አቤቱታ መሠረት በማድረግ እንጂ ቀድሞ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ ተገቢ አልነበረም በሚል ምክንያት ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5,212 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 881 Download Cassation Decision

 • 85237 criminal law/ double jeopardy/ constitution

  አንድ ሠው በአንድ ወንጀል ድርጊት ክስ ቀርቦበት የመጨረሻ የሆነ ውሣኔ ተሰጥቷል በማለት በድጋሚ ልከሰስ አይገባም በሚል የሚያቀርበው ክርክር ከዚህ ቀደም ተጣርቶ ክስ የቀረበበትና የመጨረሻ ውሣኔ የተሰጠበት የወንጀል ድርጊትን በድጋሚ (ለሁለተኛ ጊዜ) ክስ ቀርቦበታል ከተባለው የወንጀል ድርጊት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑ ተገናዝቦ ሊታይ የሚገባው ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 2(5), 678, 696(ሐ) እና 378 ህገ መንግስት አንቀጽ 23 Download Cassation Decision

 • 85468 civil procedure/ evidence law/ time to present documentary evidence

  ተከራካሪ ወገኖች በቅድሚያ ሊያቀርቧቸው ሲችሉ ሆነ ብለው ወይም በቸልተኝነት ያላቀረቧቸውን ማስረጃዎች በክርክር ሂደት ሁሉ እያንጠባጠቡ ሊያቀረቡ ወይም የማስረጃ ማሰባሰብ ሥራውን ፍርድ ቤት እንዲያከናውን ሊጠይቁ የሚችሉበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣  በፍ/ቤት እገዛ ማስረጃ የሚቀርበው ተከራካሪ ወገን አጠቃቅሎ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ በቅድሚያ ሲረጋገጥ ስለመሆኑና ፍ/ቤቱ የተጠየቀው ማስረጃ ለተያዘው ጉዳይ ያለውን አግባብነት በተመለከተ የተቀበለው እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 234(1) Download Cassation Decision

 • 85596 criminal law/ suspension of penalty

  በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ተከሣሽ ላይ የሚወሰነው የእስራት ቅጣት አፈፃፀም እንዲገደብ ለማድረግ ስለማይችልባቸው ሁኔታዎች፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 194(1) እና (2)¸190¸192 Download Cassation Decision

 • 85718 civil procedure/ jurisidiction/ validity of judgment

  አንድን ጉዳይ ለማየት በህግ ስልጣን በሌለው ፍ/ቤት ታይቶ የተሰጠ ውሣኔ በይግባኝ ታይቶ እንዲታረም ካልደተረገ በቀር በጉዳዩ ላይ አስገዳጅነት ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 212 Download Cassation Decision

 • 85764 civil procedure/ execution of judgment/ jurisdiction

  አንድን የተሰጠ ፍርድ ከማስፈፀም ጋር በተገናኘ የአፈፃፀም ስልጣን መሰረቱ ፍርዱን መስጠት ወይም ፍርዱን በሰጠው ፍርድ ቤት ፍርዱን ለማስፈፀም የሚያስችል ውክልና ማግኘት እንጂ የፍርድ ባለዕዳውን ወይም ባለመብቱ የሚኖርበት ክልል (ከተማ) ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 378 Download Cassation Decision

 • 85873 civil procedure/ compromise agreement/ out of court compromise

  አንድ ስምምነት በፍ/ቤት ሊፀድቅ የሚችለው ጉዳዩ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት በመታየት ሂደት ላይ እያለ ተከራካሪ ወገኖች ጉዳዩን በስምምነት የጨረሱ መሆኑን ገልፀው ይኼው ስምምነት ለህግና ለሞራል ተቃራኒ ያለመሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፣  ከፍርድ ቤት ውጪ በሚደረግ እርቅ ወይም ግልግል መሰረት ያለመግባባትን ያስቀሩ ወይም ለጉዳያቸው እልባት ያገኙ ሰዎች የእርቁን ወይም የግልግሉን ስምምነት በፍርድ ቤት ማስመዝገብ ወይም ማስፀደቅ የማያስፈልጋቸው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 277 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3312 እና 3324 Download Cassation Decision

 • 85979 property law/ religious institution/ ownership of graveyard/ constitution

  የአንድ እምነት ወይም ሐይማኖት ተከታይ ወይም አማኝ በመሆን በሐይማኖታዊ ተቋሙ ውስጥ የመቃብር ቤት ገንብቻለሁና የቤቱን ግምት ይከፈለኝ በሚል ከሚቀርብ ጥያቄ ጋር በተገናኘ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1179 ድንጋጌ ተፈፃሚ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1179 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 11,27 (1-3) UDHR-Art. 18 ICCPR.Art. 18(1) Download Cassation Decision

 • 86049 property law/ civil procedure/ jurisdiction/ relief requested/ ownership/ expropriation

  ፍርድ ቤቶች ከሣሽ በክሱ ገልፆ በትክክል ዳኝነት የጠየቀበት ጉዳይ በቤት ላይ ያለውን የባለሀብትነት መብት ለማስከበርና የመፋለም ክስ ሆኖ እያለ ክሱ የቀረበው በአዋጅ የተወረሰ ቤት ወይም ከአዋጅ ውጪ በባለስልጣን ቃል ትእዛዝ ወይም በቀላጤ የተወሰደን ቤት ለማስመለለስ ነው በሚል ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት የሚሰጡት ውሣኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 47/67 የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2257 Download Cassation Decision

 • 86133 civil procedure/ excution of judgment/ investigation of claims to attached property

   በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418 መሠረት የሚቀርብ አቤቱታ መደበኛውን የሙግት ሥነ- ሥርዓት ተከትሎ መከናወን ያለበት ስለመሆኑ፣  በፍርድ አፈፃፀም ደረጃ ንብረት እንዳይያዝ ወይም እንዳይከበር በሚል የመቃወሚያ አቤቱታ በቀረበ ግዜ ጉዳዩን የያዘው የአፈፃፀም ችሎት በንብረቱ ላይ ተቀዳሚ መብት አለኝ በሚል የቀረበውን የመቃወም አቤቱታ በመደበኛው የሙግት ሥነ-ሥርዓት ሂደት ክርክሩን በማስተናገድ ንብረቱ እንዲያዝ ወይም እንዲከበር የሚያደርግ ህጋዊና በቂ ምክንያት መኖር ያለመኖሩን በማስረጃ በማጣራት ለጉዳዩ እልባት መስጠት ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418, 419, 421 Download Cassation Decision

 • 86187 contract law/ evidence law/ denial of signature/ error of law

  ተከራካሪ ወገኖች በአንድ የሰነድ ማስረጃ ላይ የተመለከተን ፊርማ የማን ስለመሆኑ በሚመለከተው የመንግስት አካል ተጣርቶ ውጤቱ ከቀረበና ከታወቀ በኋላ ሰነዱ በውጭ አገር ተመርምሮ ውጤቱ እንዲታወቅ በማለት የሚያቀርቡት ጥያቄ በህግ አግባብ አጥጋቢና አሣማኝ ምክንያትን በመጥቀስና በማስረጃ አስደግፈው ያላቀረቡ እንደሆነ ጥያቄው ተቀባይነት ሊኖረው የማይቻል ስለመሆኑ፣  የፍ/ቤት የተሰጠ ትእዛዘ /ውሣኔ/ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት የሚቻለው በተከራካሪ ወገኖች ፍትህ የማግኘት መብት ላይ መሠረታዊ ለውጥ የሚያስከትል እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2008, 2007, 2001, 2005 Download Cassation Decision

 • 86284 labor dispute/ termination of contract of employment/ damage to employee's property/

  በአሠሪው ንብረት ላይ ጉዳት በማድረሱ ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ የተሰናበተ ሠራተኛ ጉዳቱን ያደረስኩት በሥራ መደራረብ እና ከልምድ ማነስ ነው የሚል ምክንያት አቅርቦ የተከራከረ መሆኑ ስንብቱን ህገ ወጥ ነው ለማለት የሚያበቃ (የሚያስችል) ስላለመሆኑ፣አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27(1)(ሸ), 13(3) Download Cassation Decision

 • 86388 commerical law/ criminal law/ business license/ criminal liability

  የንግድ ሥራ ፈቃድ ኖሮት ነገረ ግን በህግ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ፈቃዱ ሳይታደስ በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የተገኘ ሰው የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ እንደሌለው ተቆጥሮ በወንጀል ኃላፊነት ጥፋተኛ ተደርጐ ሊያስቀጣው የሚችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 2(10), 36, 60(1) Download Cassation Decision

 • 86454 civil procedure/ counter claim/ court fee

  በአንድ የቀረበ ክስ በተከሣሽነት የተሰየመ ወገን በከሳሽ ከቀረበበት ክስ ጋር በተገናኘ ክስ በቀረበበት ንብረት (ጉዳይ) ጋር በተያያዘ የሚያቀርበው የዳኝነት ጥያቄ በህጉ አግባብ የተከሣሽ ከሣሽነት ክሱን ተገቢውን ዳኝነት በመክፈል ያቀረበ ካልሆነ በስተቀር ዳኝነት ሊሰጥ የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 234(1) (ረ)(ሠ), 215(2), 235(2) Download Cassation Decision

 • 86510 civil procedure/ statement of claim/ relief sought/ powe of court

   ከሣሽ የሆነ ወገን የሚያቀርበውን የዳኝነት ጥያቄ አይነትና መጠኑን በክሱ ማመልከቻ በግልጽ በማስፈር ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ፣  ተከራካሪ የሆኑ ወገኖች በህግ የተፈቀደን መፍትሔ ለማግኘት በግልጽ ዳኝነት መጠየቅ የሚገባቸው ስለመሆኑ፣  የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 241 ድንጋጌ መሠረታዊ ዓላማ ተከራካሪ ወገኖች በጽሁፍ ያቀረቡት ክርክር ለማብራራት እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 246-248 መሠረት ጭብጥ ለመመስረት እንዲያግዝ እንጂ በጽሁፍ ማመልከቻ ላይ ያልሰፈረን የዳኝነት ጥያቄ ተከራካሪዎች እንዲጠይቁ የሚያስችል ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 222, 234, 235, 236, 83, 224, 182, 241, 246-248, 251, 255 Download Cassation Decision

 • 86551 civil procedure/ dispute as to the amount of claim/ relief sought after

  አንድን ጉዳይ በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣኑ የሚመለከት ፍ/ቤት በህጉ አግባብ ክስ ተሻሽሎ ከፍ ያለ ዳኝነት ባልተጠየቀበት ሁኔታ በግምት ላይ ተቃውሞ ቀርቦ ግምቱ እንዲጣራ ሲደረግ የንብረቱ ግምት ከፍ ማለቱ በመረጋገጡ ብቻ ቀድሞ ከተጠየቀው ዳኝነት በላይ ዳኝነት የሚሰጥበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 182(1) ,92, 225, 226, 250,136 Download Cassation Decision

 • 86570 criminal law/ legitimate self defence

  ህጋዊ መከላከል (Legitimate self-defense) በወንጀል የማያስቀጣው የራስን ወይም የሌላን ሰው መብት ህገ ወጥ ከሆነ ጥቃት ወይም በቅርብ ከሚደርስ ህገ ወጥ ጥቃት ለማዳንና ጥቃቱ እንዳይደርስ ከማድረግ ሌላ አማራጭ (መንገድ) ሣይኖር ከሁኔታው መጠን ባለማለፍ የተፈፀመ ስለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 78 ,79 Download Cassation Decision

 • 86597 tax law/ criminal law/ Value added tax (VAT)/ vicarious liability of owner or manager/

  ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በተገናኘ ከሚመለከተው የገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ፈቃድ ሳያገኝ ተገቢ ያልሆኑ ፓዶችን (የVAT ደረሰኞችን) ማሳተምና መገልገል በወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑና የድርጅቱ ባለሀብት (ሥራ አስኪያጅ) ድርጊቱ ሲፈፀም በቦታው ያልነበረ መሆኑን በመግለጽ የሚያቀርበው መከራከሪያ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው ማንኛውም በጐ አሳቢ ሰው ሊያደርገው የሚችለውን ጥንቃቄ ያደረገና ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ ድርጅቱን በመምራት ኃላፊነቱን የተወጣ መሆኑን ማስረዳት የቻለ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 56(3),(ለ), 3(1)(ለ), 2(11), 3(1)(ሀ) አዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀጽ 2, 19(50) (ሐ) Download Cassation Decision

 • 86672 tax law/ criminal law/ Value added tax (VAT)/ criminal liability

  የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ነጋዴ (ሠው) ያለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሽያጭን አከናውኗል በሚል በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን ስለሚችልበት አግባብ፣ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 11(1)(2)፣ 22(1)(3) አዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀጽ 11(1) የወንጀል ህግ አንቀጽ 23(2)፣ 58(3) ደንብ ቁጥር 139/1999 Download Cassation Decision

 • 86813 contract law/ contract of surety/ employment contract/

  ከሠራተኛ ቅጥር ውል ጋር በተገናኘ የዋስትና ግዴታ የገባ ሰው የሠራተኛው የቅጥር ውል እንዲሻሻል ወይም እንዲለወጥ ከተደረገ በኋላ ሠራተኛው ከተሻሻለው ወይም ከተለወጠው የቅጥር ውል ጋር በተያያዘ ያለበትን ተጠያቂነት አስመልክቶ አስቀድሞ በገባበት የዋስትና ግዴታ መሰረት ተጠያቂ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1827(1) Download Cassation Decision

 • 86817 Civil procedure/ jurisdiction/ tax law/ tax exemption/ tour and travel

  ከአስጐብኚና የጉዞ ወኪል የንግድ ሥራ ፈቃድ ጋር በተያያዘ ከቀረጥና ታክስ ነፃ የሚገቡ መኪኖችን በተመለከተ የሚቀርብ ክርክርን መደበኛ ፍ/ቤቶች በቀጥታ ክስ ለማስተናገድ የሥረ ነገር ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 87(1), (5), (9), (10), ደንብ ቁጥር 146/2000 Download Cassation Decision

 • 86845 criminal law/ breach of trust/ corruption

  አንድ ሰው በስራው ስልጣን መሠረት በአደራ የተሰጠውን ወይም ሊጠብቀውና ሊከላከለው የሚገባውን የህዝብ ወይም የመንግስት ጥቅም የሚጐዳ ተግባር የፈፀመ እንደሆነ በወንጀል ህግ አንቀጽ 411 መሠረት በወንጀል ሊጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 411(ሐ), 407Download Cassation Decision

 • 86847 contract law/ contract of rent/ sub letting/ right of the lessor

  የማይንቀሣቀስ ንብረት ተከራይ የሆነ ሰው ንብረቱን በሙሉ ወይም በከፊል ለ3ኛ ወገን በኪራይ ሊሰጥ የሚችለው ተከራዩ አስቀድሞ ለአከራዩ አሳውቆ አከራዩ የማይቃወም መሆኑ ሲታወቅ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2957(1)(2), 1731 በአ.አ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ አስተዳደር ልማት ቢሮ ደንብ ቁጥር 3/2004, 4/2004 Download Cassation Decision

 • 87190 civil procedure/ appeal procedure/ time for appeal

  በፍ/ብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ የተመለከተው 60 ቀን የይግባኝ ማቅረቢያ ግዜ ታሳቢ የሚያደርገው እና ተፈፃሚ የሚሆነው ተከራካሪ ወገኖች ባሉበት ውሣኔ መሰጠቱን ወይም ለውሣኔ የሚያበቃ ክርክር የተደረገ መሆኑን ተረድተው ቀርበው ለመከታተልና የዳኝነቱን ውጤት ለመስማትና ለማወቅ ያልፈለጉትን ወይም ደግሞ የተከራካሪዎችን የመደመጥ መብት ማክበር ይቻል ዘንድ በህጉ በተዘረጋው ሥርዓት መሠረት በአግባቡ ጥሪ ተደርጐላቸው በጥሪው መሠረት ክርክራቸውን በአግባቡ ለመምራት ባልቻሉ ወገኖች ላይ ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 87285 labor dispute/ absence with leave/ sick leave

  አንድ ሠራተኛ ከሥራ መቅረቱ በህመም ምክንያት መሆኑ እንደበቂ ምክንያት ሊወሰድ የሚችለው በህጉ አግባብ፣ በህመሙ ምክንያት ስለመቅረቱ ለአሰሪው ያሳወቀና ፈቃድ ያገኘ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 85(4) Download Cassation Decision

 • 87338 labor dispute/ duration of contract of employment/ benefits of worker

  አንድ ሠራተኛ የቅጥሩ ውል አይነት ቋሚም ይሁን ግዜያዊ ለሠራተኛ በህጉ በተፈቀዱ ጥቅሞች የመጠቀምና ህጉ የሰጣቸውን ከለላዎች የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 162 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 42(2) Download Cassation Decision

 • 87420 Family law/ name/ family name/ change of name

  የቤተ ዘመድ ስም እንዲለወጥ በፍ/ቤት ጥያቄ ለማቅረብ የሚቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 42 , 33(1) , (2) Download Cassation Decision

 • 87834 civil procedure/ compromise agreement/ effect of compromise on third parties

   ተከራካሪ ወገኖች ለክርክራቸው ምክንያት ሊሆን የሚችለውን ጉዳይ ወይም ያከራከራቸውን ጉዳይ በእርቅ ስምምነት የጨረሱ እንደሆነ የእርቅ ስምምነቱ ግብ ተከራካሪዎቹ (ታራቂዎቹ) በግላቸው ያላቸውን መብትና ግዴታ እንደሁኔታው በማስተካከል ለክርክሩ መንስኤ የሆነውን ጉዳይ በስምምነት ማስቀረት ስለመሆኑና የእርቅ ስምምነቱ ውጤትና ተፈፃሚነቱ እርቁን ባደረጉት ተከራካሪ ወገኖች መካከል ብቻ ተገድቦ የሚቀር እንጂ የሌሎች 3ኛ ወገኖች መብትና ግዴታ ሁሉ በማካተት የ3ኛ ወገኖች መብትና ግዴታን አብሮ በእርቅ እንዳለቀ የሚያስቆጥር ስላለመሆኑ፣  የተከራካሪ ወገኖች የእርቅ ስምምነት በፍ/ቤት ትእዛዝ (ውሣኔ) መጽደቅና መመዝገብ መብቴን ወይም ጥቅሜን ይነካል በሚል 3ኛ ወገኖች የሚያቀርቡት የመቃወም አቤቱታ ህጋዊና ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3311 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 Download Cassation Decision

 • 88060 privatization/ commercial law/ administrative law

  የመንግስት የልማት ድርጅት ወደ ግል ይዞታነት፣ ወይም ወደ አክስዮን ማህበር፣ በሚለወጥበት ወይም ወደ ቀድሞ ባለሀብቱ በሚመለስበት ጊዜ ወደ አዲሱ ባለቤት የማይተላለፉ ሒሣቦችን ለመሰብሰብ ዕዳዎችን ለመረከብና የፍርድ ቤት ጉዳዮችን ለመከታተል ስልጣን የተሰጠው የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 208/92 አንቀጽ 5፣6 Download Cassation Decision

 • 88084 property law/ ownership/ sale of immovables/ title deed of immovable property/ constitution

  አንድ ሰው ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ የሚችለው በህግ ጥበቃ የሚደረግለትንና ያለውን መብት እንጂ የሌላውን መብት ስላለመሆኑ፣  በህግ ጥበቃ የሚደረግለት መብት ሣይኖር በስሙ የተመዘገበ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት የምስክር ወረቅተ ከያዘ ሰው ንብረቱን በመንደር ውል የገዛ ገዢ ተገቢውን ማጣራት በማድረግና፣ በጥንቃቄ፣ የገዛና የቅን ልቦና ያለው ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣  የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የተሰጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ደንብና አሰራርን መሠረት ያላደረገ እንዲሁም ከስልጣን ውጪ የተሰጠና በህግ ፊት የማይፀና ስለመሆኑ በማናቸውም ማስረጃ ለማረጋገጥ የተቻለ እንደሆነ በተሰጠው የምስክር ወረቀት የተፈጠረውን የህጉን የህሊና ግምት ማፍረስ የሚቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1195, 1196, 2884, 2882-2884 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40(1)(2) Download Cassation Decision

 • 88432 extracontractual liability law/ strict liability/

  አንድ ሠው በሰራው ሥራ ወይም በፈፀመው ድርጊትና ድርጊቱ በሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳያስከትል ተገቢውን ጥንቃቄ ባለማድረጉ ምክንያት በ3ኛ ወገኖች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት በፍ/ብሔር ኃላፊነት ተጠያቂ የሚሆን ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2069 Download Cassation Decision

 • 88798 property law/ possessory action/ contract of rent/ government houses/

  ከመንግስት የተከራየውን ቤት ከአከራዩ ፈቃድ ውጪ ለ3ኛ ወገኖች አከራይቶ ሲገለገል የነበረ ሰው በመንግስት መመሪያ መሠረት ቤቱ ተከራይቶ ሲሰራበት ለነበረው ሰው በመተላለፉ ምክንያት የመጀመሪያው ተከራይ በመመሪያው መሠረት ቤቱ የተላለፈለት ሰው ላይ የሚያቀርበው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 88867 civil procedure/ execution of judgment/ priority of creditors

  በአንድ የፍርድ ባለእዳ ንብረት ላይ ፍርድ እንዲፈፀምላቸው የሚጠይቁ የፍርድ ባለገንዘቦች ያሉ እንደሆነ አፈፃፀሙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403 መሠረት ሊስተናገድ የሚገባ እንጂ በሌላ የፍ/ባለመብት ምክንያት በሌላ የአፈፃፀም መዝገብ ላይ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቶ የአፈፃፀም ጥያቄው ካልቀረበ በስተቀር ሊቀጥል አይችልም ለማለት የማይችል ስለመሆኑ፣  አፈፃፀሙ በሚካሄድበት ወቅት በንብረቱ ላይ የመያዣ ውልን መነሻ በማድረግ የቀዳሚነት መብት አለን የሚሉ ወገኖች ያሉ እንደሆነም ጥያቄው በቀረበ ጊዜ እንደየአግባብነቱ ታይቶ ሊወሰን የሚገባው ስለመሆኑ፣  አፈፃፀሙን የያዘው ፍ/ቤት በንብረቱ ባለቤት ላይ የገንዘብ ክፍያ ፍርድ አሰጥተው እና ገንዘቡም እንዲከፈላቸው ጥያቄ ያቀረቡ የፍርድ ባለገንዘቦችን አስቀርቦ ጥያቄያቸውን በመመርመር ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ አኳያ አገናዝቦ በመመልከት አፈፃፀሙ ሊመራ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 403, 378 Download Cassation Decision

 • 88959 administrative law/ addis ababa city/ land law/ possessory action

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር በከተማው ክልል ውስጥ የሚገኘውን መሬትና የተፈጥሮ ሀብት የማስተዳደር ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ፣  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በህግ የተሰጠውን የማስተዳደር ስልጣን መሠረት በማድረግ በከተማው ክልል ውስጥ የሚገኘውን መሬት በተመለከተ የከተማዋን መሪ ፕላን እንዲሁም የከተማውን ማህበረሰብ ፀጥታና ደህንነት ታሣቢ በማድረግ በከተማው የሚገኝ ቦታ (መሬት) ለምን ለምን አገልግሎት መዋል እንዳለበት የመወሰን ስልጣንና ኃላፊነት ያለው ስለመሆኑና ይህንን ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገው እንቅስቃሴ እንደ የሁከት ተግባር ሊቆጠር የማይችል ስለመሆኑ፣  አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 11(2)(ለ)(ሰ), 38 Download Cassation Decision

 • 89088 civil procedure/ execution of judgment/ public auction/ second auction

  ለፍርድ አፈፃፀም ከተያዘ የሀራጅ ጨረታ ሽያጭ ጋር በተገናኘ ለሁለተኛ ጊዜ በወጣው ጨረታ የተያዘው ንብረት ሊሸጥ የሚገባው ባለሙያ ካቀረበው የንብረቱ ግምት ዋጋ በላይ በተገኘ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ብቻ ሣይሆን የባለሙያው ግምት ሳይጠበቅ በሁለተኛው ጨረታ ከተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ የሆነውን ዋጋ ላቀረበው ተጫራች ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 428(1) Download Cassation Decision

 • 89494 civil procedure/ evidence law/ documentary evidence

  የፍርድ ቤትን እገዛ በመጠየቅ ማስረጃ ማስቀረብ የሚቻለው ጠያቂው ተከራካሪ ወገን እንዲቀርብ የተጠየቀውን ማስረጃ ትክክለኛ ግልባጭ በቅርብ ግዜ ለማምጣት የማይችልበትን ወይም ለማስገልበጫ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመክፈል የማይቻል መሆኑን እንዲሁም ማስረጃው ለክርክሩ ምን ያህል ጠቃሚነት እንዳለውና ትክክለኛ ፍርድን ለመስጠት የሚያስችል ስለመሆኑ በጽሁፉ ገልፆ ለማስረዳት የቻለ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 89504 extracontractual liability law/ insurance/ indemnity/ subrogation

  ከውል ውጪ በሆነ ግንኙነት አንድ ሰው በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ባደረሰ ጊዜ ጉዳት የደረሰበት ንብረት ባለቤት ለንብረቱ የመድን ዋስትና የገባ ሆኖ የመድን ተቋሙ በመድን ውሉ መሠረት ጉዳት ለደረሰበት ወገን የጉዳት ካሣ በመክፈል በጉዳት አድራሹ ንብረት ባለቤት ላይ ብቻ ክስ በመመስረትና ጉዳቱን በቀጥታ ያደረሰውን ሰው በመተው ጉዳቱ ለደረሰበት ሰው የከፈለውን የጉዳት ካሣ ክፍያውን እንዲከፍለው ለመጠየቅ ስለመቻሉ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1677, 1896, 2081, 18, 2156 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 36(2) Download Cassation Decision

 • 89530 Civil procedure/ jurisdiction/ labor law dispute/ social courts

  የክርክሩ ገንዘብ መጠን ከአምስት ሺህ ብር በታች በመሆኑ ምክንያት ብቻ ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ጋር በተገናኘ የሚቀርብን ክርክር የቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤቶች አይተው ለመወሰን ስልጣን አላቸው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 138, 142 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 9(1), 231(1)(ለ), አዋጅ ቁ. 416/96 አንቀጽ 41(1), Download Cassation Decision

 • 89640 tax law/ custom law/ extra contractual liability/ assessment of damage

  ከጉምሩክ ህግና አፈፃፀም ጋር በተያያዘ በኮንትሮየባንድ ወንጀል ተጠርጥሮ በጉምሩክ ተቋም በቁጥጥር ሥር እንዲውል የተደረገ የንግድ ተሽከርካሪን አስመልክቶ ለንብረቱ ባለቤት የተቋረጠ ጥቅም (ገቢ) እንዲከፈል ሲወሰን የካሣውን መጠን ለመወሰን የተሽከርካሪውን ዓመታዊ የተጣራ ገቢ በተመለከተ ባለንብረቱ ለሚመለከተው የመንግስት አካል በህጉ አግባብ ያሳወቀውን የገቢ መጠን ከሌሎች አግባብነት ካላቸው ማስረጃዎች ጋር በማገናዘብና መሠረት በማድረግ ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ፣  በአንድ የመንግስት ባለስልጣን ተረጋግጦ የተሰጠ የሰነድ ማስረጃ በህጉ መሠረት ተቃውሞ ቀርቦበት ዋጋ የሌለው ስለመሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር ማስረጃው በማስረጃነት ዋጋ ሣይሰጠው ሊታለፍ የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2010, 2011, 2090, 2091, 2141, 2152, 2153 የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 136, 138, 180 (1 Download Cassation Decision

 • 89641 succession law/ partition of property/ liquidation of property/ petitio heriditatis/

  ከውርስ ሀብት ክፍፍል ጋር በተገናኘ የውርስ ሀብት ተጣርቶና ሪፖርት ቀርቦ በመጽደቁ መነሻነት ሀብቱ ተከፋፍሎ ከተፈፀመ በኋላ ወራሾቹ ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሣይኖራቸው ውርሱን ወይም ከውርሱ አንዱን ክፍል በእጁ አድርጓል በሚል እውነተኛ ወራሽ ወራሽነቱ እንዲታወቅለትና የተወሰዱበት የውርስ ንብረቶች እንዲመለሱለት በሚል ለመጠየቅ የሚችለው ተገቢውን የዳኝነት ክፍያ በመክፈል አዲስ ክስ በመመስረት እንጂ ክፍፍሉ ተፈጽሞና ውሣኔ አግኝቶ የተዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 996(1), 998(1), 999 Download Cassation Decision

 • 89893 civil procedure/ interlocutory order/ apeal procedure/

  አንድ ፍርድ ቤት ክርክርን በሚሰማበት ወቅት የሚሰጠው ጊዜያዊ አገልግሎት ያለው ትዕዛዝ (Interlocutory order) ላይ በመነጠል ክርክር የሚካሄድበት ዋናው ጉዳይ ላይ ውሣኔ ከመስጠቱ በፊት ይግባኝ ሊቀርብበት የሚችለው የተሰጠው ትእዛዝ በባህሪው የሰውን መታሰር ወይም የንብረት ማስተላለፍን ወይም ስም ማዞርን ጉዳይ በተመለከተ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 320(3)(4) Download Cassation Decision

 • 90089 criminal law/ bodily injury/ pregnant woman/ death of fetus/ homicide

  ነፍሰጡር (እርጉዝ) የሆነች ሴትን ሆዷ ላይ በመምታት ጽንሱ እንዲሞት ማድረግ ድርጊቱን በፈፀመው ሰው ላይ በግድያ ሙከራ የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 27(1), 581(ለ), 540 Download Cassation Decision

 • 90298 civil procedure/ cassation procedure/ power of court

  ባለ አምስት ዳኞች የሚሰየሙባቸው የክልል ፍርድ ቤቶች ሰበር ሰሚ ችሎቶች በአጣሪው ችሎት ጉዳዩ ያስቀርባል በሚል በተመለከተው ነጥብ (ጭብጥ) ሳይገደብ ሌላ (ሌሎች) ጭብጦችን በመመስረት ክርክሩ እንዲሰማ በማድረግ ውሣኔ ለመስጠት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 90389 labor dispute/ termination of contract of employment/ breach of responsibility by worker

  የሥራ ኃላፊነቱን ባለመወጣት ተገቢነት የሌላቸው ሰዎችን ወደ አሰሪው ድርጅት ውስጥ ዘልቀው እንዲገቡ በማድረግ ጥፋት የፈፀመ የጥበቃ ሰራተኛ ወደ ድርጅቱ በገቡት ሰዎች ምክንያት የተፈጠረ የፀጥታና የደህንነት ችግር አልተከሰተም በሚል ምክንያት ብቻ አሰሪው በሰራተኛው ላይ የፈፀመውን የስራ ውል ማቋረጥ ተግባር ህገ ወጥ ነው ሊያስብል የሚችል ስላለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27(1)(ሸ), 17(1)(ሸ)(ቀ), 14(2)(ሀ) Download Cassation Decision

 • 90452 civil procedure/ ex parte judgment/ setting aside exparte judgment

  በሌለበት የተሰጠ ውሣኔ እንዲነሣ በቀረበ አቤቱታ መነሻነት ፍ/ቤቱ አስቀድሞ የሰጠውን ውሣኔ ያነሳውና አቤቱታ አቅራቢው ክርክሩን እንዲያቀርብ በድጋሚ እድል ከተሰሠጠው በኋላ የጽሁፍ ክርክሩን ያላቀረበና ክሱ በሚሰማበት ቀጠሮ ያልቀረበ እንደሆነ ክርክሩን እንደገና ለመስማት በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት የከሣሽ ክስና ማስረጃ እንደገና ተመርምሮ ተገቢው ውሣኔ ከሚሰጥበት በቀር እንዲነሣ ትእዛዝ የተሰጠበት የቀድሞው ውሣኔ በቀጥታ ተመልሶ እንደገና እንዲፀና ሊደረግ የሚችልበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78(2), 70(ሀ) Download Cassation Decision

 • 90543 civil procedure/law of succession/ res judicata

  ከውርስ ሀብት ክፍፍል ጋር በተገናኘ አንድ ሰው ሟች በተውት ኑዛዜ መሠረት የጥሬ ገንዘብ ክፍያ እንዲከፈለው ክስ አቅርቦ ገንዘቡ እንዲከፈል ዳኝነት ከተሰጠ በኋላ በሌላ ግዜ የሟቹ የውርስ ሀብት ይጣራልኝ በማለት የሚያቀርበው የዳኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣  ኑዛዜን መሠረት አድርጐ የሚቀርብ የኑዛዜ ተጠቃሚት መብት ይረጋገጥልን ጥያቄና የውርስ ይጣራልኝ ጥያቄዎች ተመሳሳይ የሆነ የፍሬ ነገርና የህግ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዬች ስለመሆናቸው፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5(2) Download Cassation Decision

 • 90737 Civil procedure/ jurisdiction/ cooperative societies/ arbitration

  ከህብረት ሥራ ማህበራት ጋር በተገናኘ የማህበር የሥራ ኃላፊዎችን በተመለከተ ገንዘብ አጉድለዋል በማለት ገንዘቡ እንዲከፈል ማህበሩ በኃላፊዎቹ ላይ የሚያቀርበው ክስ አስቀድሞ በእርቅ ካልተቻለ ደግሞ በሽምግልና ሊታይ የሚገባው እንጂ በቀጥታ በመደበኛ ፍ/ቤት ክስ ሊቀርብበት አይችልም ለማለት የማይቻል ስለመሆኑና መደበኛ ፍ/ቤቶች ጉዳዩን አይተው ለመወሰን ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 49(1-4), 47(1), 26(2), 39(1)(ለ)(ሐ), 152 አዋጅ ቁጥር 402/96 አንቀጽ 46 ደንብ ቁጥር 106/96 አንቀጽ 14(ሀ)(ሐ)(መ) Download Cassation Decision

 • 90793 insurance/ formation of contract/ object of contract/ scope of liability of insurer

  አንድ ውል በቂ የሆነ እርግጠኛነት ያለውና ህጋዊ የሆነ ጉዳይ ለማከናወን ሊደረግ የሚገባ ስለመሆኑ፣  የመድን ዋስትና ሽፋን የተገባለት ተሽከርካሪ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ ከትራንስፖርት ጋር በተገናኘ በወጡ ህጐች ከተፈቀደው የመጫን አቅም በላይ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ አደጋ የደረሰበት እንደሆነ መድን ሰጪው የዋስትናውን ሽፋን ገንዘብ ለመድን ገቢው የመክፈል ኃላፊነት የማይኖርበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1678(ለ) Download Cassation Decision

 • 90862 contract law/ antichresis/ mortage/ unlawful enrichment/ reinstatement

  በመያዣ ውል መነሻነት አንድን የማይንቀሳቀስ ንብረት ከነይዞታው የያዘ ሰው በይዞታው ላይ የንብረቱ ባለቤት ሳይቃወመው ግንባታ የፈፀመ ከሆነ ተጠቃሹ የመያዣ ውል አይፀናም በሚል ተዋዋዬቹ ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ሲደረግ የንብረቱ ባለቤት በመያዣው ይዞታ ላይ የወጣውን የግንባታ ወጪ ግንባታውን ላካሄደው ወገን ለመክፈል የሚገደድ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1818, 2162 Download Cassation Decision

 • 90920 Civil procedure/ jurisdiction/ federal court/ intervention/ consti

  አንድን ክርክር በማስተናገድ ላይ ያለ የክልል ፍ/ቤት በፌዴራል መንግስት የተመዘገበ ተቋም (ድርጅት) አግባብነት ያለው የጣልቃ ገብ አቤቱታ በቀረበለት ጊዜ ጉዳዩን ጣልቃ ገቡን ወደ ክርክሩ በማስገባት አይቶ ለመወሰን ስልጣን የሌለው በመሆኑ ክርክሩ ጣልቃ ገብን ባካተተ መልኩ ለማየት ወደሚችለውና ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ጉዳዩ ቀርቦ ሊታይ የሚገባ መሆኑን ገልፆ መዝገቡን መዝጋትና ተከራካሪዎችን ማሰናበት የሚገባ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 5(6),14 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(4) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ህገ መንግስት አንቀጽ 64(4) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 9, 231(1)(ለ) Download Cassation Decision

 • 91103 civil procedure/ cost of litigation/ reimbursement

   ከወጪና ኪሣራ አወሣሠን ጋር በተገናኘ ከቅን ልቦና ውጪ ለክርክር የተዳረገ ወገን የክርከሩ ረቺ መሆኑ እስከታወቀ ድረስ ቅን ልቦና ከሌላው ወገን በክርክሩ ምክንያት ያወጣውን ወጪ እንዲተካለት በሚል ውሣኔ ሊሰጥ የሚገባ ስለመሆኑ፣  የወጪና ኪሣራ ጥያቄን አስመልክቶ ፍ/ቤቶች በመጠኑ ላይ ለመወሰን በህግ ስልጣን የተሰጣቸው ስለመሆኑና ረቺ የሆነ ወገን ሁል ግዜ ወጪና ኪሣራ እንዲተካለት ሊወሰን ይገባል ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 462-464 Download Cassation Decision

 • 91535 criminal law/ unlawful act/ elements of crime/

  አንድ ሠው ወንጀል አደረገ የሚባለው ህገ ወጥነቱ እና አስቀጪነቱ በህግ የተደነገገን ድርጊት ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ ስለመሆኑና አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለውም ወንጀሉን የሚያቋቁሙት ህጋዊ፣ ግዙፋዊና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ስለመሆኑ፣  ማንም ሰው በዋና ወንጀል አድራጊነት ወንጀል እንዳደረገ ተቆጥሮ የሚቀጣው በቀጥታ ወይም በእጅ አዙር ወንጀሉን ያደረገ በሆነ ጊዜ ወይም ወንጀሉን እርሱ በቀጥታ ባያደርገውም እንኳን በሙላ አሳቡና አድራጐቱ በወንጀሉ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆኑ ድርጊቱን የራሱ ያደረገ እንደሆነ ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 2፣23(1)፣ 32(1) የወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 111፣112፣141፣142 Download Cassation Decision

 • 91710 extracontractual liability law/ photograph/ compensation

  ባለፎቶግራፍ ወይም ባለስዕሉ ካልፈቀደ በቀር የማንም ሰው ፎቶግራፍ ወይም ስዕል በህዝብ አደባባይ ሊለጠፍም ሆነ ሊባዛ ወይም ሊሸጥ የማይችል ስለመሆኑና ፎቶው ወይም ስዕሉ ጥቅም ላይ ለዋለበት የማስታወቂያ ሥራ ባለፎቶው ወይም ባለስዕሉ ካሣ ሊከፈለው የሚገባ ስለመሆኑ፣ ለባለ ፎቶው ወይም ለባለስዕሉ የሚከፈለውን የካሣ መጠን ድርጊቱን የፈፀመው ሰው በዚሁ ድርጊት ያገኘው ሀብት (ጥቅም) ተመዛዛኝ በሚሆንበት መጠን በዳኛች ሊወሰን ስለመቻሉ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 28 29(2), 2142 Download Cassation Decision

 • 91968 civil procedure/ Review of judgment/ falsified documents

  ሀሰተኛ ማስረጃ ለፍ/ቤት በመቅረቡ የተነሣ የተወሰነበት ተከራካሪ ወገን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6(1)ን መሠረት በማድረግ ፍርዱ በድጋሚ እንዲታይለት አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ ሀሰተኛ ማስረጃውን የሰጠው አካል በምን ምክንያት በህገ ወጥ ተግባር ሀሰተኛውን ማስረጃ ሊሰጥ እንደቻለ የማስረዳት ግዴታ ጭምር አለበት ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6(1) የወንጀል ህግ አንቀጽ 403፣405 Download Cassation Decision

 • 92020 extracontractual liability law/ contract of carriage/ accident/ liability/ constitution/ children

  ጥቅምን መሠረት ባላደረገ ሁኔታ ህፃናትን (እድሜው ለአካለ መጠን ያልደረሰ ሰውን) አሳፍሮ በመጓዝ ወቅት በደረሰ አደጋ ምክንያት በህፃናቱ ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ የተሽከርካሪው ባለቤትና በወቅቱ በተሽከርካሪው ሲገለገል የነበረ ወይም ሹፌሩ የጉዳት ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርባቸው ስለመሆኑ፣  የተሽከርካሪ ባለቤት የሆነ ሰው ጥቅም በሌላው ግንኙነት መነሻ በተሽከርካሪው ተሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ ሰው ላይ ለሚደርስ የአደጋ ጉዳት ካሣ ለመክፈል የማይገደድ ቢሆንም ጉዳቱ የደረሰው ከፍተኛ ጥንቃቄና እንክብካቤ ሊደረግላቸው በሚገባ ህፃናት ላይ በሆነ ጊዜና ህፃናቱም ጥንቃቄ ባልተሞላበት ሁኔታ በተሽከርካሪው ላይ የተጫኑ (የተሣፈሩ) እንደሆነ የተሽከርካሪው ባለቤት የጉዳት ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርበት ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 36(2), 15, 25 የህፃናት መብቶች ስምምነት አንቀጽ 3, 6(1) የአፍሪካ ህፃናት መብቶችና ደህንነት ቻርተር አንቀጽ 4(1), 5(1) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2126(2), 2127, 2130 2131, 2089(2), 2081(1) Download Cassation Decision

 • 92459 civil procedure/ contempt of court

  በችሎት በመገኘት ስልክን ማስጮህ ብሎም ፍርድ በሚነበብበት ጊዜ በችሎት ዳኛው ሥነ- ሥርዓት እንዲይዝ ሲነገረው ችሎቱ በሥነ-ሥርዓት ያናግረኝ በማለት ያልተገባ ባህሪ ማሣየት በችሎት መድፈር ወንጀል ሊያስቀጣ የሚችል ተግባር ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 481 የወንጀል ህግ ቁጥር 449(1)(ሀ) Download Cassation Decision

 • 92466 labor dispute/ scope of application of labor proclamation/ manager

  አንድን ሠራተኛ የሥራ መሪ ነው ለማለት የሚቻለው በህግ ወይም እንደ ድርጅቱ የሥራ ፀባይ በአሰሪው በተሰጠ የውክልና ስልጣን መሠረት የሥራ አመራር ፖሊሲዎችን የማውጣትና የማስፈፀም እንዲሁም በተጨማሪነት ወይም ይህንን ሣይጨምር ሠራተኛን የመቅጠር፣ የማዛወር፣ የማገድ፣ የመመደብ ወይም ሌሎች የሥነ-ሥርዓት እርምጃ የመውሰድ ተግባሮችን የሚያከናውን እንደሆነ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 3(2)(ሐ) አዋጅ ቁ. 494/98 አንቀጽ 2(1)(ሐ) Download Cassation Decision

 • 92546 administrative law/ prosecutor

  በአቃብያነ ህግ ሙያ የተሰማሩ ሠዎች ላይ ከዲሲፒሊን ጉዳዬች ጋር በተያያዘ ክስ በቀረበ ጊዜ ጉዳዩ በተዋረድ በተቋቋሙትና ስልጣን በተሰጣቸው አካላት ታይቶ ሊወሰን ስለሚችልበት አግባብ፣ የአቃቤ ህግ መተዳደሪያ ደንብ ቁ. 44/1991 አንቀጽ 78, 79, 82(1)(2), 83(1)(3), 84(ሀ), 85, 86(ሀ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 25, 37 Download Cassation Decision

 • 93137 civil procedure/ review of judgment/ procedure in review of judegment

  የዳግም ዳኝነት (Review of Judgment) ዓይነተኛ ዓላማ ተገቢ ሁኔታዎችና ፍሬ ነገሮች ተሟልተው መገኘታቸው ሲረጋገጥ በሀሰተኛ ማስረጃ፣ በመደለያና በመሰል ወንጀል ጠቀስ ድርጊቶች ምክንያት የተዛነፈን ፍትህ ወደ ነበረበት መመለስ ስለመሆኑ፣  የዳግም ዳኝነት ጥያቄ (አቤቱታ) ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ተግባራት የሚከናወንበት በመሆኑ ጥያቄው ለሰበር ችሎት በቀረበ ጊዜ ችሎት አቤቱታውን ፍሬ ነገር የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ላላቸው የስር ፍ/ቤቶች ሊመራውና ሊያስተላልፈው በሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6(1)(ሀ)(ለ) አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) Download Cassation Decision

 • 93173 criminal law/ illegal arm possession

  ፈቃድ የሌላቸው የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶችን በቤቱ ውስጥ አከማችቶ የተገኘ ሰው መሣሪያዎቹን ለመነገድ በሚል ሀሳብ የያዘ መሆኑ የተረጋገጠ ካልሆነ በስተቀር ግለሰቡ በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን የሚገባው በወንጀል ህግ አንቀጽ 481(1)(ሀ) ሣይሆን በአንቀጽ 809(ሀ) ሥር በተመለከተው ድንጋጌ መሠረት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 481(1)(ሀ), 809(ሀ) Download Cassation Decision

 • 93741 criminal law/ negligence/ conditions for negligence

  አንድ ሰው በቸልተኝነት ወንጀል ፈጽሟል ሊባል የሚችለው የድርጊቱን ውጤት እያወቀ ውጤቱ አይደርስም ከሚል መነሻ ድርጊቱን የፈፀመ እንደሆነ ወይም ድርጊቱ የወንጀል ውጤት የሚያስከትል መሆኑን ባያውቅም ውጤቱን ማወቅ ነበረበት ወይም ጥረት ቢያደርግ ማወቅ ይችል ነበረ ለማለት የሚቻል እንደሆነ ስለመሆኑ፣  አንድ ሰው የፈፀመው ድርጊት በቸልተኛነት ነው ለማለት በመስፈርትነት ሊወሰድ የሚገባው የድርጊቱ ፈፃሚ በድርጊቱና በውጤቱ መካከል ያለውን ግንኙነት አስመልክቶ ያለው ወይም ሊኖረው የሚገባው ግንዛቤ ስለመሆኑና ይህም የድርጊቱ ፈፃሚ የነበረው እውቀትና ግንዛቤ ወይም ሊኖረው የሚገባውን እውቀትና ግንዛቤ መመዘን ያለበት ከግለሰቡ እድሜ፣ ያለው የኑሮ ልምድ የትምህርት ደረጃ ሥራውና የማህበራዊ ኑሮ ደረጃውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ፣ የወንጀል ህግ አንቀጽ 59(1), 543(2), 57 Download Cassation Decision

 • 93779 Family law/ divorce/ religious court/ sharia/ res judicata

  ተጋቢዎች የጋብቻቸውን ፍቺ አስመልክቶ ጉዳዩ በመደበኛው ፍ/ቤት ቀርቦና ክርክር ተካሄዶ ውሣኔ ከተሰጠበት በኋላ በሌላ ጊዜ በተመሳሳይ ጉዳይ ሀይማኖታዊ ስርዓትን በመጠቀም በሸሪአ ፍ/ቤት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 5(1)(2), 244(2)(ለ), 245(2) አዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀጽ 5(4), 6(2) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 34(5) Download Cassation Decision

 • 95995 Family law/ civil procedure/ cause of action/ change of name/ father name

  የአባት ስም እንዲስተካከልልኝ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ የክስ ምክንያት የለውም ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣  አንድ ሰው አንድ የቤተዘመድ ስምና አንድ ወይም ብዙ የግል ስሞችና የአባት ስም ሊኖረው ስለመቻሉና የአንድ ልጅ የአባት ስም የሚሆነው የአባቱ የግል ስም ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 231 (1)(ሀ) የፍ/ብ/ህ/ቁ. 32(1)፣ 36(1) Download Cassation Decision