volume 20

volume 20

 • 100395 property law/ sale of immovable property/ obligations of the seller

  የማይንቀሳቀስ ንብረት የሸጠ ሰው ንብረቱን ከሌሎች ሰዎች ቁጥጥር ይዞታ ሥር ነፃ አድርጎ ፣የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ባለሀብትነት ለማስተላለፍ የሚያስችሉ አስፈላጊ ሰነዶች ለገዢ የማስረከብና የማይንቀሳቀሰዉን ንብረት የማይነካ የባለሀብትነት መብት ለገዥ ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆነ ተግባራትን የመፈጸም ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2875፣ 2879(1)፣2281 Download Cassation Decision

 • 101003 criminal law/constitution/ cassation procedure/ participation in criminal offense/ accomplice/

  በአንድ የወንጀል ድርጊት በዋና ወንጀል አድራጊነት ወይም ግብረ አበርነት የተሳትፉ ተከሳሾች በግል ሁኔታዎች ሊኖር ከሚችለው ልዩነት በስተቀር ለተመሳሳይ የወንጀል አፈፃፀምና የወንጀል ተሳትፎ ተመጣጣኝና ተመሳሳይ ቅጣት ሊወሰን የሚገባ ስለመሆኑ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ቁጥር 196(1) ለሰበር ስርዓትም ተፈፃሚነት ያለውና ከተከሳሾች አንደኛው ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ውድቅ የሆነበትና አያስቀርብም የተባለን ተከሳሽ ጭምር ሊያካትት የሚገባ ስለመሆኑ፡- የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 25፣22 የወንጀል ሕግ አንቀጽ ፣4፣6 የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ 2/2006 አንቀፅ.3(2) Download Cassation Decision

 • 101277 civil procedure/ cassation procedure/ leave to cassation/ time for cassation appeal

  የሰበር አቤቱታ በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ሳይቀርብ ጊዜው ካለፈ የሰበር አቤቱታ ከመቅረቡ በፊት የይግባኝ ማስፈቅጃ ማመልከቻ መቅረብ ያለበት ሰለመሆኑ፤ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 22(4) ፣ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 324 Download Cassation Decision

 • 101462 constitution/ criminal law/ tax law/custiom law/ retroactive law

  ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የወጣ ህግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣው ሰው ጠቃሚ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ተፈጻሚነት ሊኖረው የሚገባው ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የወጣው ህግ ስለመሆኑ፣ በአዲሱ የጉሙሩክ አዋጅ ቁ. 859/2006 አንቀጽ 182 ስር የተመለከተው ድንጋጌ ተፈጻሚነት ሊኖረው የሚገባው ክርክር ካላስነሳው ጉዳይ በሌሎች ህጎች የተመለከቱት ድንጋጌዎች በማይነካ ሁኔታ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 22/2/ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ ጠቅላላ ክፍል በአንቀጽ 6 Download Cassation Decision

 • 102141 civil procedure/ pleaders/ agents

  አንድ በፍርድ ቤት የተወከለን ሰው በችሎት ተገቢ ያልሆነ ስነ ምግባር አሳይቷል በማለት ፍ/ቤት የውክልና ስልጣንን መሻር የማይቻል ስለመሆኑ፣ ፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 58 Download Cassation Decision

 • 102982 criminal law/ terrorism/ element of criminal offense

  ለሽብር ተግባር የሚያገለግል ንብረት ይዞ መገኘት ወንጀል ተፈፅሟል የሚባልበት አግባብ፤ በልዩ ሁኔታ በህግ የማስረዳት ሸክም ወደ ተከሳሽ ከዞረባቸው ወንጀሎች ውጭ ፤ ዓ/ህግ የሚያቀርበውን ክስ የወንጀል ደንጋጌውን የሚያቋቁሙት የህጋዊ ፣ግዙፋዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮችን የማሰረዳት ሸክም የመወጣት ግዴታ ያለበት ሰለመሆኑ፤ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141 ፣ የወ/ሕ/ቁ 23(2) ፤ የፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥ 652 Download Cassation Decision

 • 103478 civil procedure/ summary procedure/ check/ hearing of witnesses

  ቼክን በተመለከተ በአጭር ስነ ስርዓት /Summary proceding/ ዳኝነት ታይቶ እንዲወሰን ክስ በቀረበበት ወቅት ተከሳሽ መከላከያውን እንዲያቀርብ ጥያቄ አቅርቦ ተፈቅዶለት መልስ እንዲያቀርብ ተደርጎ መልስና በሕግ አግባብ ምስክር ቆጥሮ እያለ ምስክሮች ሳይሰሙ ይኼው ታልፎ የቼክ ባሕርይን ብቻ መሰረት ተደርጎ ዳኝነት የሚሰጥበት አግባብ ትክክል ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 285/1/ 286 እና 291 የን/ሕ/ቁ. አንቀጽ 717 Download Cassation Decision

 • 104544 insurance law/ civil procedure/ joint plaintiffs

  ከአንድ በላይ የሆኑ ከሳሾች በጋራ በመሆን የህብረት ክስ ሊያቀርቡ ስለሚችልበት ሁኔታ የመድን ሰጪውና የመድን ተቀባዩ ባደረጉት የመድን ሽፋን ውል ላይ የማግለያ ድንጋጌ በስምምነታቸው እስካሰፈሩ ድረስ ይኸው ሊጠበቅ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.35 Download Cassation Decision

 • 104943 civil procedure/ execution of judgment

  አንድ ለፍርድ ማስፈጸሚያ በሐራጅ ይሸጥ የተባለን ንብረት በባለሙያው የተቀመጠውን የሐራጁ መነሻ ዋጋ አነሰ በማለት የሐራጅ ሽያጩ ተከናውኖ ውጤቱ ባልታወቀበት ሁኔታ የተጀመረው አፈጻጸም ቀሪ ይሁን ማለት ተገቢ ስላለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 105125 property law/ constitution/ acquisition of ownership

  አንድ ሰው ህጋዊ ባለይዞታው ሳይቃወም በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ቤት ወይም ንብረት ያፈራ እንደሆነ የዚሁ ቤት/ ንብረት/ ባለመብት የሚሆን ስለመሆኑ፣ የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 1179(1)(2) ከኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40 አኳያ ሊታይ ስለሚችልበት አግባብ Download Cassation Decision

 • 105677 civil procedure/ res judicata/ valid judgment

  አንድ የዳኝነት አካል የሥረ - ነገር ስልጣን ባይኖረውም እንኳን የሰጠው ውሳኔ ሥርዓቱን ተከትሎ እስካልተሻረ ድረስ የፀናና የመጨረሻ በመሆኑ አዲስ ክስ በተመሳሳይ ጉዳይ ማቅረብ ተገቢ ስላለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5/1/ እና 212 Download Cassation Decision

 • 105694 Family law/ certificate of marriage/ cancellation of certificate of marriage

  የጋብቻ የምስክር ወረቀት ተገቢውን ስርዓት ተከትሎ የተሰጠ አይደለም ተብሎ መሰረዝ ጋብቻ አልነበረም ለማለት የሚያስችል ስላለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 105752 contract law/ cancellation of contract/ cancellation by agreement

  በአንድ ውል ውስጥ ውልን የሚያፈርሱ የስምምነት ቃሎች ተገልጾ ከተጻፈና የዚህም ስምምነት አፈጻጸም ጉዳይ ተሟልቶ ከተገኘ አንደኛው ተዋዋይ ውል ፈርሷል ሲል መግለጽ የሚችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 1786 Download Cassation Decision

 • 105956 civil procedure/ power of court/ liquidator/ evidence law/ expert testimony

  ሒሳብ አስተሣሣቢ የመመደብ ሥልጣን ያለው ዋናው ጉዳይ በዳኝነት አይቶ የመወሰን ስልጣን ያለውና የግራ ቀኙን ክርክር የሰጠው ፍ/ቤት ስለመሆኑ፣ አንድን ጉዳይ ለመወሰን የቀረቡት /የተሰጡት/ የሙያ አስተያየቶች ተቃራኒ ይዘት ባለበት ሁኔታ የአንድን ባለሙያ አስተያየት ብቻ በመቀበል መወሰን ተገቢ ስላለመሆኑ፣ ( የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 136፣145/1/፣246፣248 እና 264 Download Cassation Decision

 • 106436 property law/ rural land law/ tigray land law/ public notary/ authentication

  በትግራይ ክልል በገጠር መሬት ላይ የሚደረግ ልውውጥ ሕጋዊ ነው የሚባለው በውልና ማስረጃ ፀድቆ የወረዳው የመሬት ዴስክ አውቆ በቅጽ ተሞልቶ የተለዋወጡ ከሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣ የትግራይ የመሬት አዋጅ ቁጥር 239/06 እና ደንብ ቁጥር 48/2000 Download Cassation Decision

 • 107217 civil procedure/ first hearing/ admission

  ማናቸውም ተከራካሪ ወገን በመከላከያ መልሱ ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ የተከሰሰበትን ነገር በሙሉ ወይም በከፊል የሚያምን መሆኑን የገለጸ እንደሆነ ወይም በሚደረግ ምርመራ የእምነት ቃሉን የሰጠ እንደሆነ ፍ/ቤቱ በታመነው ገር ላይ ብቻ ፍርድ መሰጠት ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 83 ፣234/1/ /ሠ/ ፣ 241 እና 242 Download Cassation Decision

 • 107542 contract law/ contract of sale/ defect/ cancellation of contract

  በተሸጠ ነገር ላይ የተገኘው ጉድለት ለውል ማፍረሻ ምክንያት ሊሆን ስለማይችልበት ምክንያት የፍ/ሕ/ቁ.2344(2) ፣2289(1) Download Cassation Decision

 • 107777 property law/ urban land law

  የከተማ ቦታ የሊዝ ይዞታ በሚቋረጥበት ወቅት /ሲቋረጥ / ባለይዞታው እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በቦታው ላይ ያሰረፈውን ንብረት በማንሳት ቦታውን አግባብ ላለው አካል መልሶ ማስረከብ ያለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 26(5) እና (6) Download Cassation Decision

 • 108328 law of inheritance/ liquidation of succession/ power of court

  አንድ ፍ/ቤት የውርስ ክርክርን አስመልክቶ የሚቀርብለትን የውርስ አጣሪዎች ቃለ- ጉባኤ ከማስጽደቁ በፊት በእርግጥ የውርስ ሀብት የማጣራት ሕጋዊ ሂደት ተከትሎ የተካሄደ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 946፣950፣1062፣1079፣1080 Download Cassation Decision

 • 108550 criminal law/ custom offense/ tax law/ confiscation

  የጉምሩክ ወንጀል ጋር በተያያዘ ፤ተከሳሽ በወንጀሉ ጥፋተኛ ባይባልም ንብረቱ የሚወረሰው ሰለድርጊቱ አፈፃፀም ሁኔታ የሚያሰረዳ አጥጋቢ ማስረጃ መቅረቡን ፍ/ቤቱ አሳማኝ ሆኖ ሲያገኘው ስለመሆኑ ፤ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 104 እና አዋጅ ቁጥር 859/2006 Download Cassation Decision

 • 108638 contract law/ government houses/ cancellation of contract

  የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በይዞታው ስር የሚገኙትን የመንግስት ቤቶች ለማከራየት የሚያደርጋቸው ውሎች ያልተጠበቁ ምክንያቶች ካልተከሰቱ እና በተለይም ደግሞ ውሉን ለማቋረጥ የሚያስችል በተከራይ ወገን በኩል ጥፋት ተፈጽሟል ካልተባለ በቀር በድርጅቱና በተከራዮች መካከል የሚደረጉ ውሎች በየዓመቱ እየታደሱ የሚቆዩ ስለመሆኑ፣ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁጥር 555/2000 አንቀጽ 6/1/ Download Cassation Decision

 • 108647 civil procedure/ intervention by third party/ preliminary objection

  በክርክር ወቅት ጣልቃ እንዲገባ የተፈቀደለት ተከራካሪ በመጀመሪያ ሊያቀርብ የሚፈልገውን መቃወሚያ እንዳያቀርብ የሚከለክለው ህግ የሌለ ስለመሆኑ፣ ( የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41 ፣234/1/ Download Cassation Decision

 • 109054 civil procedure/ joinder of suits/ relief sought

  አንድ ከሳሽ ክሱን የመሰረተው በብዙ ጉዳዮች ወይም በተለያዩ ነገሮች ላይ የሆነ እንደሆነ በተለይ በእያንዳንዱ ጉዳይ እንዲታይ የሚጠይቀውን ዳኝነት መግለጽ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 224(2) Download Cassation Decision

 • 109061 contract law/ contract of carriage/ damage

  የደረሰው ጉዳት አጓዥ በፈጸመው ተግባር ወይም ባደረገው ጉድለት እንዲሁም ይህ ተግባር አደጋ ሊያደርስ ወይም ሊፈጥር የሚችል መሆኑ እየታወቀ ሲሆን የኃላፊነት መጠኑ በህጉ ከተቀመጠው ውጪ ሊሆን የሚችል ስለመሆኑ፣ በልጅ ቀለብ አወሳሰን ረገድ ልንከተላቸው ስለሚገቡ መሰረታዊ መርሆች ( የን/ሕ/ቁ. 597፣ 599) (የፍ/ሕ/ቁ. 2091፣ 2092 የኢ.ፌ.ድ.ሪ የቤተሰብ ህግ ቁ.. 213/92 አንቀጽ 197 Download Cassation Decision

 • 109392 contract law/ surety contract/ contract of employment

  የዋስትና ውል ግዴታ ሰራተኛው ተቀጥሮ በሚያገለግልበት ወቅት ለሚደርሰው የገንዘብና የንብረት መጥፋትና መጉደል ተጠያቂ የሚያደረግ ስለመሆኑ፣ የፍ/ሔር/ሕ/ቁ. 1933/1/ 1897 Download Cassation Decision

 • 109563 civil procedure/ power of court/ evidence law/ additional evidence

  ፍ/ቤቶች እውነትን ለማውጣት ማስረጃ አስቀርበው መስማት አለባቸው ሲባል በቀረበው ማስረጃ እውነት እስከተረጋገጠ ድረስ የግድ ተጨማሪ ማስረጃ እንዲያቀርቡ የሚገደድበት ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ፣ የፍትሐብሔር ክርክር ማስረጃ የሚሰማውና ፍሬ ነገር እንዲጣራ የሚደረገው በማስረጃ የሚገኘው ፍሬ ለዳኝነት አሰጣጡ እጅጉን አስፈላጊና የግድ ሆኖ ሲገኝ ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 110040 law of inheritance/ intestate succession/ representation

  በፍ/ብ/ህ/ቁ. 842/3/ መሰረት የተተኪ ወራሽነት ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝ ሊሟሉ ስለሚገባቸው ጉዳዮች፣ Download Cassation Decision

 • 110680 law of inheritance/ things making up inheritance

  የአንድ ሰው መብትና ግዴታ ለተወላጆቹ በውርስ ሊተላለፍ የሚችለው በሟቹ ምክንያት የሚቋረጡ ካልሆነ በቀር ሟቹ በሞተበት ቀን የነበሩት መብቶችና ግዴታዎች ስለመሆናቸው፣ የፍ/ሕ/ቁ. 826/2/ ሟች የድርሻ መልቀቅ ውል ፈጽሞ ከዚያም ኑዛዜ ቢያደርግና ይኽው ኑዛዜ የድርሻ መልቀቁን ውል እስካልነካ ድረስ የውሉን ተፈጻሚነት ሊያስቀር የማይችል ወይም በአዲሱ ኑዛዜ ተተክቷል ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 900 እና 901 Download Cassation Decision

 • 110901 civil procedure/ jurisdiction/ addis ababa/ urban land law/ expropriation/ compensation

  የአዲስ አበባ ከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የቤት ባለቤትነት ክርክርን አጣርቶ የመወሰን ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ፣ Download Cassation Decision

 • 111311 property law/ urban law law/ illegal possession of land

  ማንኛውም ሰው አግባብ ካለው አካል ፈቃድ ሳያገኝ በህጋዊነት ከያዘው ይዞታ ጎን ያለን የከተማ ቦታ አስፋፍቶ መከለልና መጠቀም የማይቻል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 5(2) Download Cassation Decision

 • 111960 constitution/ criminal law/ tax law/custiom law/ retroactive law

  የተሻረው ህግ ይሰራ በነበረበት ጊዜ የተፈጸመ ወንጀል ሲኖርና በዚህ ህግ ግን እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ሊያስከስስም ሆነ ሊያስቀጣ አይችልም ፣ ክሱም ተጀምሮ እንደሆነ የሚቋረጥ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 5/3/ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 99፣ አዋጅ ቁ. 859/2006 Download Cassation Decision

 • 112190 property law/ sale of immovable property/ government house/ good faith

  በመንግስት የተወረሰን ቤት የባለቤትነት መብት ከሌለው ሰው/አካል/ መግዛት የማይንቀሳቀስ ንብረትን በቅን ልቦና ባለሀብትነትን የሚያጎናጽፍ ስላለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 47/67 Download Cassation Decision

 • 113002 Family law/ pension/ common property

  ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል ተጠቃሚ ሆነው ባሉበት ፍቺ ቢከሰት የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነው ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል ለባል ወይም ለሚስት ሊያካፍል የሚገባ ስላለመሆኑ ፣ የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/95 አንቀጽ 35 Download Cassation Decision

 • 113143 criminal law/ criminal procedure/ judgment writing

  የወንጀል ጉዳዮችን በመጀመሪያ ደረጃ ይሁን በይግባኝ ደረጃ የሚመለከት ፍ/ቤት ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ የማስረጃውን አጭር መግለጫ፣ ማስረጃውን የተቀበለበትን እናያልተቀበለበትን ምክንያቶች በፍርድ ላይ ማስፈር የሚገባው ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 149/1/ Download Cassation Decision

 • 113529 law of inheritance/ death of heir/ transfer of right/ certificate of heir

  ለአንድ ውርስ ወራሽ የሆነ አንድ ሰው ውርስ ከተከፈተ በኋላ የሞተ እንደሆነ የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባያወጣም ለውርሱ አይገባም እስካልተባለ ድረስ የወራሸነት መብቶች ለእርሱ ወራሾች የሚተላለፍ ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 114279 Family law/ rural land law/ Amhara land law/ common property

  የገጠር መሬት እንደሌላው ንብረት በመቁጠር ከቤተሰብ ህጉ አንጻር የሚታይ ስላለመሆኑ ፣ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በአንድ ተጋቢ ስም ተዘጋጅቶ ከተሰጠ በኋላ ጋብቻ ቢፈፀምና ተጋቢዎቹ መሬቱን የጋራ ለማድረግ ሊስማሙ የሚችሉ ስለመሆኑ፣ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 133/1999 አንቀጽ 24/3/ ደንብ ቁ. 151/1999 አንቀጽ 20/6/ Download Cassation Decision

 • 114553 contract law/ evidence law/ signature

  በአንድ ሰነድ ላይ ያለን ፊርማ በቴክኒክ ምርመራ የማን እንደሆነ ለማረጋገጥ ባልተቻለ ጊዜ ፊርማው ሲፈረም የነበሩ ምስክሮችን ቃል በመስማትና በሌሎች ማስረጃዎች ፊርማው የማን እንደሆነ በመመዘን ማረጋገጥ የሚቻል ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 2472(1) Download Cassation Decision

 • 114622 civil procedure/ jurisdiction/ oromia/ urban land law/ expropriation

  በኦሮሚያ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚነሱ የከተማ ቦታን ከማስለቀቅና ምትክ ቦታ እና ካሣን ከመክፈል አንጻር የሚነሱ የመብት ጥያቄዎችን በመጀመሪያ ደረጃ የማየት ስልጣኑ በከተማው አስተዳደር የተዋቀረው አካል ስለመሆኑ፣ የኦሮሚያ ክልል የመሬት ሊዝ አዋጅ ቁ. 721/2004 አንቀጽ ቁ. 26፣27፣28፣29 እና 30 አዋጁን ለማስፈጸም የወጣው ደንብ ቁጥር 155/2005 አንቀጽ 26፣55 እና 56 Download Cassation Decision

 • 114623 civil procedure/ compromise agreement/ binding nature of compromise agreement

  ተከራካሪ ወገኖች በፍርድ ቤት የሚከራከሩበትን ጉዳይ በእርቅ መጨረስ የሚችሉና የእርቅ ውሉን ጉዳዩን ለሚያየው ፍርድ ቤት አቅርበው ማፀደቅ እንደሚችሉ ፍርድ ቤት ቀርቦ የፀደቀ የእርቅ ውል ሥምምነት በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ ያህል አስገዳጅነትና ተፈፃሚነት ያለው ከመሆኑ ባሻገር በዚህ እርቅ ውል ተካፋይ ያልሆነ መብቴ ተነክቷል የሚል ወገን የፍርድ መቃወሚያ ሊያቀርብ የሚችል ሥለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.276፣277(1) እና 358 Download Cassation Decision

 • 114816 civil procedure/ admission/ the party who starts case

  ተከሳሽ ከሳሽ ያቀረበውን ክስ አምኖ ነገር ግን ሕግ ወይም ሌላ ፍሬ ነገር በመጥቀስ የቀረበብኝ ክስ ዋጋ የለዉም ብሎ የሚከራከር ከሆነ ሙግቱን የሚጀምረው ተከሳሽ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 258/1/ Download Cassation Decision

 • 114888 civil procedure/ execution of judgment

  አንድ ጠበቃ ሕግን የማስከበር ፣ፍትህን የማስገኘትና ለፍትህ አስተዳደሩ የማገዝ ኃላፊነቱን በመተው ተቃራኒ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ መሆኑ ከተረጋገጠ የጥብቅና ፍቃዱ ሊሰረዝ የሚችል ስለመሆኑ የአማራ ክልል የጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ ምዝገባና የጠበቆች ሥነምግባር ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁ. 75/1994 Download Cassation Decision

 • 115763 insurance law/ property insurance/ mortgage/ pledge/

  ለአንድ ንብረት የሚከፈለው የኢንሹራንስ ገንዘብ የመያዣ መብት ላላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች ይሰጣል የሚለው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ኢንሹራንስ ሰጪው ላልተከፈለ የአርቦን ክፍያ ኢንሹራንስ ገቢውን ከመጠየቅ ውጪ የመያዣ መብት ያለውን አካል መጠየቅ የማይችል ስለመሆኑ የን/ሕ/ቁ.684(1) Download Cassation Decision

 • 115892 civil procedure/ appeal/ interlocutory appeal/ preliminary objection

  መብቴን የሚነካ ፍርድ ተሰጥቷል በሚል የሚቀርብ የፍርድ መቃወሚያን ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይቅርብ በማለት የሚሰጥ ውሳኔ ተገቢ ሰላለመሆኑ፤ መቃወሚያ መቅረብ ያለበት ክርክሩን ሰምቶ ውሳኔውን ለሰጠው ፍ/ቤት ሰለመሆኑ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 Download Cassation Decision

 • 115963 civil procedure/ evidence law/ expert testimony/ weighing evidence

  በክርክር ሂደት ላይ ፤ የቀረቡት የባለሙያ አሰተያየቶች ተቃራኒ ይዘት ካላቸው ፤ ግልፅ መሰፈረት እና ምክንያት በሌለበት አንደኛውን ተቀብሎ ሌላውን ውድቅ ማደረግ ተገቢ ሰላለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 250 እና 136(1) Download Cassation Decision

 • 115981 contract law/ donnation/ invalidation of contract

  የስጦታ ዉል ውስጥ ተቃራኒ የሚሆን ቃል ከሌለ በቀር ስጦታ ከተደረገ በኋላ ልጅ መወለዱ ስጦታውን ለመሻር ምክንያት የማይሆን ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2450 Download Cassation Decision

 • 116038 labor law dispute/ scope of application of labor proclamation/ managers/ period of limitiation

  አንድን ሰራተኛ የሥራ መሪ ነው ሊባልበት ስለሚቻልበት አግባብ፡- የሥራ መሪን በተመለከተ ክርክር ሲነሳ ተግባራዊ ሊሆኑ ስለሚገባቸው ህጎች፡- የስራ መሪ የሚያቀርባቸው የመብት ጥያቄዎች ቀሪ ስለሚደረጉበት የይርጋ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀፅ 2(!)፣ 3(2(ሐ) የፍ/ሕ/ቁ.1677(1)፣1845፣2512፣2593 Download Cassation Decision

 • 116119 Family law/ filiation/ paternity/ contestation

  በአባት በኩል ያለን መወለድ መቃወም የሚቻለው የልጁ አባት ነው ተብሎ በህግ ግምት የሚሰጠው ሰው እሱ የሞተ ወይም ችሎታ ያጣ እንደሆነ ከተወላጆቹ አንዱ የመካድ ክስ በማቅረብ መቃወም የሚችል ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/1992/አንቀጽ 167፣174 እና 179 Download Cassation Decision

 • 116154 civil procedure/ jurisdiction/ federal courts/ labor dispute/ labor board

  የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በተደራጀባቸውና ባልተደራጀባቸው ክልሎች ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የሚነሱ ይግባኞች መቅረብ ያለባቸው ከፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጋር አቻ ስልጣን ላላቸው በየክልሉ ላሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎቶች ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 154 የዒ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/2/ አዋጅ ቁ. 322/95 Download Cassation Decision

 • 116405 criminal law/ criminal procedure/constitution/ / speedy trial/ amendment of charge

  በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ሥርዓት ህግ መሰረት ክስ እንዲሻሻል መፍቀድ የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብትን የሚያጣብብ ነው የሚባል ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 188፣119 ኢፌድሪ ሕግ መንግስት አንቀጽ 20(1) Download Cassation Decision

 • 116950 Family law/ minor/ sale of immovable property

  እድሜው ያልደረሰ ልጅ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ የሚያስችል የሞግዚት ስልጣን ይሰጠኝ ጥያቄ ፍ/ቤቶች የህፃንን መብትና ድህንነት ቅድሚያ እንዲሰጠው በማደረግ ሲወሰኑ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቀረበውን መሰረታዊ ጥያቄ እና አማራጭ መፍትሔ መኖሩን አለመኖሩን በማጣራት መወሰን ያለበት ሰለመሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግሰት 36 (2) ፣ ፍ/ብ/ሕ/ቁ 280 እና 289(1) የቤተሰብ ህግ አዋጅ 213/1992 አንቀፅ 43 Download Cassation Decision

 • 116961 contract law/ evidence law/ loan/ payment of loan

  በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2472 ላይ ገንዘብ ሰለመከፈሉ ማሰረጃን በተመለከተ የተደነገገው ፤ ከብድር ውጭ ለሆነ ግንኙነት ከተከፈለ ገንዘብ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚነት የሌለው ሰለመሆኑ ፤ Download Cassation Decision

 • 117036 contract law/ contract of sale/ delivery/ force majuer/ damage

  አንድ ዕቃ ለመሸጥ /በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ለማስረከብ/ የተዋዋለ ወገን ከዕርሱ አቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ውሉን መፈጸም ባልቻለ ጊዜ በቅድሚያ ለዚሁ ስራ የተቀበለውን ገንዘብ ከወሰደበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ከመመለስ ውጭ ውሉን ባለመፈጸሙ ምክንያት ለደረሰው ኪሳራ እንዲከፍል የማይገደድ ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2356/1/ Download Cassation Decision

 • 117070 labor law dispute/ salary/ commission

  ተዋዋይ ወገኖች በስራ ውል ስምምነታቸው በግልፅ ኮሚሽንን የደሞዝ አካል አድርገው እስከተዋዋሉ ድረስ ቅራኔ በተነሳ ሰዓት ኮሚሽንን እንደ ደመወዝ አይደለም በማለት መውሰድ ተገቢ ስላለመሆኑ አዋጅ ቁ.377/1996 አንቀፅ 53(2(መ) Download Cassation Decision

 • 117345 law of inheritance/ things making up inheritance

  የአንድ ሰው መብትና ግዴታ ለተወላጆቹ በውርስ ሊተላለፍ የሚችለው በሟቹ ምክንያት የሚቋረጡ ካልሆነ በቀር ሟቹ በሞተበት ቀን የነበሩት መብቶችና ግዴታዎች ስለመሆናቸው፣ Download Cassation Decision

 • 117506 extracontractual liability/ joint and several liability/ indemnification

  በአንድ ሰው ላይ ለደረሰ ጉዳት ኃላፊነትን በሚጥሉ የተለያዩ የህግ ድንጋጌዎች ምክንያት ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎች ለጉዳቱ በአንድነትና በነጠላ ኃላፊ በሚሆኑበት ጊዜ ኃላፊ ከሆኑት ሰዎች አንዱ ብቻ ጥፋት የሰራ እንደሆነ በመጨረሻ የተወሰነውን ዕዳ እርሱ እራሱ ብቻ የመቻል ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2157 Download Cassation Decision

 • 117608 insurance law

  የመድን ውል ሽፋን ተጠቃሚ ለተገለገለበት ጊዜ በውሉ መሰረት የአርቦን ክፍያ መክፈል ያለበት ስለመሆኑ ፤ የአርቦን ክፍያ በአንድ ወር ጊዜ ባለመጠየቁ ውሉ እንደተቋረጠ ስለሚቆጠር ክፍያውን የመጠየቅ መብት፤ ጉዳት ከደረሰም ኃላፊነት ለመውሰድ አይገደድም ከሚል መደምደሚያ ለብድር (ዱቤ) ላይ ለተመሰረተ ግንኙነት ተፈፃሚ ሰላለመሆኑ ፤ የን/ሕ/ቁ 666 (4) Download Cassation Decision

 • 117735 civil procedure/ execution of judgment

  የጋራ ወራሾች ሀብት በሆነ ንብረት ላይ ከእንዳንዱ የጋራ ባለሀብቶች ላይ ገንዘብ የመጠየቅ መብት ያላቸው ሰዎች የባለድርሻውን ድርሻ ለመያዝ የሚችሉ ስለመሆኑ፣ በውርስ ሀብት እና የጋራ ወራሾች ያልተከፋፈሉ የውርስ ንብረት መካከል ስላለው ልዩነት የፍ/ሕ/ቁ. 943፣1052፣1053፣1060 እና 1260 Download Cassation Decision

 • 117754 civil procedure/appeal/ papuer/ court fee

  " Download Cassation Decision

 • 117819 civil procedure/ jurisdiction/ urban land law/ lease

  የከተማ ቦታን በሊዝ በመጫረት ጨረታውን በማሸነፍ የሊዝ ውል የተፈጸመ እንደሆነ ይህን የውል ግንኙነት ለመዳኘት የሚችለው ፍርድ ቤት ስለመሆኑ፣ የሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 የፍ/ሔር/ሕ/ቁ. 1731፣1808/2/ Download Cassation Decision

 • 117862 labor law dispute/ duty to report for work

  አንድን ሰራተኛ በስራ ላይ አልተገኘም ማለት የሚቻለው የስራ ውሉ ፀንቶ እስከቆየበት ጊዜ ድረስ ብቻ ስለመሆኑ፡- አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 27 (1) (ለ) Download Cassation Decision

 • 117877 criminal law/ appeal/ sentencing

  የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ መመሪያ መሰረት በማድረግ በማረም የሚጠው ውሳኔ ከተጠየቀ ዳኝነት ውጭ ተሰጥቷል የሚያስብል ስላለመሆኑ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ.2/2002 አንቀፅ 21(1) (ሀ) ፣ ወ/ሕ/ቁ 184(!0 (ለ) እና 194 (1) (ለ) Download Cassation Decision

 • 117907 civil procedure/ execution of judgment

  አንድ ጠበቃ በገባው ውል መሰረት እስከ መጨረሻው ድረስ ጉዳዩን ከተከታተለና ከሙያው አንጻር እውቀትና ጥረቱን ተጠቅሞ አገልግሎት ከሰጠ የተፈለገው ውጤት ባለመምጣቱ ብቻ የተሟላ አገልግሎት አልሰጠም ሊሰኝ የማይችል ስለመሆኑ እና በውሉ መሰረት የተስማሙበትን የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ ቀሪ ሊያደርገው የማይችል ስለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 118084 criminal law/ breach of trust

  በእምነት ማጉደል ወንጀል ላይ የተቀመጠው ያልተገባ ጥቅም የማዋል ሓሳብ መርሕ ፤ ለከባድ እምነት ማጉደል ወንጀልም ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ ፤ ወ/ሕ/ቁ 675(3) እና 676 (2) (ሀ) Download Cassation Decision

 • 118105 law of inheritance/ period of limitation

  የተሰጠ ወራሽነት ማረጋገጫ የተሰረዘ ከሆነ ፤በይግባኝ ካልተሻረ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተሰጠ የውርስ ባለቤትነት ውሳኔ የሰረዝልኝ ጥያቄን ክርክር ስምቶ መወሰን ያለበት እንጂ በቀድሞ ያልተነሳ የይርጋ ተቃውሞ በመቀበል ጥያቄው ውድቅ ሊደረግ የማይገባ ሰለመሆኑ ፤ Download Cassation Decision

 • 118130 criminal law/ constitution/ criminal procedure/ juvenile offender/

  ወንጀል ፈጽሞ የተከሰሰን ህፃን ደህንነት ሊጠበቅበት ሥለሚችልበት አግባብ ለአዋቂ ጥፋተኞች የተደነገጉት መደበኛ ቅጣቶች ለወጣት ወንጀል አድራጊዎች ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ስለመሆኑ፡- የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህግ መንግሥት አንቀጽ 36 (2)፣ የህፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ 3(1)፣ የአፍሪካ የህፃናት መብቶች ደኅንነት ቻርተር በአንቀጽ 4 (1) የወንጀል ህግ አንቀጽ 53 (1)፣ 157፣ 168 የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ 171፣180 Download Cassation Decision

 • 118191 property law/ rural land law/ donation/ Amhara rural land law/

  የገጠር መሬት የይዞታ ባለመብት የሆነ በሙሉ ፍቃድ የሰጦታ ውል አድርጎ እንዲሁም ውሉ በሚመለከተው አካል ከተመዘገበ በኃላ ፤በውሉ ላይ ያልተመዘገበ ቅድመ ሁኔታ በመዘርዘር ውሉ ፈራሽ እንዲሆን በማለት የሚቀርብ ጥያቄ ውልንም ህግንም የሚቃረን መሆኑ የአ/ብ/ክ/መ አዋጅ 133/98 አንቀፅ 15 እና 17 ፤ የአ/ብ/ክ/መ ደንብ ቁጥር 51/99 እና የፍ/ሕ/ቁ 2436 ፣2437 ፣2438 ፣2439 Download Cassation Decision

 • 119159 criminal law/ criminal guilt/ conccurrence

  ከአንድ የወንጀል ድርጊት በኃላ ተከታትሎ የተፈፀመ ድርጊት ፤አንድን ወንጀል ከግብ ለማድረስ ሲል ተከታትሎ የተደረገ ድርጊት ከቀድሞ አሳቡና ሊደርስበት ከቀደው ግብ ጋር የተያያዘ በዋናው ወንጀል የሚጠቃለል ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ የሚጣራበት አግባብ፤ ዓ/ሕግ ባስከፈተው የይግባኝ መዝገብ ላይ መ/ሰጭ ሕግን መሰረት አድርጎ የሚቀርበው ክርክር ተቀባይት ሊያጣ የማይገባው ሰለመሆኑ፤ ወ/ሕ/ቁ 88(3) Download Cassation Decision

 • 119500 criminal law/ attempt/ sentencing/ extenuating circumstance/ sentencing guideline

  በሙከራ ደረጃ ለተፈፀመ ወንጀል ቅጣት እንደሚቀንስ በግልፅ በመመሪያ ቁ.2/2006 ላይ ባይደነገገም ነገር ግን በወንጀል ህጉ ቅጣትን በመሰለው እንዲያቀል ለፍ/ቤቱ በተፈቀደበት ሁኔታ መሰረት ቅጣትን አቅሎ ሊወሰን የሚችል ሰለመሆኑ ፤ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ.2/2006 አንቀፅ 24 ፣ የወ/ሕ/ቁ 31 እና 180 Download Cassation Decision

 • 119557 property law/ rural land law/ Amhara land law/ usufruct

  የመሬት የይዞታ መብት ያለው ሰው ፤በይዞታው ላይ የአላባ የመጠቀም መበት መስጠቱ በሌላ ጊዜ ይዞታውን በስጦታ የማሰተላለፍ መብቱን የማይገድብ ሰለመሆኑ ፤ የአ/ብ/ክ/መ/መሬት አጠቃቀም አዋጁ 133/98 አንቀፅ 1፣7 Download Cassation Decision

 • 119563 extracontractual liability/ period of limitation/ possessory action

  በመሬት ይዞታዬ ላይ ጉዳት ደርሶብኛል በማለት የሚቀርብ ክስ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለበት ሰለመሆኑ ፍ/ሕ/ቁ 2143 Download Cassation Decision

 • 119639 labor law dispute/ termination of contract of employment/ breach of duty by employee

  የአሰሪውን ትእዛዝ አልፈፀመም ተብሎ የስራ ስንብት ያደረገ አሰሪ ትእዛዙ ያለመፈጸሙን የማስረዳት ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13 Download Cassation Decision

 • 119694 labor law dispute/ civil procedure/ denial/ payment

  አሰሪ የተጠየቀን የስራ ስንብት ክፍያን በተመለከተ አጠቃላይ ተቃውሞ አቀርቦበት እያለ ፤ ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ሰሌቱን በተመለከተ አልተቃወመም በሚል በመተርጎም በሰራተኛው የተጠየቀን የስንብት ክፍያ ዳኝነት ሙሉ በሙሉ በመወሰን የሚሰጥ ዳኝነት ተገቢ ስላለመሆኑ ፤ፍ/ቤቱ በሕጉ አግባብ አስልቶ መጠኑን ሊወሰን የሚገባ ሰለመሆኑ ፤ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀፅ 40 (1 እና 2) Download Cassation Decision

 • 119709 civil procedure/ jurisdiction/ Amhara/ appeal procedure

  ከፊል የዳኝነት ሰልጣን ላለው አካል በፍሬ ነገር ደረጃ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ መሆኑ በግልፅ ተቀምጦ እያለ፤ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በሕግ አተረጎጎም ረገድ ብቻ የተሰጠውን ስልጣን በማለፍ ማሰረጃን በመመዘን በፍሬ ነገር ላይ የሚሰጠው ድምዳሜ ሰርዓቱን የተከተለ ስላለመሆኑ ፤ የአ/ብ/ክ/መ/ መገናኛ ብዙሀን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ 200/2005 አንቀፅ 13(2) Download Cassation Decision

 • 120841 law of inheritance/ minors/ period of limitation/ certifcate of heirs

  አንድ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ወራሽነት መብቱን ለአካላ መጠን ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 15 ዓመት ባለው ጊዜ ውሰጥ የውርሱን ንብረት ለመጠየቅ በይርጋ የማይታገድበት ስለመሆኑ ፤ ፍ/ብ/ሕ/ቁ 198 ፣ 1000(2) የተሰጠ ወራሽነት ማረጋገጫ የተሰረዘ ከሆነ ፤በይግባኝ ካልተሻረ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተሰጠ የውርስ ባለቤትነት ውሳኔ የሰረዝልኝ ጥያቄን ክርክር ስምቶ መወሰን ያለበት እንጂ በቀድሞ ያልተነሳ የይርጋ ተቃውሞ በመቀበል ጥያቄው ውድቅ ሊደረግ የማይገባ ሰለመሆኑ ፤ Download Cassation Decision

 • 120844 family law/ second wife/ common property

  የመጀመሪያ ሚስት በንብረትዋ ላይ ስምምነት ባላደረገችበት ፤ባል ሁለተኛ ሚስት ሲያገባ መቃወሚያ አላቀረበችም በማለት በንብረትዋ ላይም ስምምነት አድርጋለች በማለት በመደምደም ፤ሁለተኛ ሚስት እኩል እንድትካፈል በማለት የሚሰጥ ውሳኔ ህጋዊ ስላለመሆኑ Download Cassation Decision

 • 121063 labor law dispute/ termination of contract of employment/ pregnancy

  በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ በግልጽ በተቀመጡ ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር አንዲት ሰፍሰጡር ሴት ከወሊድ በኋላ አራት ወራት ውስጥ ከስራ ያለመባረር መብት ያላት ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 25፣27፣29/3/ እና 87/5//6/ Download Cassation Decision

 • 121387 civil procedure/ admission/ failure to deny/ summary procedure

  ፍ/ሥ/ሥ/ሕጉ በግልፅ ያልተካደ ፍሬ ነገር እንደታመነ ይቆጠራል የሚለው ድንጋጌ በልዩ ስርዓት( በአጭር ሁኔታ) ለሚመሩ ክርክሮች ላይ ጭምር ለቀረበ መልስ ላይም ተፈፃሚ የሚሆን ስለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 284 (ሀ) Download Cassation Decision

 • 122249 civil procedure/ pleading/ amendment of pleading

  " ከሳሽ ያቀረበው ክስ እና የክሱ ዝርዝር ይዘት የተለያየ ሆኖ የተገኘ ከሆነ ፤ ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ክሱ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በማዘዝ ፤የክርክሩን ሂደት መምራት ያለበት ሰለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 90(1) Download Cassation Decision "

 • 123056 property law/ government houses/ contract of rent/

  ማንኛውም የቀበሌ መኖሪያ ቤት የተከራየ ሰው የራሱ ቤት ከገነባ ወይም የጋራ ሕንጻ ቤት ከገዛ ወይም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲን ቤት ካገኘ ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት ቤቱን የለቀቁ ከሆነ ቤቱን ባለበት ሁኔታ ለአስተዳደሩ ማስረከብ ያለበት ስለመሆኑ፣ የአ.አ.ከ.አስተዳደር ባወጣው የመንግስት ቤቶች አስተዳደር መመሪያ ቁ. 3/2007 አንቀጽ 42/ሀ Download Cassation Decision

 • 124618 civil procedure/ execution of judgment

  በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ተይዞ የሚሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሁለት /ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች በህብረት የያዙት እና ያልተከፋፈሉት በሆነ ጊዜ ከተከፋዮቹ አንዱ ንብረቱን ለመግዛት በጨረታ ተወዳዳሪ ሆኖ የቀረበ እንደሆነ የፍርድ ባለእዳው እንደቀረበ ተቆጥሮ የተቀዳሚነት መብት የሚሰጠው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 443፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 126/1/፣ 1386-1409 Download Cassation Decision

 • 125004 labor law dispute/ transfer/ absence from work

  የዝውውር ውሳኔን ተከትሎ ሰራተኛው ለአምስት የሰራ ቀናት የሰራ ቦታ ላይ አልተገኘም በማለት የማሰናበት እርምጃ ተገቢነት ለማጣራት ፤ ከነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም ሰራተኛው የሰራ ቦታ ላይ መገኘት ከሚችልበት ሁኔታ አንፃር እንዲሁም ከቀረበው ማስረጃ አንፃር በመመዘን የሚወሰን ስለመሆኑ ፤ Download Cassation Decision

 • 125778 labor law dispute/ termination of contract of employment/ disciplinary measures

  አሰሪ ሰራተኞችን ከማሰናበቱ በፊት በትክክል አጣርቶ እርምጃ መውሰድ ሲገባው ፤ክርክር ከተጀመረ በኃላ ከስንብት ደብዳቤ ሌላ ደብዳቤ መፃፉ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁን ዓላማ እና መንፈስ የማያሟላ ሰለመሆኑ ፤ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 91 (1) (3) አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 (1) (ሸ) ( ቀ) Download Cassation Decision

 • 127154 labor law dispute/ public pension/ lien/ attachement

  ለጡረታ አፈፃፀም ተብሎ የመንግሰት ሰራተኛን የግል ማህደር በኤጀንሲው እንዲላክ ተጠይቆ፤ሰራተኛው የመንግስት ብረት አልመለሰም በማለት ማህደር አልክም ማለት ህጋዊ ሰላለመሆኑ ፤ የጡረታ አበል የማግኘት መብት የዕዳ መያዣ ሊደረግ ወይም በውርስ ወይም በማናቸውም መንገድ ሊተላለፍ የማይችል ሰለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 345 /97 አንቀፅ 47 (2) ፣ 44 እና 55 (2) Download Cassation Decision

 • 131863 criminal law/ criminal procedure/ constitution/ bail right

  በወንጀል ተጠርጥሮ በህግ ከለላ ስር የሚገኝን ተጠርጣሪ በዋስትና የመለቀቅ ጥያቄ ባነሳ ጊዜ ተጠርጣሪው በከተማው ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ /የመታወቂያ/ አድራሻ የለውም በማለት የዋስትና መብቱን መከልከል ህገ መንግስታዊ ስላለመሆኑ፣ አንቀጽ 19/6/፣ 25 እና የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 69/ሀ/ Download Cassation Decision

 • 134228 criminal law/ criminal procedure/ bail right

  የዋስትና መብት የሚነፈግባቸው ምክንያቶች ፍርድ ቤቶች ከተለያዩ ሁኔታዎች አንፃር እየተመለከቱ ሊመዝኗቸው የሚገባቸው ስለመሆኑ አንድ ተከሣሽ የዋስትና መብት ቢከበርለት ግዴታውን የሚፈጽም የማይመስል ነው ተብሎ ግምት የሚወሰደው በቂና ህጋዊ ሊባሉ በሚችሉ ምክንያቶች ሊሆን እንደሚገባ፤ እንዲሁም ምክንያቶቹ በቂና ህጋዊ ናቸው የሚለው ጉዳይ ከተለያዩ ከባባዊ ሁኔታዎችና ከጉዳዩ ልዩ ባህርይ አንፃር ፍርድ ቤቱ ሊገነዘበው የሚችለው ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባ ስለመሆኑ የወ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 67(ሀ) Download Cassation Decision

 • 88135 insurance law/ liability of insurers

  የመድን ሥራ የሚሰሩ የመድን ኩባንያዎች በመድን ፖሊሲ ውስጥ ፖሊሲውን ተጠያቂነትን አያስከትልም ወይም በፖሊሲው መሰረት የካሳ ክፍያ ጥያቄ መነሻ የሆነው ክስተት ከደረሰ በኃላ የተወሰነ ድርጊት ከተፈፀመ ወይም ሳይፈፅም ከቀረ ኃላፊነቱ ቀሪ ይሆናል የሚል የውል ሁኔታ ተፈፃሚነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 559/2000 በአንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 1 Download Cassation Decision

 • 88542 criminal law/ fine/

  ፍ/ቤቶች የገንዘብ መቀጫን ሲወስኑ ከግምት እና ግንዛቤ ውሰጥ ሊያስገቡዋቸው የሚገቡ የተከሳሽ ግላዊና የወንጀሉን ሁኔታዋችን በማገናዘብና ፤ በወንጅል ህጉ እና በቅጣት መመሪያው ላይ የተቀመጡ መሰፈርቶችን መሰረት በማድረግ መወሰን ያለባቸው እንጂ በደፈናው የገንዘብ መቀጮ መወሰን ተገቢ ሰላለመሆኑ ፤ የወ/ሕ/ቁ 88 /2/ እ 90 90 (2)፤ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2000 Download Cassation Decision

 • 98771 labor law dispute/ scope of application of labor proclamation/ employment agency

  የግል አሰሪና ሠራተኛ (ስራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ) እና በሰራተኛ የሚነሳ ማንኛውም የስራ ክርክር የሚፈታው በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 632/2001 አንቀጽ 4 Download Cassation Decision