98348 contract/ performance bond

ለመልካም ሥራ አፈጻጸም ለዋስትና የተያዘ ገንዘብ ውሉ እንደውሉ ሳይፈጸም ሲቀር ዋስትና አስያዡ የተያዘውን ገንዘብ በውል ለተጎዳው ወገን መክፈል የሚገባው ስለመሆኑ ለመልካም ስራ አፈፃፀም የሚሰጥ ዋስትና ዓይነተኛ ዓላማው በተሰራው ነገር ጉዳት የደረሰበት ተዋዋይ ወገን በገንዘቡ ረገድ ለመካስ ስለመሆኑ ፍ/ሕ/ቁ. 1815

 

ys¼m¼q$¼98348

¬HúS 18 qN 2008 ›¼M


 

xmLµÓCÝ.1ኛ አቶ ዘሪሁን የኔነህ ቀረቡ

2ኛ የአቶ የኔነህ ጨርቆሴ ህጋዊ ወረሾች

1.  አቶ ታረቀኝ የኔነህ

2.   ,,  የኃላሸት የኔነህ አልቀረቡም

3.   ,,  ዘሪሁን የኔነህ

t-¶Ý( ሀዋሣ ዩኒቨርሲቲ ነገረ ፈጅ እንግዳወርቅ ጌታቸው ቀረቡ

mZgb#N mRMrN tk¬†N FRD s_tÂLÝÝ

F R D

ጉዳዩ የመልከም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን አመልከቾች ባሁኑ ተጠሪ እና በዚህ መዝገብ የክርክሩ ተከፋይ ባልሆኑ 1ኛ ወ/ት ንሰሐ ወርቅህ 2ኛ ዳሽን ባንክ ላይ ባቀረቡት ክስ መነሻነት ነው፡፡ የክሱ ይዘትም በዚህ መዝገብ የክርክሩ ተከፋይ ያልሆነችው ወ/ሪት ንሰሐ ወርቅነህ ከአሁኑ ተጠሪ ሀዋሣ ዩኒቨርሰቲ ጋር በተፈራረሙት የበሰለ ምግም አቅርቦት ውል 1ኛ ተከሳሽ የነበረቸው ወ/ት ንሰሐ ቀርቅነህ ለመልከም አፈፃፀም ዋስትና 3ኛ ተከሳሽ ከነበረው የዳሽን ባንክ እንዲሰጣት ጠይቃ፤ 3ኛ ተከሳሽም ለዋሰትና የሚበቃ ንብራት እንድታቀርብ በመጠየቁ የአሁኑ 1ኛ አመልከች በስሙ ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤትና የሰሌዳ ቁጥር 3-42314 አይሱዙ የጭነት መኪና እንዲሁም 2ኛ አመልከች የመኖሪያ ቤት በመያዣ እንዲያዝ በመፍቀዳቸው ሦስቱም ንብረቶች በብር 658,568.00 ተገምተው ህዳር 15 ቀን 2007 ዓ/ም እ/ኤ/አ/ በተፈረመ የመያዣ ውል ለ3ኛ ተከሳሽ ሰጥቷል፡፡ 2ኛ ተከሳሽ (የአሁኑ ተጠሪ) አቅርቦቱ የጥራት ደረጃውን አልጠበቀም በሚል የአቅርቦት ውሉን ከታህሳስ 13 ቀን 2000 ዓ/ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ አቋርጧል፡፡  ውሉ በተቋረጠ በ4ኛ ቀን 2ኛ ተከሳሽ ቀደም ሲል በጨረታው 2ኛ የወጣውን ተወዳዳሪ በ1ኛ ተከሳሽ ምትክ በመተካት ውል መፈጸሙ አቅርቦቱ በግለሰቡ አማካኝነት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የ1ኛ ተከሳሽ የአቅርቦት ውል በመቋረጡ በ2ኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) ላይ የደረሰ ኪሳራ ወይም ተጨማሪ ወጪ ከለ ለ1ኛ ተከሳሽ ተከፋይ ከሚሆን የአቅርቦት ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወጪው ከተካካ በኃላ 3ኛ ተከሳሽ ለሰጠው የብር 658,568 .00 ዋስትና በመያዣነት የተያዙ ንብረቶች እነዲለቀቅላቸው


ጥያቄ አቅርበው ኪሳራው አስልቶ ከአንደኛ ተከሳሽ ተከፋይ ሂሳብ ተቀነሽ በማድረግ ለራሱ ገቢ ካደረገ በኃላ ንብረቶችን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ የአቅርቦት ውሉ በ2ኛው ተጫራች አማከይነት ወዲያውኑ በመቀጠሉ ንብረቶቹ በመያዣነት እንደተያዙ ሊቀጥሉ ወይም የዋስትናውን ገንዘብ ሊወረስ የሚችልበት አግባብ ባለመኖሩ ዋስትናው ቀሪ ሆኖ ንብረቶቹ እንዲለቀቁ በ3ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኙት የበለቤትነት ሰነዶች ተመለሽ እንደሆኑ እንዲወስንላቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

 

በስር ፍርድ ቤት ተከሳሾች የነበሩ የአሁኑ ተጠሪ ጨምሮ መልስ አቅርቦዋል፡፡ 1ኛ ተከሳሽ የነበረቸው የሚትከሰስበት ምክንያት እንደሌላ፤ ውሉ በ2ኛ ተከሳሽ ፍላጎትና ውሳኔ ተቋርጠዋል፤ በጨረታው አሸናፊ የሆነውን 2ኛ ተጫራች የነበረው ተተክቶ ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር የውል ግዴታ ገብቶ ሥራን ቀጥሏል፡፡ 2ኛ ተከሳሽ የሚጠይቀው ዕዳ የለውም መያዣው ሊለቀቅ ይገባል የሚል ይዘት ያለው መልስ ያቀረበች ሲሆን፤ 2ኛ ተከሳሽ (የአሁኑ ተጠሪ) ደግሞ ከአመልካች ጋር የውል ግንኝነት የሌለው በመሆኑ ተጣምሮ መከሰስ እንዳልነበረበት ክሱን ንብረቱን በያዘው አካል  ላይ ብቻ መቅረብ ያለበት ስለመሆኑ በፍሬ ጉዳዩም የምግብ አቅርቦት ውሉ የተቋረጠው በ1ኛ ተከሳሽ ግዴታ ያለመወጣት ምክንያት በመሆኑ ተጠሪ ለተጨማሪ ኪሳራ ተደርጓል፡፡ መያዣው ሊመሰስ አይገባም የሚል ክርክር አቅርቦዋል 3ኛ ተከሳሽ የነበረው የዳሽን ባንክ 1ኛ ተከሳሽ የውል ግዴታቸው ባለመወጣታቸውን በገባው ውል መሠረት የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ብር 658,568.00 ለሐዋሳ ዩኒቨርሰቲ ገቢ አደርገዋል፡፡ መያዣው ሊለቅ አይችልም፡፡ ክሱ ውድቅ ሊደረግ ይገበል የሚል ይዘት ያለው መልስ አቅርበዋል፡፡

 

የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ በመጀመሪያ ደረጃ የቀረቡ መቃወሚያዎች ውድቅ አድርጓል፡፡ በፍሬ ጉዳዩም 2ኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) 1ኛ ተከሳሽ በውሉ መሠረት ግዴታዋን አልተወጣችም በሚል ያፈረሰው በመሆኑ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ሁኔታ መመለስ የሚገበቸው ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ውሉን ለመፈጸም የተሰራው ሁሉ ቀሪ ሆኖ ውጤት ስለማይኖረው በፍ/ሕ/ቁ. 1815 መሠረት አመልከቾች የገቡት ዋስትና ቀሪ ይሆናል፡፡ 2ኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) ውሉን እስከ ፈረሰ ድረስ ከ1ኛ ተከሳሽ አለኝ የሚለው ቀሪ ሂሣብ ከለው በህግ ከመጠየቅ ውጭ ለዋስትና ግዴታ የተገባው ንብረት ለ3ኛ ተከሳሽ ሊከለከል አይገበም፡፡ የምግብ አቅርቦት ውሉ ሲቋረጥ መያዣው ይቋረጣል፡፡ 3ኛ ተከሳሽ ገንዘቡን መክፈል አልነበረበትም፡፡ 3ኛ ተከሳሽ ለመልካም አፈፃፀም የከፈለው ገንዘብ የማስመለስ መብቱ ተጠብቆ ከአመልካቾች የተያዙ መኖሪያ ቤቶችና መኪና የባለቤትናት ማረጋገጫ ሰነዶች ጭምር ይመለስ በማለት ወስኗል፡፡ የአሁኑ ተጠሪ እና በስር ፍርድ ቤት 3ኛ ተከሳሽ የነበረው ዳሽን ባንክ እንደቅደም ተከተላቸው በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 63309 እና 63860 ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ቅሬታ አቅርበው ተቀባይነት አላገኘም፡፡ የአሁኑ ተጠሪ እና በስር ፍርድ ቤት 3ኛ ተከሳሽ የነበረው


ዳሽን ባንክ በስር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡት ቅሬታ ተቀበይነት በማግኘቱ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር የሃዋሳ ዩኒቨርሰቲ በራሱ አነሰሽነት ውሉን ለማቋረጥ የሚችል ስለመሆኑ በሕግ መብት ያለው ቢሆንም እንደ ውሉ ያልፈጸመው ወገን ማን ነው? የሚለውን ክርክር ባስነሳ ጊዜ እና እንደውሉ ባለመፈፀሙ ምክንያት የደረሰው የጉዳት ኪሣራ ምን ያህል ነው? የሚለው ሁሉ የመረጋገጥ ግዴታ ስላለበት በዚህ ጭብጥ መሰረት 1ኛ ተከሳሽ ባለችበት የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ተሰምቶ ሊወሰን እንደሚገባ፤ በዚህ ክርክር ውጤት መሠረት በማድረግ የዳሽን ባንክ ለዩኒቨርሲቲው የከፈለው የክፍያ መጠን አግባብ መሆኑና አለመሆኑን ታይቶ አሰፈላጊው ዳኝነት እንዲሰጥበት በጭብጥ የተያዙ ነጥቦች በክርክር እና በማስረጃ መሠረት ተለይቶ ከመታወቁ በፊት በመያዣ የተያዙ ንብረቶች ሊለቀቁ አይገበም በማለት ጉዳዩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343 (1) መሠረት ተጠርቶ እንዲወሰን ለሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት መልሶታል፡፡

 

የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የኮ/መ/ቁ. 67820 በማንቀሰቀስ ጉዳዩ በድጋሚ የተመለከተው ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ ባለመቅረቧ ክርክሩ በሌለችበት እንዲቀጥል አደርጓል፡፤ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ 1ኛ ተከሳሽ ከተጠሪ ጋሪ በፈፀመችው የምግብ አቅርቦት ውል ከ11/2/2000 እስከ 11/12/2000 ዓ/ም ለ10 ወር ጊዜ ለማቅረብ የተስማማች ቢሆንም 2 ወር አቅርቦት ከፈጸመች በኃላ በማቋረጧ ተጠሪ ውሉን በ14/04/2000 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ ማቋረጡን፤ ለውሉ ማቋረጥ ምክንያትም በጥራትና በጊዜ መቅረብ ባለመቻሉ ስለመሆኑ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ያሰያል፡፡ 1ኛ ተከሳሽ ቀርባ አልተከራከረችም በመሆኑም 1ኛ ተከሳሽ ለውሉ መቋረጥ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ማረጋገጥ ተችሎአል፡፡ ሁለተኛ ጭብጥ በተመለከተ የጉዳት ከሳ ከደረሰው ጉዳት አንፃር መታየት ያለበት ስለመሆኑ ተጠሪ የገባው ሁለተኛ ውል በመጀመሪያ ውል ከተቀመጠው ዋጋ በልዩነት 1,347,403.02 ተጨማሪ ወጭ የሚጠይቀው መሆኑ መከራከሩን፣ አቅርቦት በመጠን ሲያንስ ሂሳቡ ሲቀነስ እንደነበር ውሉ ከመቋረጡ በፊት የደረሰው ኪሳር ዝርዝር አለመያዙን ውሉ በመቋረጡ ምክንያት የደረሰ ጉዳት ሲመዘንም ከ14/4/2000 እስከ 17/4/2000 ዓ/ም በለው ጊዜ የደረሰ ኪሳራ መሆኑን እንደሚያሳይ ለ8 ሺህ ተማሪዎች ለዳቦ ግዥ ለ3 ቀናት ያወጣው የኪሳራ ልክ 96,000 ብር መሆኑ እንዳረጋገጠ፤ 3ኛ ጭብጥ በተመለከተ 2ኛ ተከሳሽ የደረሰበት የጉደት መጠን አስልቶ ክስ ከሚያቀርብ በቀር አጠቃላይ ለውሉ አፈፃፀም የተያዘው መብት እንደሌለው፤ 3ኛ ተከሳሽ (ዳሽን ባንክ) የሚፈጸመው ክፍያም ውል ባለመፈፀሙ የደረሰ ጉዳት ታሳቢ የሚያደረግ እንጂ ጉዳት ቢደርስም በይደርስም ለመክፈል ይገደዳል ማለት አለመሆኑን፤ በዚሁም በሁለተኛ ጭብጥ በተረጋገጠው መሰረት 3ኛ ተከሳሽ ለ2ኛ ተከሳሽ ሊከፈል የሚገባው ብር 658,568 ሳይሆን ብር 96,000 መሆኑን፤


አራተኛው ጭብጥ መያዣው ከላይ በተመለከተው የካሣ ልክ ያረፈበት በመሆኑ ይህ ክፍያ ሳይፈፀም መያዣ ሊለቀቅ የሚችልበት አግባብ የለም በማለት ወስኗል፡፡

 

የአሁኑ ተጠሪ በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር ከመረመረ በኃላ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ አቅረቢ የዋጋ ልዩነት መኖሩን አልተከደም፡፡ በስር 1ኛ ተከሳሽ የነበሩ አቅረቢ ለ8 ወራት ቢያቀርቡ ችግሩ አይከሰትም ነበር፡፡ 2ኛ ተጫራች የነበረው ሌላ ውድድር ሳይደረግ የአቅረቦት ውል እንዲቀጥል የተፈቀደው የ8,000 ተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ማሟላት ፋታ የማይሰጥ ነው፡፡ የፌዴራል መንግስት የግዥ አዋጅ መመሪያ ይዘት መረዳት የሚችለው በአቅራቢ ችግር ምክንያት ውሉ በመቋረጡ ሊከሰት የሚችለው ተጨማሪ ውጭ /ጉዳት/ መሸፈን የሚገበው አቅረቢ መሆኑንና ለዚህም ለውሉ መልከም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለደረሰው ጉዳት መተኪያ ሊውል የሚችል መሆኑን ነው፡፡ ተጠሪ በውሉ መቋረጥ ምክንያት ደረሰብኝ የሚለው ጉዳት ብር 1,453,429.20 ነው፡፡ ይሁን እንጂ ክርክሩ ሲጀመረም ይሁን አሁን በይግባኝ ደረጃ ይህ ገንዘብ ሊከፈልኝ ይገበል የሚል ግልጽ ጥያቄ አላቀረበም፤ በግልጽ የጠየቀው ለመልከም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና የተያዘው ብር 658,568.00 ሊከፈለኝ ይገባል በማለት ስለሆነ በይግባኝ ባይ (ተጠሪ) ለደረሰው ጉዳት ሊከፈል የሚገበው ብር 96,000 ሳይሆን ለውሉ መልካም አፈፃፀም የተያዘ ጠቅላላ ገንዘብ ብር 658,568 ነው፡፡ አመልከቾች ይህንን ገንዘብ ለሥር 3ኛ ተከሳሽ (ዳሸን ባንክ)  ሲተኩ የዋስትና መያዝው ይለቀቅላቸው በማለት ወስኗል፡፡

 

የአሁኑ አመልከቾች በስር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሳኔ በመቃወም ጉዳዩን በሰበር ታይቶ እንዲመረመር እና እንዲለወጥ የሚጠይቅ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ችሎት እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ግራ ቀኙ በጽሑፍ ክርክር አደርጓል፡፡ የአመልካቾች ቅሬታ መሠረታዊ ይዘትም ውሉ የተቋረጠው በዩኒቨርሰቲው ድብቅ ምክንያት ነው፡፡ አቅርቦቱ የተቋረጠው ለ3 ቀን ብቻ በመሆኑ የጉዳት ከሳ ልክ መታየት ያለበት ከዚህ አንፃር መሆኑን እርግጠኛ ጉዳት መድረሱ ሳይረጋገጥ የጉዳት ከሳው ለመልከም አፈፃፀም ዋስትና የተያዘው በሙሉ እንዲከፈል መውሰኑ በአግባቡ አይደለም፡፡ የግዥ አዋጅና መመሪያ አፈፃፀም በአግባቡ አልታየም፡፡ ጉዳዩ ሰበር በመለሰው መሰረት አልተጣራም የሚል ነው፡፡ ተጠሪ በበኩሉ የአቅርቦት ውሉ የተቋረጠው በስር 1ኛ ተከሳሽ በነበረችው ምክንያት መሆኑን መረጋገጡን በመጀመሪያ እና ሁለተኛ አቅራቢ የዋጋ ልዩነት መኖሩን በተጠሪ  ተቋም ላይ ጉዳት ማድረስን ተረጋግጦ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ ሊጸና ይገባል በማለት ተከራክራዋል፡፡ የመልስ መልስም ቀርበዋል፡፡


የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም ግራ ቀኙ በጽሑፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ውሳኔ አግባብነት ከለው ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ እንዲሁም ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል፡፡ እንደመረመርነውም አመልካቾች እና ተጠሪ እያከራከራ ያለው መሰረታዊ ነጥብ ለመልካም አፈጻጸም የተሰጠ ዋስትና ሙሉ በሙሉ ገቢ ሊሆን የሚችልበት የህግ አግባብ መኖር ያለመኖሩን ነው፡፡ የአሁኑ አመልካቾች በተጠሪ ላይ የደረሰው ጉዳት የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዳጣራው የምግብ አቅረቦቱ ለ3 ቀን ብቻ ተቋረጦ የነበረ መሆኑን እየታወቀ የ8 ወር አቅርቦት መሰረት ተደርጎ የጉዳት ከሳው ሊሰላ አይገባም በሚል ምክንያት ነው፡፡ ተጠሪ በበኩሉ የመጀመሪያ አቅርቢ በውሉ በሠረት ባለ መፈፀምዋ ውሉን እንደተቋረጠ 2ኛ አቅረቢ ሲመረጥ ያቀረበው ዋጋ ከመጀመሪያው የአቅርቦት ዋጋ በግልጽ ጭማሪ ያለው በመሆኑ የሥር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንን በማጣራት ለመልከም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ገቢ እንዲሆን መወሰኑ በአግባቡ ነው የሚል ክርክር ማቅረቡን ተመልክተናል፡፡

 

በስር ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው ወ/ት ንሰሐ ወርቅነህ በገባችው ውል መሰረት የምግብ አቅርቦቱ በመጠን በጊዜ እና በጥራት ባለማከናወንዋ ተጠሪ ማስጠንቀቅያ በመስጠት ውሉን አቋርጦታል፡፡ በስር 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው ለውሉ መቋረጥ መነሻ አለመሆናን ያቀረበችው ክርክር ይሁን ማስተባበያ የለም ፡፡ በስር 3ኛ ተከሳሽ የነበረው ዳሽን ባንክ የመልከም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ሊሰጥ የተቻለው ምናልባት በስር 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው በውሉ ይዘትና መንፈስ አቅርቦቱን ከለከናወነች ተጠሪ ለሚደርስባት ጉዳት ለማከከሻ እንዲሆን ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው ለሁለት ወር ያህል ስታቀርብ በነበረችበት ጊዜ የነበረው ዋጋ እና ውሉ ከፈረሰ /ከተቋረጠ/ በኃላ በ2ኛ አቅራቢ የተጠየቀው ዋጋ ለወንዶ ገነት ዳን ኮሌጅ የ0.28 ሳንቲም ለሌሎች ከምፓሶች ደግሞ 0.39 ሳንቲም የዋጋ ልዩነት እንዳለው በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ጉዳይ ነው፡፡ የዋጋ ልዩነቱ በ8 ወራት ሂሣብ ስሌቱ ሲሰራ በድምሩ ብር 1,453,429.20 ስለመሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ከዚህ መረዳት የሚቻለው መጀመሪያ ከነበረው የአቅርቦት ውል 2ኛ አቅራቢ ዋጋ በመጨመሩ በተጠሪ ላይ ተጨማሪ ገንዘብ ወጭ ለማድረግ የሚገደድ ስለመሆኑ የሚካድ አይደለም፡፡ አመልካቾች አቅርቦቱ የተቋረጠው ለ3 ቀን ብቻ ነው የሚል ክርክር ያቀረቡ ቢሆንም በተጠሪ ላይ የደረሰው ጉዳት ለ8 ወራት የሚዘልቅ ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት ከተደረገው ክርክር መረዳት ተችሏል፡፡ ምክንያቱም የአሁኑ ተጠሪ ከ2ኛ አቅራቢ ጋር ያደረገው ውል ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጭ የጠየቀው በመሆኑ በስር 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው በውሉ መሰረት በጊዜ መጠን እና ጥራት የምግብ አቅረቦቱ ቢቀጥል ሌላ 2ኛ አቅራቢ በላሰፈለገ ነበር፡፡ በመሆኑም በተጠሪ ላይ ጉዳት አልደረሰም የሚለውን ክርክር በስር ፍ/ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ከተረጋገጠው አንጻር የህግ መሰረት ያለው ክርክር ሁኖ አላገኘነውም፡፡


በመሰረቱ ለመልካም ስራ አፈፃፀም የሚሰጥ ዋስትና ዓይነተኛ ዓለማው በተሰራው ነገር ጉዳት የደረሰበት ተዋዋይ ወገን በገንዘብ ረገድ ለመካስ ነው፡፡ ከስር ፍ/ቤት የክርክር ሂደት መገንዘብ እንደተቻለው በስር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው አቅራቢ በውሉ መሠረት ማቅረብ ባለመቻሏ ውሉ ፈርሷል፡፡ ተጠሪ ከሌላ ተዋዋይ የአቅርቦት ውል የፈፀመ መሆኑ ባይካድም በመጀመሪያ እና ሁለተኛ አቅርቦት ላይ በዋጋ ረገድ ከፍተኛ ልዩነት መኖሩን ግልጽ ነው፡፡ በአሁኑ ተጠሪ እና በስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበረችው ግለሰብ ተፈፀሞ የነበረው የምግብ አቅርቦት ውሉ ለ10 ወራት የሚቆይ እንደነበር፤ ይሁንና በ1ኛ ተከሳሽ ውል አለመፈፀም ምክንያት በ2ኛ ወር ተቋርጧል፡፡ በአሁኑ ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ የነበራችው እንደውሉ ባለመፈፀምዋ ከ2ኛ ተዋዋይ የአቅርቦት ውል ለማድረግ የተገደደ በመሆኑ ተጨማሪ ወጭ የጠየቀው ስለመሆኑ አላከራከረም፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት 3ኛ ተከሳሽ ከነበረው ዳሽን ባንክ የውል ማሰከበሪያ ገንዘብ ገቢ እንዲሆንለት መጠየቁ ውሉን መሰረት ያደረገ በደረሰው ጉዳት ልክ ሳይሆን በተሰጠው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ገንዘብ ብር 658,568,00 የተገደደ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህ አንፃር የስር ጠቅለይ ፍርድ ቤት በከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል መልካም የስራ አፈፃፀም ዋስትና ላይ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ማለትም ብር  658,568.00 ገቢ እንዲሆን መወሰኑ ውሉን በህጉ አግባብ ተፈፃሚ አደረጓአል ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸሙን አያሳይም፡፡ በእነዚህ ሁሉ ምክንያት የስር ጠቅላይ ፍርድ  ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደረሰ በተባለው ጉዳት ሊከፈል ይገባል በማለት የወሰነው 96,000 ብር በማሻሻል ለመልከም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና የተያዘው ብር 658,568.00 ገቢ እንዲሆን መወሰኑ በህጉ አግባብ ሆኖ በመገኘቱ የሚታረም የህግ ስህተት የለውም፡፡ በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል፡፡

 

 ው ሳ ኔ

 

1. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 89493 በ30/03/2006 ዓ/ም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 67820 በ 09/07/2005 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በማሻሻል የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል፡፡

2. በተጠሪ ላይ ለደረሰ ጉዳት ሊከፈል የሚገባው ብር 96,000 ሳይሆን ለውሉ መልከም ስራ አፈፃፀም የተያዘው ጠቅላላ ገንዘብ ብር 658,568 /ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ስምንት/ ተብሎ መወሰኑ በአግባብ ነው ብለናል፡፡


 

 

3. አመልካቾች ይህንን ገንዘብ በስር 3ኛ ተከሳሽ ለነበረው ደሽን ባንክ ሲተኩ የዋስትና መያዣው ይለቀቅለቸው ብለናል፡፡

4. በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ለተደረገው ክርክር በጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸው ይቻሉ ብለናል፡፡

5.  መዝገቡ ተዘጋ ወደ መ/ቤት የመለስ፡፡


 

 

ሩ/ለ


የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

 
 
 

Google Adsense