110681 civil procedure/ execution of judgment

በአፈጻጸም ወቅት አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት በሐራጅ ተሸጦ ከእዳ መክፈያ /ከግራ ቀኙ/ ይካፈሉ በተባለበት ጊዜ የሐራጅ ማስታወቂያ የፍ/ባለመብትን ጥቅም ላይ በቀጥታ ጉዳት እስካላደረሰ ወይም የሚያደርስ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የሐራጅ ማስታወቂያው ተገቢ ለሆነ ቀን በአየር ላይ አልዋለም ወይም በጨረታው ለሚሳተፉ ሰዎች በቂ ጊዜ አልተሰጠም የሚባልበት ሁኔታ አለመኖሩ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. አንቀጽ 445

 

የሰ/መ/ቁ.114043

የካቲት 18 ቀን 2008 ዓ/ም

ዳኞች፡- አልማው ወሌ

 

ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ

አመልካች፡- የኢትዩጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አቃቤ ሕግ ዐ/ህግ መብት አየሁ ቀረቡ ተጠሪ፡- አባዲ ሞገስ - ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

 

 ፍ ር ድ

 

ጉዳዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ እና በአቶ ንጉሴ ገ/ሕይወት ላይ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአውሲረሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው፡፡ የክሱ ይዘትም፡- ተከሳሾች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1(ሀ) እና(ለ) እንዲሁም የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 166 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ሆነ ብለው ሕገ ወጥ ጥቅም ለማስገኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ወይም ማወቅ ሲገባቸው ንብረትነቱ የ2ኛ ተከሳሽ(ንጉሴ ገ/ሕይወት) የሰሌዳ ቁጥር 2-A01474 አ.አ የሆነች የቤት መኪና የቀረጥና ታክስ ስሌቱ ብር 170,958.10(አንድ መቶ ሰባ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስምንት ብር ከአስር ሳንቲም) የሚያወጣ የኮንትሮባንድ እቃ በ2ኛ ተከሳሽ እና በሌሎች ግብረአበሮች አማካኝነት ጭኖ በመያዟ እና 2ኛ ተከሳሽም የመኪናው ባለቤት በመሆኑ እና የኮንትሮባንድ ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታዬ ባለበት ሁኔታ እና ጉዳዩ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲያስገኝ ድረስ ተከሳሽ በዋስ ሁኖ ጉዳዩን እንዲከታተል የተሰጠውን መብት በመጠቀም ልትወርስ የምትችለውን መኪና በቀን 27/04/07 ዓ/ም የመኪና ሽያጭ ውል በመፈራረም ሽያጩን ከቅን ልቦና ውጪ ከመደበኛ የገበያ ዋጋ በታች በ35,000.00(ሰላሳ አምስት ሺህ) በመሸጥ እና መኪናዋንም በጉምሩክ ወንጀል መተላለፍ ምክንያት በጉምሩክ ቁጥጥር ስር መሆኗን እያወቁ የባለቤትነት መብት /ሊብሬ/ 2ኛ ተከሳሽ ለ1ኛ ተከሰሽ (አባዲ ሞገስ) ስም ንብረቱ


እንዲተላለፍ በማድረግ በቁጥጥር ስር የነበረችውን መኪና በ1ኛ ተከሳሽ  አማካኝነት በቀን 01/05/07 ዓ/ም ሚሌ ቅ/ጽ/ቤት ቀርቦ መኪናዋን ለማውጣት ሲሞክር በቁጥጥር ስር በመዋሉ የጉምሩክ ቁጥጥር በማሰናከል ወንጀል ተከሶአል የሚል ነው፡፡ የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው የእምነት ክህደት ቃልም ስለወንጀሉ የሚያውቁት ነገር የሌለ መሆኑን፣ መኪናውን በቅን ልቦና የገዙት መሆኑን ጠቅሰው መብታቸውን ጠብቀው የተከራከሩ ሲሆን የስር 2ኛ ተከሳሽ ግን ሊቀርብ ባለመቻሉ በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግ ትእዛዝ ተሰጥቶአል፡፡ በአመልካችና በአሁኑ ተጠሪ መካከል ያለው ጉዳይ ግን ክርክሩ ለብቻው እንዲቀጥል ተደርጎ አመልካች አሉኝ ያላቸውን ማስረጃዎችን ያቀረበ ሲሆን ተጠሪም የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ ከተደረገ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ ተጠሪ መኪናውን የገዙት የፍርድ ቤት እግድ በሌለበት ሁኔታ ከመሆኑም  በላይ መኪናው እንዲለቀቅለት ጉምሩክ ቀርቦ መኪናው ኮንትሮባንድ በመጫኑ ምክንያት ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ) መክፈሉ ግዥውን የፈፀመው በቅን ልቦና መሆኑን የሚያሳይ መሆኑ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ተጠሪን ከወንጀሉ ክስ ነፃ ያሰናበታቸው ሲሆን የተያዘውም ንብረት ተገቢውን የአስተዳደር ቅጣት መክፍሉ ተረጋግጦ እንዲለቀቅ በማለት ወስኖአል፡፡ በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም፡፡ የአሁኑ የሠበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡-ተጠሪ ከቅን ልቦና ውጭ በመንቀሳቀስ በአዲሱ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 198(1) በወቅቱ የመኪናው ባለቤት የነበረው ግለሰብ በመተላለፍ በሕግ ጥላ ስር ውላ እና የውርስ ውሳኔ ተላለፎባት የምትገኘውን መኪና በሕገ ወጥ መልኩ በመግዛት እና ባለቤት ነኝ በማለት የጉምሩክ ቁጥጥር ስራን ሆነ ብሎ ለማሰናከል ጥረት ያደረገ እና በእጅ በማስገባት ሲል እጅ ከፍንጅ የተያዘ መሆኑ መረጋገጉን ገልፆ ተጠሪ በዚሁ አድራጎታቸው ጥፋተኛ ሊባሉ እንደሚገባ፣ የሥር ፍርድ ቤቶች ከስልጣናቸው ውጪ መኪናው እንዲለቀቅ የሰጡት ውሳኔም ተገቢነት የሌለው መሆኑን ዘርዝሮ ውሳኔው ሊታረም ይገባል በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው፡፡ አቤቱታው ተመርምሮም ለክርክሩ ምክንያት የሆነው መኪና ለተጠሪ እንዲለቀቅ የመወሰኑን አግባብነት  ለመመርመር ተብሎ ለዚህ ችሎት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርበውም ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጎአል፡፡

 

የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማጋዘብ ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጸር በሚከተለው  መልኩ መርምረናል፡፡


ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው መኪና በስር 2ኛ ተከሳሽ በነበሩት ግለስብ ስም የሚታወቅ ሁኖ የኮንትሮባንድ ወንጀል ተፈጽሞበታል ተብሎ በ09/04/2007 ዓ/ም በአመልካች ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የአሁኑ ተጠሪ በ13/08/2007 ዓ/ም በውልና ማስረጃ በተደረገ የሽያጭ ውል ከስር 2ኛ ተከሳሽ በብር 35,000.00 የገዙ መሆኑን፣ግዥው ሲፈጸም በመኪናው ላይ የተላለፈ እገዳ የሌለ መሆኑ የተረጋገጠና ተጠሪ መኪናው መያዙን አውቀው ለማስለቀቅ በሄዱበት ጊዜም ብር 40,000.00(አርባ ሺህ) እንዲከፍሉ ሲጠየቁ ይህንኑ ክፍያ ከፈፀሙ በኃላ የጉምሩክ ቁጥጥር ስራ በማሰናከል ወንጀል የተከሰሱ መሆኑን ነው፡፡

 

አመልካች በተጠሪ ላይ የጠቀሰባቸው አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 166 ሙሉ ይዘቱ ሲታይ የጉምሩክ ቁጥጥርን ስለማሰናከል የሚል አርእስት ያለው ሁኖ ዝርዝሩ ማንኛውም ሰው የጉምሩክ ሹም ሰነዶችን እንዳይመረምር ወይም ማጓጓዣዎችን ወይም ዕቃዎችን እንዳይፈትሽ ወይም ወደ መጋዘን፣ የንግድ መደብር ወይም መኖሪያ ቤት እንዳይገባ ያደረገ ወይም ሁከት የፈጠረ ወይም ለሚጠየቀው ጥያቄ ትክክለኛ መልስ ያልሰጠ ወይም ለምርመራ ያልተባበረ ወይም በማናቸውም መንገድ ሥራውን ለማደናቀፍ ጣልቃ የገባ እንደሆነ ከስድስት  ወር በማያንስና ከአንድ ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት እና ከብር 5‚000 በማያንስና ከብር 10‚000 በማይበልጥ መቀጮ እንደሚቀጣ በንኡስ ቁጥር አንድ ስር ያሰፈረ ሲሆን በንዑስ ቁጥር ሁለት ደግሞ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው ወንጀል የተፈፀመው ኃይል በመጠቀም ወይም በቡድን በመደራጀት ከሆነ የእስራት ቅጣቱ ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ዓመት ፅኑ እስራት ከፍ ይደረጋል በሚል የተቀመጠ ነው፡፡ ከድንጋጌው ለተጠሪ አድራጎት አግባብነት ያለው የወንጀሉ ማቋቋሚያ "በማናኛውም መንገድ ስራውን ለማደናቀፍ ጣልቃ የገባ" የሚለው ሐረግ ሲሆን አድራጎቱ ሆነ ተብሎ የሚፈጸም መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ የጉምሩክ ቁጥጥርን የማሰናከል ተግባር ሆነ ተብሎ የሚፈፀም ስለመሆኑ የተጠቃሹ አዋጅ ድንጋጌ ይዘቱን መንፈሱ የሚያሳይ ሲሆን አመልካች ተጠሪ አድራጎቱን ሆነ ብለው ስለመፈፀማቸው የሚያስገነዝቡትን የድርጊት አፈፃጸም ተግባር የማስረዳት ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23(4)፣ ከወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 141 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡

በተያዘው ጉዳይ አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረባቸው ማስረጃዎች ተጠሪ አከራካሪው መኪና የኮንትሮባንድ ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ ከተያዘ በኋላ መግዛታቸውን ያስረዱ ቢሆንም ተጠሪ በመኪናው ላይ የእግድ ትዕዛዝ ባለመሰጠቱ ምክንያት ተገቢው ማጣራት ተደርጎ በውልና ማስረጃ ቀርበው ግዥውን ፈጽመው መኪናው በጉምሩክ ቁጥጥር ስር የዋለ መሆኑን ከአወቁ በኋላም በመኪናው ላይ የሚፈለገውን ቀረጥና ታክስ እንዲከፍሉ ሲጠየቁ ብር 40,000.00 ለአመልካች ገቢ ከአደረጉ በኋላ በወንጀል የተከሰሱ መሆኑን በመከላከያ ማስረጃዎቻቸው አረጋግጠው አመልካች ይህንኑ ማስረጃ ሊያፈርስ የሚያስችል ማስረጃ ሊያቀርብ ያለመቻሉን ፍሬ ነገሩን የማጣራትና


ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዳይ ሁኖ አግኝተናል፡፡ በመሆኑም የተጠሪ የግዥ ተግባር በቅን ልቦና የተፈጸመ መሆኑን የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት በመሆኑ በዚህ ረገድ የበታች ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዳሜ ደግሞ ከአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 166 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ሲታይ በዚህ ችሎት ሊሊወጥ የሚችል ሁኖ አልተኘም፡፡ ስለሆነም ተጠሪ የፈፀሙት ተግባር በቅን ልቦና የተከናወነ መሆኑን ፍሬ ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዳይ በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን ቅሬታ ይህ ችሎት የሚቀበልበት አግባብ የሌለ ሁኖ ተገኝቶአል፡፡ እንዲሁም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ባቀረበው የወንጀል ክስ መነሻ ለክርክሩ ምክንያት በሆነው መኪና አስተዳደራዊ ቅጣት ተከፍሎ እንዲለቀቅ ያሰፈሩት ምክንያት ክፍልም በውጤቱ ሲታይ በአዋጅ ቁጥር 859/2006 ለአመልካች መስሪያ ቤት የተሰጠውን አስተዳደራዊ ስልጣን የገደበ ነው ለማለት የሚቻል ሁኖ አልተገኘም፡፡ ምክንያቱም የበታች ፍርድ ቤቶቹ የአመልካችን አስተዳደራዊ ስልጣን ተፈጻሚ እንዲሆን በሚያስገነዝብ መልኩ በውሳኔአቸው ላይ ከማስፈራቸው ውጪ ይህንኑ ስልጣኑን ተግባራዊ እንዳያደርግ በግልጽ አልገለፁምና፡፡ በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች በጉዳዩ ለይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል፡፡

 ው ሳ ኔ

 

1. በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አውሲረሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 3867 ግንቦት 06 ቀን 2007 ዓ/ም ተሰጥቶ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 3997 ግንቦት 28 ቀን 2007 ዓ/ም የፀናው  ውሳኔ  በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 192(2(ሀ)) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. ተጠሪ የቅን ልቦና ገዥ ነው ተብሎ ከወንጀሉ በነፃ እንዲሰናበት በመደረጉ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም ብለናል፡፡ ሆኖም አመልካች በሕጉ በተሰጠው ስልጣን አግባብ በመኪናው ላይ የሚወስደውን አስተዳደራዊ ውሳኔ ይህ ውሳኔ አያስቀረውም ብለናል፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝብ ቤት ይመለስ ብለናል፡፡

 

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

 

 

መ/ተ