አንድ ጉዳይ ከውል መተካት አንፃር እንዲታይ ይተካል በተባለው እና ተተክቷል በሚባሉ ውሎች መካከል ያለው የውለታ ጉዳይም ሆነ የውለታው ምክንያት በይዘቱ አዲስ መሆን እንዳለበትና ይህንኑ በውለታውም አይነት ሆነ ከውለታው ምክንያት አንፃር ታይቶ አዲስ የሆነው ውል ቀደም ሲል ተደርጎ በነበረው ውል ላይ የተመለከቱትን ግዴታዎች በማያጣራጥር አኳኋን ሊያስቀር የሚችል ፈቃድ ከተዋዋይ ወገኖች እንዲኖር አስፈላጊ ስለመሆኑ እና ውልን ከማሻሻል ጉዳይ አንፃር ሊታይ የማይገባ ስለመሆኑ
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1826 እና 1828