128086 contract law/ civil procedure/ arbitration/ jurisdiction

አንድ የግልግል ዳኝነት ጉባኤ መቀመጫ አዲስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያ ከሆነ፤ጉዳዩም ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠበት በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት ከሆነ፤የዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና የአገሮች ልምድ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕጎች እና የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት ከሰጣቸዉ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም አንጻር ተከራካሪ ወገኖች “የግልግል ዳኝነት ጉባኤው ዉሳኔ የመጨረሻ ዉሳኔ ነዉ” ብለው ቢስማሙም ዉሳኔዉ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ከሆነ በሰበር ከመታየት የሚከለከልበት የሕግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ፤ 

 በተንኮል የተደረገ ዉል ፈራሽ የሚሆነዉ ከተዋዋዮቹ አንደኛዉ ወገን ዉሉ እንዲደረግ ያደረገዉ በሁለተኛዉ ተዋዋይ ላይ ተንኮል ባይደርስበት ኖሮ ዉል የማያደርግ እንደነበረ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፤ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1704(1)፤1808(1)
 የአንድ ዉል በፍ/ቤት ዉሳኔ የፈረሰ እንደሆነ የዉሉ መፍረስ የሚያስከትለዉ ዉጤት ተጣርቶ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ
በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1704(1)፤ 1808(1)፤1815

Download here