አንድ ሰው በራሱ በኩል ምንም የገባው ግዴታ ባይኖርም በራሱ ጥፋት በሌላው ሰው ላይ ጉዳትን ካደረሰ ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ እና ማንም ሰው ከራሱ ጥፋት የተነሳ በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ካደረሰ ላደረገው ጉዳት ኪሳራ መክፈል ያለበት ስለመሆኑ
የፌዴራል ፖሊስ አባላት አግባብነት ባለው ሕግ እና ደንብ መሰረት ተሽከርካሪዎችን የማስቆም እና የመፈተሽ ስልጣን እና ኃላፊነት ያላቸው ቢሆንም ይህንን ኃላፊነት በሚወጡበት ጊዜ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2031(1) ስር የተመለከተውንና የሙያ ስራው የሚመራበትን ደንብ ማክበር የሚጠበቅባቸው ስለመሆኑ
ፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2031 (1)፣ 2027 (1) እና 2028