አንድ ቼክ በሚወጣበት ጊዜ በቼክ አውጭው ሂሣብ ቁጥር በቂ ስንቅ አለመኖሩ እየታወቀ ቼክ የተሰጠ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ከግል ተበዳዩ ጋር የቤተሰባዊ ግንኙነት ያላቸው ስለሆነና ቼኩን የሰጠው በመተማመኛ መልኩ ነው በማለት ድርጊቱ በቸልተኝነት የተፈፀመ ነው በሚል በወንጀል ህግ ዓንቀፅ 693(1) መሰረት የቀረበ ክስ ወደ ወንጀል ህግ አንቀፅ 693(2) በመቀየር ተከሳሹን ጥፋተኛ ማለት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 23፤59 ድንጋጌ ያላገናዘበ ስለመሆኑ