“በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 27 መሰረት አግባብ ያለው አካል በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን የማስለቀቂያ ትዕዛዝ መስጠት እና ካሣ መክፈል ሳያስፈልግ የሠባት የሥራ ቀናት የጽሑፍ ማሥጠንቀቂያ ብቻ ለባለይዞታው በአካል በመስጠት ወይም በቦታው በሰፈረው ንብረት ላይ በመለጠፍ የማስለቀቅ ሥልጣን ይኖረዋል” በማለት የተቀመጠው ሀሳብ በሕጋዊ መንገድ ለተያዙ የከተማ ቦታዎችን ለማስለቀቅ የተቀመጠውን የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የመስጠት እና ካሣ የመክፈል ሥርዓት ማሟላት ሳያስፈልግ በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን ማስለቀቅ የሚቻልበትን ሥርዓት የሚደነግግ እንጂ የከተማ ቦታን ወሮ ለያዘ ሰው የወንጀል ሀላፊነትን የሚያስቀር ስላለመሆኑ
አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 26(4)፣27