በአንድ የወንጀል ክስ ማመልከቻ ላይ ተጠቅሶ የቀረበ ድንጋጌና የክሱ ፍሬነገር ዝርዝር ላይ በስህተት የተጠቀሰ ወይም ሳይጠቀስ የታለፈ መሠረታዊ ነገር መኖሩ ሳይረጋገጥ ከወዲሁ አንቀጽ ካልተለወጠ በሚል ምክንያት ክስ እንዲሻሻል ትእዛዝ መስጠትና ይህ ካልተፈጸመ በሚል የክሱን መዝገብ መዝጋቱ ክስ እንዲሻሻል የሚደረግብትን ህጋዊ አላማ ያላገናዘበ ስለመሆኑ
አንድ ተከሳሽ ላይ የቀረበ ክስ ሁለት ሆኖ 1ኛዉ ክስ ቀደም ሲል ፍርድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ተሻሽሎ ባለመቅረቡ የሚዘጋ ቢሆን ሁለተኛዉ ክስ ላይ ያለምንም ህጋዊ ምክንያት ዉሳኔ ሳይሰጥ ማለፍ ሥነ-ሥርዓታዊ ስላለመሆኑ
በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/112፣113/2/፣119