All cases Volume 23
-
119851 civil procedure/ splitting of claims/ reverse cassation interpretation
አንድ ከሳሽ ክስ ሲያቀርብ ለክሱ ምክንያት የሆኑት ነገሮች በሙሉ አጠቃሎ ማቅረብ ሲችል ቀንሶ ባስቀረው ጉዳይ ላይ ድጋሚ ክስ ሊያቀርብ የማይችል ስለመሆኑፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 216(3)፤218 አንድ ጉዳይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343 መሰረት ወደ ስር ፍ/ቤት ተመልሶ ፍሬ ነገሩ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በመቃወሚያው ላይ አስቀድሞ በተሰጠ ብይን ላይ ተጠቃሎ የሚቀርብ የሰበር አቤቱታ ህጉን መሰረት ያደረገና ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑየፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 320(3)፤/የፌ/ፍ/ቤቶችን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል በሰ/መ/ቁ 90810 ፣ 76963፣ 125165 እና ሌሎችም በርካታ መዛግብት ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም በዚህ መዝገብ ውሳኔ ተለውጧል፡፡/ Download here
-
128086 contract law/ civil procedure/ arbitration/ jurisdiction
አንድ የግልግል ዳኝነት ጉባኤ መቀመጫ አዲስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያ ከሆነ፤ጉዳዩም ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠበት በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት ከሆነ፤የዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና የአገሮች ልምድ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕጎች እና የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት ከሰጣቸዉ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም አንጻር ተከራካሪ ወገኖች “የግልግል ዳኝነት ጉባኤው ዉሳኔ የመጨረሻ ዉሳኔ ነዉ” ብለው ቢስማሙም ዉሳኔዉ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ከሆነ በሰበር ከመታየት የሚከለከልበት የሕግ መሰረት የሌለ ስለመሆኑ፤ በተንኮል የተደረገ ዉል ፈራሽ የሚሆነዉ ከተዋዋዮቹ አንደኛዉ ወገን ዉሉ እንዲደረግ ያደረገዉ በሁለተኛዉ ተዋዋይ ላይ ተንኮል ባይደርስበት ኖሮ ዉል የማያደርግ እንደነበረ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ፤ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1704(1)፤1808(1) የአንድ ዉል በፍ/ቤት ዉሳኔ የፈረሰ እንደሆነ የዉሉ መፍረስ የሚያስከትለዉ ዉጤት ተጣርቶ መወሰን ያለበት ስለመሆኑበፍ/ብ/ሕ/ቁ.1704(1)፤ 1808(1)፤1815 Download here
-
131804 extracontractual law/ criminal liability
ከህግ አግባብ ውጪ ገንዘብ እንዲከፈል መደረጉን ተከትሎ የተሰጠ የወንጀል ጥፋተኝነት ውሳኔን መሰረት በማድረግ ገንዘብ ያለአግባብ እንዲከፈል ያደረገውን አካል ከውል ውጪ ኃላፊነት የተደነገገውን መሰረት በማድረግ ያላግባብ እንዲከፈል የተደረገው ገንዘብ እንዲመለስ ለመጠየቅ የሚቻል ስለመሆኑ፡- የፍ/ብ/ህ/ቁ 2035 Download here
-
132055 criminal procedure/ bail
የአንድ ተከሳሽ ያለፈ የቅጣት ውሳኔ አሁን ከተከሰሰበት ጉዳይ ጋር በማያያዝ በዋስ ቢለቀቅ ተመሳሳይ ወንጀል ሊፈጸም ይችላል የሚል ግምት በመውሰድ የዋስትና ጥያቄን አለመቀበል አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ በሕግ በግልጽ ካልተደነገገ በቀር አንድ ተከሳሽ በፍርድ ዳኝነት በግልጽ እስካልታወቀ ድረስ የቀድሞ ጥፋተኝነቱ የማይገለፅ ስለመሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 67 (ለ)፣138 (1) Download here
-
133398 contract law/ defect in formation of contract
አንድ ንብረት የገዛ ሰው የገዛውን ንብረት በፈለገው መልኩ መጠቀም የማያስችል ሁኔታ መፈጠር ፤ ውሉ ከመደረጉ በፊት ችግሩ/ጉድለቱ እንዳለ ቢያውቁ ኑሮ ውሉን አይፈጽምም ነበር የሚያሰኝ በመሆኑ ጉድለት ያለበት ውሉ ነው ተብሎ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት መመለስ ያለባቸው ስለመሆኑ፡- ፍ/ብ/ሕ/ቁ 1815፣ፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 2289 Download here
-
134343 property law/ urban land
የከተማ መሬት ይዞታ አጠቃቀም ላይ የመወሰን ስልጣን በህግ ስልጣን በተሰጣቸዉ በሚመለከታቸው የአስተዳደር አካላት ውሳኔ ባልተሰጠበት ሁኔታና በአስተዳደር አካል ያልተረጋገጠ መብት ይዞ ውሳኔ እንዲሰጥ ለፍርድ ቤት የሚቀርብ የዳኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/የከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ኤጀንሲን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁ. 179/05 አንቀጽ 8 Download here
-
134663 contract law/ agency
አንድ ዉክልና በላዩ ተዘርዝረዉ የተመለከቱትን ጉዳዮችና የነዚሁ ተከታታይ እና ተመሳሳይ የሆነዉን እንደ ጉዳዩ አይነትና እንደ ልማድ አሰራር አስፈላጊ የሆነዉን ማከናወን የሚያስችል ሲሆን ወካዩ የፈጸመዉ ተግባር የወካይና ተወካይ ጥቅሞችን ግጭት የሚያስከትል በሆነ ጊዜ 3ኛዉ ወገን ይህን ሁኔታ ያወቀና ሊያዉቅ የሚገባ መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር ኃላፊነት የማይኖርበት ስለመሆኑ ፍ/ሕ/ቁ 2206፤2187 Download here
-
137704 constitution/ civil procedure/ summon/ judgment in default
አንድ ተከሳሽ በሕግ አግባብ መጥሪያ የደረሰዉ እና እርሱ በሌለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ማወቁን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በሌለሁበት የተሰጠዉ ፍርድ ተነስቶ የመከላከያ መልስ ላቅርብ በማለት የሚያቀርበውን አቤቱታ በህግ በተቀመጠው አንድ ወር ጊዜ ዉስጥ አልቀረበም በሚል ምክንያት ብቻ መከላከያ መልስና ክርክር አቅርቦ የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብት መንፈግ ያልተገባና ህጋዊነት የሌለው ስለመሆኑ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78፣95 /2/ Download here
-
137704 constitution/ civil procedure/ summon/ judgment in default
አንድ ተከሳሽ በሕግ አግባብ መጥሪያ የደረሰዉ እና እርሱ በሌለበት ዉሳኔ መሰጠቱን ማወቁን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በሌለሁበት የተሰጠዉ ፍርድ ተነስቶ የመከላከያ መልስ ላቅርብ በማለት የሚያቀርበውን አቤቱታ በህግ በተቀመጠው አንድ ወር ጊዜ ዉስጥ አልቀረበም በሚል ምክንያት ብቻ መከላከያ መልስና ክርክር አቅርቦ የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብት መንፈግ ያልተገባና ህጋዊነት የሌለው ስለመሆኑ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78፣95 /2/ Download here
-
139187 civil procedure/litigation cost
አንድ ውል አይፈርስም ተብሎ ከተወሰነ በኋላ በተደረገው ውል መነሻነት የወጣ ወጭ ካለ በማጣራት በዚያው መዝገብ ላይ መወሰን የሚገባው እንጂ በሌላ መዝገብ አዲስ ክስ ቀርቦና እንዲከራከሩበት መወሰን ለተራዘመ የክርክር ሂደት ስለሚጋብዝ በዚህ መነሻነት መዝገቡን መዝጋት ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ Dowload here
-
139313 civil procedure/ joinder of defendants
አንድ ከሳሽ መብቱን ማግኘት የሚገባው ከየትኛው ተከሳሽ ላይ እንደሆነ ለይቶ ለማወቅ የሚያጠራጥር ሁኔታ ያጋጠመው ሲሆን አንዱን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑትን ሰዎች በህብረት በመክሰስ ሀላፊነቱ የሚመለከተው የትኛው እንደሆነ ተለይቶ እንዲወሰንለት ማመልከት ስለመቻሉ ፍርድ ቤቶች በአንድ ክስ ላይ ስማቸው በተከሳሽነት ከቀረቡ መካከል ስማቸው ከመጠቀሱ ውጪ በግልፅ ዳኝነት አልቀረበባቸውም በሚል ምክንያት ብቻ አንዱን ወይም የተወሰኑትን ሀላፊነት የለባቸውም በማለት የሚደርሱበት መደምደሚያ ህጉን ያተከተለ ስለመሆኑ፡- የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 36(5) Download here
-
141625 Constitution/ Administrative law/ city administration/ right to petition
የከተማ ይዞታን የማስተዳደር ስልጣን በህግ አግባብ የተሰጠው አካል ስልጣንና ኃላፊነቱን በህግ አግባብ አልተወጣም የሚል ክርክር ያለው ወገን ጉዳዩን ለፍ/ቤት የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 37፣ 40(3)(4)፣79(1) እና 78(4) Download here
-
142242 civil procedure/ splitting of claims
በአንድ ክስ አጠቃሎ ክስ ማቅረብ የሚቻለው በተቋቋመ መብት ላይ ተመስርቶ እንጂ ዳኝነት በተጠየቀበት ጊዜ ያልበሰለ ወይም ያልተረጋገጠ መብት ጭምር ማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33/2/፤216 Download here
-
142594 administrative law/ land dispute/ jurisdiction
የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ አላግባብ ተሰርዞብኛል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ጉዳዩ በቀጥታ ከመሬት ይዞታ ባለመብትነት ጋር ተያያዥነት ያለው በመሆኑ የተከራካሪ ወገኖች መደበኛ ነዋሪነት ወይም የተከራካሪው ወገን የፌዴራል መንግሥቱ ተመዝጋቢ መሆን ግምት ውስጥ ሳይገባ የክርክሩን ልዩ ባህርይ በማየትና የጉዳዩን ዓይነት መሠረት በማድረግ ንብረቱ የሚገኝበት የከተማ አሥተዳደር ፍ/ቤት የቀረበውን ክስ ተቀብሎ የመወሰን የሥረ-ነገር ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 25 ፤አዋጅ ቁጥር 226/07 አንቀጽ 57/1 Download here
-
142630 extracontractual liability/ strict liability/ vicarious liability/the police
አንድ ሰው በራሱ በኩል ምንም የገባው ግዴታ ባይኖርም በራሱ ጥፋት በሌላው ሰው ላይ ጉዳትን ካደረሰ ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ እና ማንም ሰው ከራሱ ጥፋት የተነሳ በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ካደረሰ ላደረገው ጉዳት ኪሳራ መክፈል ያለበት ስለመሆኑ የፌዴራል ፖሊስ አባላት አግባብነት ባለው ሕግ እና ደንብ መሰረት ተሽከርካሪዎችን የማስቆም እና የመፈተሽ ስልጣን እና ኃላፊነት ያላቸው ቢሆንም ይህንን ኃላፊነት በሚወጡበት ጊዜ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2031(1) ስር የተመለከተውንና የሙያ ስራው የሚመራበትን ደንብ ማክበር የሚጠበቅባቸው ስለመሆኑ ፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2031 (1)፣ 2027 (1) እና 2028 Download here
-
142851 authentication of documents
የመንግሥት አካል ፊት ቀርቦ የተረጋገጠና የተመዘገበ ሰነድ በውስጡ የሚገኘው ይዘት ሙሉ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 334/1995 አንቀጽ 27 /1/ Download here
-
143045 cooperatives/ law of succession
አንድ የመሰረታዊ ማህበር አባል ሲሞት ዕጣው ወይም ጥቅሙ በማህበሩ መዝገብ ውስጥ በወራሽነት ለሰየመው ወይም ሟቹ ወራሽ ያልሰየመ ከሆነ በሕግ ለመውረስ ለሚችል ወራሹ የሚተላለፍ ሲሆን ይህም የሚሆነው ወራሹ የማህበሩ አባል ከሆነ ወይም ለመሆን ፈቃደኝነቱን ሲገልፅ ሲሆን ወራሹ የማህበሩ አባል ካልሆነ ወይም አባል ለመሆን የማይፈልግ ወይም የማይፈቀድለት ከሆነ የሟቹ የዕጣው ዋጋ እና ጥቅም የሚከፈለው ስለመሆኑ የኅብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁ.147/1991 አንቀጽ 19፣ 32 Download here
-
143227 commercial law/ trade mark/ registration of trade mark
አንድ የንግድ ምልክት አንድ ዓይነት ወይም ተመሳሳይ የሆኑ የሌላ ዕቃዎችን አገልግሎችን በሚመለከት በሚገባ በሚታወቅ ወይም ኢትዮጵያ ዉስጥ ግልጋሎት ላይ ከዋለ የንግድ ምልክት ጋር አንድ ዓይነት ወይም ሊያሳስት በሚችል ደረጃ ተመሳሳይ ከሆነ ወይም ትርጉሙን ከያዘ መመዝገብ የሌለበት ስለመሆኑ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 አንቀጽ 7(2)፤ 36(1) Download here
-
143325 family law/vital statistics/evidence of marriage
ከወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ጽ/ቤት ያሊገባ የሚሌ ማስረጃ መውሰዴ በራሱ በሁሇት ሰዎች መካካሌ የነበረውን የትዲር ሁኔታ ግንኙነት መኖሩን የሚያረጋግጠውን ማስረጃ የሚያስተባብሌ ስሊሇመሆኑ የተሻሻሇው የቤተሰብ ሔግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 94-97 Download decision
-
144242 civil procedure/ jurisdiction/ City court
የቀበሌ የንግድ ሱቅ አላግባብ ተይዞብኛል ይመለስልኝ በሚል ለክስ ምክንያት የሆነው ጉዳይ በግለሰቦች መካከል የተደረገ ውል ሲሆን ጉዳዩን ተቀብሎ የማየት የዳኝነት ስልጣን የከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች ሳይሆን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 4፤የድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 33(1)(ረ) Download here
-
144272 civil procedure/ execution of judgment
አንድ ለክርክር ምክንያት የሆነ ንብረት በአፈፃፀም ምክንያት በሐራጅ እንዲሸጥ የአፈፃፀም መዝገቡን የያዘዉ ፍርድ ቤት ወስኖ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ ገዥ ካልተገኘ ንብረቱን ባለ ገንዘቡ የመረከብ መብት ያለው ሲሆን ይህን ግምት ማስተባበል የሚቻለዉ ደግሞ ባለገንዘቡ ቤቱን እንዲረከብ በሚል ተሰጥቶ የነበረዉ ትዕዛዝ ስነ-ስርዓት ህጉ በሚፈቅደዉ አግባብ በሌላ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሻሩ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 428(2) Download here
-
144470 civil procedure/ third party intervention
ክርክርን በመስማት ላይ ያለ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወገን በክርክሩ ጣልቃ እንዲገባ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ፣ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት አለመኖሩን ፍርድ ቤቱ ካመነበት ክርክሩ በየትኛዉም ደረጃ ላይ ቢሆን ጣልቃ ገቡ ከክርክሩ ዉጪ እንዲሆን ትዕዛዝ ከመስጠት የሚከለክለዉ ነገር የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥርዓት ህግ ከአንቀጽ 40-43 Download here
-
144901 property law/ servitude/ telecommunication
ማንኛዉም የቴሌኮሙንኬሽን ድርጅት የቴሌኮሙንኬሽን መስመር ሲዘረጋ መስመሩ የባለይዞታን ወይም የሌላ ህንጻ ላይ የሚዘረጋበት አስገዳጅ ሁኔታ ሲኖር አስቀድሞ ለባለይዞታዉ ወይም ለባለህንጻዉ በማስታወቅ የባለይዞታዉ ወይም የባለህንጻዉ ተቃዉሞ እንዳለ ሰምቶ ተገቢዉን የመወሰን ስልጣን ለኤጀንሲዉ የተሰጠ ስለመሆኑ የቴሌኮሙንኬሽን ድርጅት የአንድ ባለይዞታ ይዞታ ውስጥ ገብቶ በቋሚነት ኮንቴነር ከተከለ ለተጠቀመበት ይዞታ ተገቢዉን ካሳ ለባለይዞታው የመክፈል ግዴታ አለበት የቴሌኮሙንኬሽን አዋጅ ቁ/49/89 አንቀጽ 18፣20/1/፣22/2/፣እና አዋጅ ቁ/455/97 አንቀጽ 6 Download here
-
145456 contract law/ surety/ joint and several liability
አንድ የባንክ ሠራተኛ በሥራው አጋጣሚ ያገኘውን የደንበኛ ገንዘብ ከህግ ውጭ ቀንሶ በማስተላለፍና በማውጣት መውሰዱ በተረጋገጠበት ሁኔታ ሰራተኛው የወሰደውን ገንዘብ ዋሶቹ ከእርሱ ጋር በአንድነትና በነጠላ ገንዘቡን የመክፈል ኃላፊነት ያለባቸው ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ 1920፣1922 እና 1933 Download here
-
145523 contract law/ compensation
በአንድ ውል ምክንያት ለደረሰ የጉዳት ኪሣራ ምክንያት ግራቀኙ ተዋዋይ ወገኖች መሆናቸው ከተረጋገጠ ለደረሰው የጉዳት ኪሣራ ሁለቱም ሃላፊነቱን መሸከም ያለባቸው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ. 1799(1) ፣1802 (1)፣2090፣2091 Download this
-
145733 administrative law/ jurisdiction/ business registration
በንግድ ምዝገባ ፍቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 መሠረት አግባብ ባለው አካል አስተዳደራዊ እርምጃዎች የተወሰደበት ማናቸውም ሰው በህግ ጉዳይ ላይ ይግባኝ ቅሬታ ካለው ጉዳዩን ማቅረብ የሚገባው ለአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በይግባኝ እንጂ በቀጥታ ክስ ለአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሊቀርብ የማይገባ ስለመሆኑ የንግድ ምዝገባ ፍቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓንቀፅ 46፣47(2)፣47(3)፣ Download here
-
146457 contract law/ authentication
የዉክልና ሰነዶችን ለማረጋገጥና ለመመዝገብ ስልጣን በተሰጠዉ አካል የተረጋገጠ ሰነድ ሙሉ እምነት የሚጣልበት ማስረጃ ሆኖ ቅቡልነት ያለዉ ስለመሆኑና የሰነዱን ቅቡልነት መቃወም የሚቻለዉም በበቂ ምክንያት ፍርድ ቤት ሲፈቅድ ብቻ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ/922/08 አንቀጽ 23/1/ Download here
-
146503 civil procedure/ res judicata/ succession
አንድ ኑዛዜ ከፀደቀ በኋላ በቀረበ ንብረት ክፍፍል ውስጥ ወራሾች ከአውራሻቸው በውርስ ሊያገኙት ከሚገባው ድርሻ ተገቢውን ያላገኙ መሆኑን ገልጸው በሚከራከሩበት ጊዜ ፍሬ ነገሩ ተጣርቶ ከሚለይ በስተቀር ኑዛዜው ፀድቋል በሚል ምክንያት ብቻ የሐብት ድርሻቸውን በተመለከተ የሥረ- ነገር ክርክሩ ቀድሞ ታይቷል ተብሎ ውድቅ ሊሆን የሚችልበት የስነ ስርዓት ሕግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 5 Download here
-
146955 civil procedure/ execution of judgment/ arbitral award
የዕርቅ ስምምነት ውል እንደዉሳኔ ተቆጥሮ በፍርድ ቤት ለአፈፃፀም አቅርቦ ለማስፈፀም ስምምነቱ ግልጽና የፈፃሚዉን አካል ግዴታ በማያሻማ ሁኔታ የሚገልጽ መሆን ያለበት ሲሆን ግልጽ ያልሆነ የእርቅ ስምምነት ሲቀርብ፣ ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የሌላ ተከራካሪ ወገን ክርክር እንኳ መስማት ሳያስፈልገዉ ክሱን ዉድቅ ማድረግ የሚችል ስለመሆኑ ፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 3312(1) Download here
-
147930 family law/ loan of spouses
በጋብቻ ውስጥ የተዯረገ የብዴር ውሌ ከአንዯኛው ተጋቢ እውቅና ውጪ የተዯረገና የጋራ እዲ መሆኑ ፌሬነገር የማጥራትና ማስረጃን የመመዘን መርህን በተከተሇ መንገዴ ተረጋግጦ መወሰን ያሇበት ስሇመሆኑፌ/ብ/ህግ ቁጥር 2472 Download here
-
148158 contract law/ novation
አንድ ጉዳይ ከውል መተካት አንፃር እንዲታይ ይተካል በተባለው እና ተተክቷል በሚባሉ ውሎች መካከል ያለው የውለታ ጉዳይም ሆነ የውለታው ምክንያት በይዘቱ አዲስ መሆን እንዳለበትና ይህንኑ በውለታውም አይነት ሆነ ከውለታው ምክንያት አንፃር ታይቶ አዲስ የሆነው ውል ቀደም ሲል ተደርጎ በነበረው ውል ላይ የተመለከቱትን ግዴታዎች በማያጣራጥር አኳኋን ሊያስቀር የሚችል ፈቃድ ከተዋዋይ ወገኖች እንዲኖር አስፈላጊ ስለመሆኑ እና ውልን ከማሻሻል ጉዳይ አንፃር ሊታይ የማይገባ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1826 እና 1828 Download here
-
148270 civil procedure/ opposition
አንድ ሰው መብቴን ይነካል በሚል የመቃወም አቤቱታ ያቀረበበት ዉሳኔ በሌላ አግባብ ከተሻረ እና መብትን ሊነካ የሚችል ዉሳኔ በሌለበት የሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ ፍ/ሥ/ሥርዓት ህግ አንቀጽ 358ፍ/ሥ/ሥርዓት ህግ አንቀጽ 358
-
148570 family law/paternity/ DNA test
አባትነትን በሔግ ግምት ወይም በመቀበሌ መንገድች ሇመወሰን ክርክር ሲነሳ የባህሪ ወሳኝ ቅንጣት (DNA) ውጤት እንዯ መከሊከያ ማስረጃ እንዱቀርብ በሔጉ በግሌጽ የተቀመጠ ዴንጋጌ የላሇ በመሆኑ ፌርዴ ቤቶች በሔጉ የተረዘረጋውን ስርዒት ተከትሇውና ሇትክክሇኛ ፌትህ አሰጣጥ አስፇሊጊ መሆኑን ሲያምኑበት ተግባራዊ ሉያዯርጉት የሚችለ ስሇመሆኑ የዘር የባህሪ ወሳኝ ቅጣት (DNA) ምርመራ ውጤት በሔጉ በተመሇከተው አግባብ በሔጋዊ ምክንያቶች ሇማስረጃነት የሚቀርብ እንጂ በሔግ የተቀመጠውን ግምት እናት ስሇካዯች ብቻ ሇማስረጃነት የሚቀርብ ማስረጃ ነው ተብል ዴምዲሜ የሚዯረስበት ስሊሇመሆኑየአማራ ክሌሌ የቤተሰብ ሔግ አዋጅ ቁጥር 79/95 Download decision
-
149071 criminal law/ drawing of cheque without cover
አንድ ቼክ በሚወጣበት ጊዜ በቼክ አውጭው ሂሣብ ቁጥር በቂ ስንቅ አለመኖሩ እየታወቀ ቼክ የተሰጠ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ከግል ተበዳዩ ጋር የቤተሰባዊ ግንኙነት ያላቸው ስለሆነና ቼኩን የሰጠው በመተማመኛ መልኩ ነው በማለት ድርጊቱ በቸልተኝነት የተፈፀመ ነው በሚል በወንጀል ህግ ዓንቀፅ 693(1) መሰረት የቀረበ ክስ ወደ ወንጀል ህግ አንቀፅ 693(2) በመቀየር ተከሳሹን ጥፋተኛ ማለት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 23፤59 ድንጋጌ ያላገናዘበ ስለመሆኑ Download here
-
149301 contract law/ donation
ስጦታ የሚደረገው ስጦታው በተደረገበት ቀን የአስተላላፊው /የሰጭው/ የራሱ በሆነ ሀብት ላይ ብቻ ስለመሆኑ የፍትሓብሔር ህግ አንቀጽ 2427፤2451 /1/ Download here
-
149326 commercial law/ insurance policy
በአንድ ክስተት ከሁለት በላይ በሆኑ ሦስተኛ ወገኖች ላይ ጉዳት መድረሱ በመድን ሰጪና ተቀባይ መካከል በተደረገ የመድን ዉል መሰረት የመድን ሰጪዉ ግዴታ የኃላፊነት መጠን በመድን ዉሉ ላይ ከተመለከተዉ መብለጥ የሌለበት ስለመሆኑ የንግድ ህግ አንቀጽ 665(2) Download here
-
149861 contract law/ bailment /evidence
በአደራ የተሰጠ ገንዘብ መኖርን ለማስረዳት ተቀባይነት የሚኖረዉ ማስረጃ በጽሑፍ የተደረገ የአደራ ዉል እንጂ በሌላ የሰዉ ወይም የሰነድ ማስረጃ ስላለመሆኑ የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2782 እና 2472(1) Download here
-
150408 Family law/ civil procedure/ divorce by representation
በመርህ ዯረጃ ጋብቻ በፌቺ እንዱፇርስ መጠየቅ የሚገባው ከባሌና ሚስቱ አንዯኛው ተጋቢ ወይም ሁሇቱም ቢሆንም በህግ አግባብ ተቀባይነት ያሇው ውክሌና ማስረጃ ጋር የሚቀርብ የፌቺ ጥያቄ ተቀባይነት ያሇው ስሇመሆኑበፌ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.58፤ በፌ/ብ/ህ/ቁ.2199 Download here
-
150773 property law/ rural land/ lease/ oromia
በባህላዊ መንገድ የሚታረስ መሬትን በዉል ማከራየት የሚቻለዉ ከ3 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ሆኖ ዉሉም ዋጋ የሚኖረዉ በሚመለከተዉ አካል ተመዝግቦ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ የኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀጽ 10(2 እና 3) Download here
-
150803 land law/ criminal law/ illegal land possession
“በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 27 መሰረት አግባብ ያለው አካል በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን የማስለቀቂያ ትዕዛዝ መስጠት እና ካሣ መክፈል ሳያስፈልግ የሠባት የሥራ ቀናት የጽሑፍ ማሥጠንቀቂያ ብቻ ለባለይዞታው በአካል በመስጠት ወይም በቦታው በሰፈረው ንብረት ላይ በመለጠፍ የማስለቀቅ ሥልጣን ይኖረዋል” በማለት የተቀመጠው ሀሳብ በሕጋዊ መንገድ ለተያዙ የከተማ ቦታዎችን ለማስለቀቅ የተቀመጠውን የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የመስጠት እና ካሣ የመክፈል ሥርዓት ማሟላት ሳያስፈልግ በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታን ማስለቀቅ የሚቻልበትን ሥርዓት የሚደነግግ እንጂ የከተማ ቦታን ወሮ ለያዘ ሰው የወንጀል ሀላፊነትን የሚያስቀር ስላለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 26(4)፣27 Download here
-
151034 constitution/ human right/ criminal law/ retroactive of law
በወንጀል ጉዳይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ አዲስ የወጣ ህግ ተከሳሹን የሚጠቅም በሆነ ጊዜ ተከሳሹ አዲሱ ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ አዲስ የወጣው ህግ ተፈፃሚ እንዲሆን መደረግ ያለበት ስለመሆኑና በዚሁ ጉዳይ አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ በባህሪው እንደመደበኛ የክርክር ጉዳይ የሚታይ ሳይሆን በቀረበ ጊዜ ሊስተናገድ የሚችል በመሆኑ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የቀረበ አቤቱታ ነው በማለት ተቀባይነት የለውም የማይባል ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 22(2)፣ የወ/ሕ/አንቀጽ 6 እና 9(1)፤ ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ15/1/ Download here
-
151082 labor dispute/ manager/ leave
አንድ የሥራ ውሉ በገዛ ፈቃዱ የተቋረጠበት የሥራ መሪ ያልተጠቀመበት የአመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ ስለሚከፈልበት የሕግ አግባብ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2563 Download here
-
152038 criminal procedure/ confession
በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 27/2/ መሠረት አንድ ተከሳሽ ለፖሊስ የሚሰጠው የእምነት ቃል ለምርመራ ዓላማ ሲባል በምርመራ ጊዜ የተገኘ ማስረጃ በመሆኑ የቀረበውን ክስ ለማስረዳት የሚችል ተቀባይነት ያለው ማስረጃ መሆን አለመሆኑ በፍ/ቤት ሊመረመር እና ሊመዘን የሚገባው እንጂ ከወዲሁ ተቀባይነት አለው ተብሎ ድምዳሜ የሚወሰድበት ስላለመሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 27/2/ Download here
-
152134 succession law/ invalidation of will/ disinhersion
የፌትሒብሓር ህግ ቁጥር 973 ስሇ ኑዛዜ መነበብ እንዱሁም ኑዛዜው ሲነበብ የነበሩ ሰዎች ኑዛዜው እንዱፇርስ አቤቱታ የሚያቀርቡበትን ሥርዒት እና ጊዜውን በሚመሇከት የሚዯነግግ እንጂ ኑዛዜ ከውርስ ተነቅሇናሌ በማሇት ኑዛዜው እንዱፇርስ የሚቀርብን ወይም የቀረበን አቤቱታን የሚመሇከት ስሊሇመሆኑ አንዴ ኑዛዜ ከውርስ የመንቀሌ ውጤት ያሇው በመሆኑ እንዱፇርስ የሚሌ የዲኝነት ጥያቄ ሉታይ የሚገባው በፌትሒብሓር ህግ ቁጥር 1123 መሠረት እንጂ በፌትሏብሄር ህግ አንቀጽ 973 መሠረት ስሊሇመሆኑ Download here
-
152172 civil procedure/ execution of judgment/ interpretation of judgment
የፍርድ አፈጻጸምን የሚመራ ፍ/ቤት በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ በተዘረጋው ሥርዓት መሠረት እንደፍርዱ ይዘት እና መንፈስ ውጤት ባለው መልኩ ፍርዱን ከማስፈፀም በቀር የፍርዱን ይዘት በመመልከት የፍርዱን ይዘት አድማስ በማጥበብም ሆነ በማስፋት ፍርድን የመተርጎም ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 372፤378 Download here
-
152185 property law/ urban land/ land lease
አንድ ሰው የከተማን ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 ከመውጣቱ በፊት የይዞታ ማረጋገጫ እንዲሰጠው ጠይቆ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ተዘጋጅቶ እንዲሰጠው ውሳኔ ያገኘው አዋጁ በስራ ላይ በነበረበት ጊዜ ከሆነ የውሳኔው አፈፃፀም ሊቀጥል የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 37/1 መሠረት ሳይሆን በአዋጁ አንቀጽ 6/3/ በሊዝ ስሪት መሠረት ስለመሆኑ Download here
-
152339 civil procedure/ execution of judgment/ partition
ባልና ሚስት በጋብቻ ዉስጥ ያፈሩት ቤት ፍቺን ተከትሎ እንዲከፋፈሉ ዉሳኔ ተሰጥቶ በአፈጻጸም ሂደት አንደኛው ወገን ድርሻ ከፍሎ ለማስቀረት የጠየቀና የተወሰነ ገንዘብ ብቻ ይዞ ቀርቦ ቀሪዉን ለመክፈል ጊዜ ከመጠየቅ በቀር ግዥዉን ለመፈጸምና የቅድሚያ ግዥ መብቱን በጊዜው ሳይጠቀም ከቀረ የቅድሚያ ግዥ መብቱ ሊጠበቅ የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ስ/ሕ/ቁ 430(1) Download here
-
152417 Extracontractual liability/ bodily injury/ damage
የአካል ጉዳት ካሳ በርትዕ ሲወሰን ባጠቃላይ የተጎጂው የመስራት አቅሙ ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን መነሻ በማድረግ አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታዎች በተጎጂው የወደፊት ህይወት ላይ ሊያስከትሉ ስለሚችሉት አሉታዊ ተጽእኖ፤ ወቅታዊ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገት እና ተጨባጭ የገንዘብ /ብር/የመግዛት አቅም በየጊዜው እየቀነሰ መሄዱ፤ ወደፊት ሊታጣ የሚችለው ገቢ ከተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር ተገናዝቦ መታየት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2091 እና 2102 እና 2153(ሀ)) Download here
-
152590 civil procedure/ judicial jurisdiction/ private international law
ፍቺ ውሳኔን ተከትሎ በአንደኛው ወገን በቀረበ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ሌላኛው ወገን በጋብቻ ጊዜ ካፈሩት ገንዘብና ንብረት ከፊሉ ከኢትዮጵያ ውጪ ይገኛል በማለት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ማቅረቡ ብቻውን ጉዳዩ የግል ዓለም አቀፍ ሕግን ተፈጻሚነት ጉዳይን/ conflict of laws/ የሚያስነሳ ነው ከሚል ድምዳሜ ላይ የማያደርስ እና የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱን የማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከመሆን የማያስቀረው ስለመሆኑ የፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ቁጥር 9፣17 ፤አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 11 (2) (ሀ) Download here
-
152719 family law/ paternity/ DNA test
የባህሪ ወሳኝ ቅጣት ( DNA) ምርመራ አንዴ ሰው የሌጁ አባት ወይም እናት አይዯሇም ሇማሇት የሚቀርብ ማስተባባያ ማስረጃ ሉሆን የሚችሌ ቢሆንም የሚከናወነው አባትነትን በሚመሇከት የመካዴ ክስ ሇማቅረብ የሚያስችለ ቀዲሚ ሁኔታዎች ሲሟለ ስሇመሆኑ እና እናትነትን በተመሇከተም በቤተሰብ ህግ ከአንቀፅ 153 እስከ 166 ዴረስ የተዘረጋው ስርዒት የሚፇቅዴ ሁኖ በፌትሃ ብሓር ስነ ስርዒት ሔጉ የተመሇከቱትን የማስረጃ አቀራረብ ስርዒቶችን መሰረት በማዴረግ ሲቀርብ ስሇመሆኑአዋጅ ቁጥር 213/1992 ከአንቀጽ 167-179 Download here
-
152755 criminal law/ drawing of cheque without cover
የአንድ ቼክ ሕጋዊነት ጥያቄ ባላስነሳበት ፤በዋናነት ደግሞ ቼኩ ተጽፎ እና ተፈርሞ መሰጠቱ ባልተካደበት ሁኔታ እንዲሁም ቼክ እንደቀረበ ክፍያ የሚፈጸምበት ሰነድ ከመሆኑ አንፃር በወንጀል ጉዳይ ያለው ተጠያቂነት ቼክ በወጣበት ወይም ለክፍያ ለቀረበበት ጊዜ በቂ ስንቅ መኖር ያለመኖሩን መሠረት ያደረገ እንጂ ለዋስትና የተሰጠ መሆን ያለመሆን በወንጀል ጉዳይ እንደ ሕጋዊ መከላከያ የሚወሰድ ስላለመሆኑ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 693(1) Download here
-
152845 civil procedure/appeal/ time to appeal
ይግባኝ የማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን የመንግስት ስራ ዝግ በሆነበት ቀን ላይ ያረፈ ሲሆንና በቀጣዩ የሥራ ቀን ይግባኙ ተዘጋጅቶ ሲቀርብ ይግባኙ እንዲከፈት መፍቀድ ሥነ-ሥርዓታዊ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1862፣ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 323/2 ፣326 Download here
-
152968 family law/Divorce/ compensation
ከባሌና ከሚስት ባንደ የተፇጸመውና ሇፌቺው ምክንያት ሆኖ የተገኘው ጥፊት በላሊው ተጋቢ ሊይ ጉዲት አስከትል ከተገኘ በዲዩ ሊዯረሰው ጉዲት ከጋራ ንብረት በካሳ መሌክ ያንዯኛውን ተጋቢ ዴርሻ አብዛኛውን ወይም ሙለውን በዯሌ ሇተፇጸመበት ወገን እንዱከፇሌ ሉወሰን የሚችሌ ስሇመሆኑየኦሮሚያ ብሓራዊ ክሌሊዊ መንግሥት የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 69/95 እንዯተሻሻሇው አዋጅ ቁጥር 83/96 አንቀጽ 111፣117 Download here
-
153228 criminal law/ evidence law/ police witness/ perjury
አንድ ምስክር በፖሊስ በወንጀል ምርመራ ወቅት የሚሰጠዉ ቃል እንደመደበኛዉ የዳኝነት አካል ወይም የዳኝነት ነክነትወይም መሰል /quasi-judicial/ ተቋም ቃለ መሃላ ፈጽሞ የሚሰጥ የምስክርነት ቃል ባለመሆኑ ምስክሩ በፖሊስ የምርመራ መዝገብ የሰጠው የምስክርነት ቃል ፍ/ቤት ቀርቦ በመለወጡ ምክንያት የሀሰት ቃል የትኛዉ እንደሆነ በትክክል በሌላ ማስረጃ ሳይረጋገጥ የምስክሩ ቃል መለያየት ብቻዉን በቂ ማስረጃ በማድረግ ምስክሩ በሀሰተኛ የምስክርነት ቃል መስጠት ወንጀል የሚጠየቅበት የህግ መሰረት ስላለመኖሩ የወንጀል ህግ አንቀጽ 453/2/ Download here
-
153231 succession law/ partition of property
የውርስ ንብረት ክፍያ ከተደረገ በኋላ በክፍያ ውስጥ ያልገቡ በውርሱ ንብረት ውስጥ ገብተው የሚቆጠሩ አዲስ ሀብቶች የተገኙ እንደሆነ አዲስ የክፍያ ስርዓት መፈፀም የሚቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1103፣1104 Download here
-
153258 family law/Divorce/ common property
የባሌና ሚስት ፌቺ ተፇጽሞ የንብረት ክፌፌሌ እስከሚዯረግ ዴረስ በጋብቻ ውስጥ የተፇራ ንብረትም ሆነ ከዚህ ንብረት የሚገኝ ገቢ የጋራ ሆኖ የሚቆይ ስሇመሆኑየተሻሻሇው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 89 Download decision
-
153418 law of person/ absence
የመጥፋት ዉሳኔ ከተሰጠና የጠፋው ሰው ንብረት ለወራሾቹ ከተላለፈ በኋላ የመጥፋት ዉሳኔ የተሰጠበት ሰዉ በህይወት ከተመለሰ ሌላ ማረጋገጫ ሳያስፈልገዉ ንብረቶቹ በሚገኙበት አኳኋን መልሶ መዉሰድ ስለመቻሉ የፍ/ብ/ህግ 168-173 Download here
-
153527 tax law/ custom/ reward for whistle-blower
በሕገወጥ ዕቃዎች መረጃ አሠጣጥ፤አያያዝ እና አመዘጋገብ እና የወሮታ ክፍያዎችን ለመወሰን ተሻሽሎ በወጣው መመሪያ ቁጥር 78/2004 መሠረት ለኢትዮጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጥቆማ ሲቀርብ ወሮታ ስለሚከፈልበት አግባብ መመሪያ ቁጥር 78/2004 አንቀጽ 16/1እና2፤17 Download here
-
153610 civil procedure/ evidence law/ witness
ለአንድ ጉዳይ ለምስክርነት የተቆጠረ ሰው በፍርድ ቤት ጥሪ መሠረት ቀርቦ የመመስከር ግዴታ ያለበት ሲሆን ምስክሩ ሊቀርብ ካልቻለም ፍርድ ቤቱ ተገቢ መስሎ በታየው መንገድ ትዕዛዝ በመስጠት ምስክሩ በሕግ አግባብ ተገዶ ወይም ታስሮ እንዲቀርብ በማዘዝ ምስክርነቱን በመስማትና ተገቢ ነው ካለም በሌላ ማስረጃም ጭምር በማጣራት የቀረበለት ጉዳይ ላይ ተገቢውን ዳኝነት ሊሰጥ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 116፣118(2)(ለ) Download here
-
153617 cooperatives/ jurisdiction/ arbitration
በአዋጅ ቁጥር 147/91 መሰረት አንድ ማሕበር ሕልዉናዉ ካበቃ በኃላ ወይም መብትና ግዴታዉ የሕብረት ሥራ ማሕበር ወደ አልሆነ የንግድ ማሕበር ተላልፎ በሚገኝበት ወቅት ጉዳዩ በሽምግልና ዳኝነት የሚታይበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ እና መደበኛ ፍ/ቤቶች ጉዳዩን ለማየት የስረ-ነገር ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 47 እና 49 Download here
-
153664 contract law/ immovable property/ written contract
የማይንቀሳቀስ ንብረት ካለዉ ልዩ ባህርይ አንፃር ንብረቱን ከአንድ ወደ ሌላ ሰዉ በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል በሦስተኛ ወገን ላይ ህጋዊ ዉጤት ያስከትል ዘንድ ዉሉ በህግ አግባብ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ ካልተመዘገበ ውሉ ፈራሽ የሚሆን ሲሆን ሻጩም በዉሉ ምክንያት የተቀበለዉን ገንዘብ የመመለስ ግዴታ ያለበት ሲሆን፣ ይህን እንዲያደርግ ሌላ ክስ ማቅረብ ሳያስፈልግ በዚያው መዝገብ ላይ መወሰን የሚቻል ስለመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ አንቀጽ 2878 Download here
-
153690 criminal law/ concurrent crimes/ aggravated punishment
አንድ ተከሳሽ በአንድ ቸልተኝነትና በአንድ ድርጊት በደረሱ ጉዳቶች በተደራራቢ ወንጀሎች ሲከሰስ ሌላ የተለየ ሀሳብና ድርጊት መኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ አንዱን በቸልተኝነት ሌላዉን ደግሞ ሆን ተብሎ ታስቦ በተፈጸመ ወንጀል ጥፋተኛ የሚደረግበት አግባብ እና ቅጣትን በሚመለከት ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈጽመዉ ሲገኙ ቅጣት ሊወሰን የሚገባዉ ለእያንዳንዱ ወንጀል መነሻ ቅጣት ከተያዘ በኃላ እነዚህን በመደመር ድምሩ የቅጣት መጠን የሚያርፍበትን ዝቅተኛ የቅጣት እርከን በመለየት ስለመሆኑ የተሻሻለዉ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 22(1/ሀ) Download here
-
153736 property law/ intellectual property/ copyright
ከቅጅ መብት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች የሚጣሩበት አግባብም ሆነ ክርክሮቹን መሠረት በማድረግ የሚሰጡ ዉሳኔዎች የቅጅ መብት ጥበቃ አጠቃላይ ዓላማ መሠረት በማድረግ የቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ለማግኘት ስራዎቹ ማሟላት የሚጠበቅባቸዉ መመዘኛዎች መሟላታቸው አለመሟላታቸውን ስለ ቅጅ መብት ዕዉቀትና ልምድ ያላቸዉ ባለሙያዎች የተካተቱበትን አጣሪ ቡድን በማቋቋም እንዲያጣሩ በማድረግ የቅጅ መብት ጥሰት የተፈፀመ መሆን አለመሆኑን በማጣራት መወሰን ያለበት ስለመሆኑ በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 91(3) ፤አዋጁ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 2(8)፣2(30)፣ 4(1)(ለ)፣ 6(1) Download here
-
153890 property/ commercial law/ business
በንግድ መደብር ውስጥ የሚገኙ ግዙፍነት ያላቸው እንደ መሳሪያዎች፣ የቤት ዕቃዎችና ሸቀጥ ያሉ ንብረቶች ባለሀብትነትን ንብረቱን በመግዛት ወይም በሌላ አኳኃን ያገኘው ወይም በኑዛዜ የተሰጠው ሰው ንብረቱን በእጁ ባደረገው ጊዜ የሚተላለፍለት ስለመሆኑና ተቃራኒ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ የእነዚሁ ንብረቶች ባለሀብት ስለመሆኑ በሕጉ ግምት የሚወሰድበት ስለመሆኑ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1186 (1)፤ንግድ ሕጉ በቁጥር 128 download here
-
153981 commercial law/ business organisations
የንግድ ማህበር ስለሚፈርስበት አግባብ የንግድ ህግ ቁጥር 217፤218 እና 542 Download here
-
154023 civil procedure/ period of limitation/ preliminary objection
አንድ ተከሳሽ የቀረበበት ክስ በይርጋ የሚቋረጥ መሆኑን ከጠቀሰ ከሳሹ ክሱ በሕጉ የተመለከተው ጊዜ ገደብ (ይርጋ) ያላለፈው መሆኑን፣ ጊዜው አልፎ ከሆነም ይርጋውን ሊያቋርጥ የሚችል ሕጋዊ ምክንያት መኖር ያለመኖሩን በተገቢው ማስረጃ ለማስረዳት የሚችልበት እድል ሳይሰጠው የተከሳሽ መቃወሚያ ብቻ መሰረት ተደርጎ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ተብሎ ብይን የሚሰጥበት አግባብ ስነ ስርዓታዊ ስላለመሆኑ ፍ/ብ/ሕ/ቁጥር1000፣1846፣1852እና1853፤የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 241፣ 244 እና 245(1) Download here
-
154115 contract law/ bank deposit
ገንዘብን በአደራ የማስቀመጥ ዉል (deposit fund) መነሻነት አደራ ያስቀመጠ ባንክ የአደራ አስቀማጩን ገንዘብ የመጠበቅ፣ ሲጠይቁ ወጪ አድርጎ የመክፈል እና ከአስቀማጩ ዉጪ ለሌላ ሰዉ ያለመክፈል ከዉል የመነጨ ግዴታ ሲኖርበት ይህን ግዴታውን ባይወጣ አስቀማጩ ላይ ሊደርስ ለሚችል ጉዳት ከዉል የመነጨ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ባንኩ የሚቀርብለትን የክፍያ ጥያቄ ሲያስተናግድ፣ገንዘብ እንዲከፈለዉ ጥያቄዉን ያቀረበ ሰዉ በርግጥም አደራ አስቀማጩ መሆን አለመሆኑን በቅድሚያ የማረጋገጥ ግዴታ የሚኖርበት ስለመሆኑ የንግድ ህግ 896 እና 897 Download here
-
154222 civil procedure/ execution/ sale by auction
በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት በመጀመሪያ ጨረታ ሽያጭ ላይ ተወዳድሮ አሸናፊ የተባለ ገዥ ዋጋ ከፍሎ ግዥዉን ባለመፈጸሙ ድጋሚ ጨረታ ሲደረግ የሽያጭ ዋጋ ቢቀንስ በሁለተኛዉ እና በአንደኛዉ ጨረታ መካከል ለተፈጠረዉ የዋጋ ልዩነትና ኪሳራ የመክፈል ግዴታ ሁለተኛውን ጨረታ ተወዳድሮ አሸናፊ የሆነው ሰው ላይ የማይወድቅ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ./429 Download here
-
154371 advocate's professional ethics
አንድ ጠበቃ ደንበኛው ላይ በቀረበ ክስ “በተመሳሳይ ጉዳይ ሁለት ፍርድ ቤት ክስ ሊቀርብ አይገባም ” በሚል በህግ የተፈቀደን መቃወሚያ ማቅረቡ የጥብቅና ሙያን የሚያጎድፍ ተግባር ፈፅሟል ተብሎ በዲስፕሊን የሚያስቀጣው ተግባር ስላለመሆኑ የትግራይ ክልል የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ ቁ/ 262/2007 አንቀጽ 30/23/ Download here
-
154727 constitution/ civil procedure/ time to prepare defense
አንድ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስና ማስረጃ በመመርመር ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ መልሱን አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ የታዘዘው እና ቀጠሮ የተሰጠው ከ10 ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከሆነ የተከሳሹን የመከላከልና የመከራከር የመሰማት መብቱን የሚነፍግ በመሆኑ በቂ ጊዜ ተሰጥቶት የመከላከያ መልሱን እና ክርክሩን እንዲያቀርብ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.240[2] Download here
-
155664 property law/ condominium houses/ possessory action
የመንግስት ቤት ህጋዊ ተከራይ የሆነ ወላጅ የኮንደሚኒየም ቤት በደረሰው ጊዜ ከመንግስት የተከራየውን ቤት ለመንግስት የማስረከብ ግዴታ ያለበት በመሆኑ የወረዳው አስተዳደር ፅ/ቤት የመንግስት ቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ለተከራዩ ልጆች ቤቱን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የሁከት ተግባር የማይስብለው ስለመሆኑ የተሻሻለው የመንግስት ቤቶችን ለማስተዳደር የወጣው መመሪያ ቁጥር 4/2009 ዓንቀፅ 15(ሐ(መ)) Download here
-
155789 criminal procedure/ amendment of charges
በአንድ የወንጀል ክስ ማመልከቻ ላይ ተጠቅሶ የቀረበ ድንጋጌና የክሱ ፍሬነገር ዝርዝር ላይ በስህተት የተጠቀሰ ወይም ሳይጠቀስ የታለፈ መሠረታዊ ነገር መኖሩ ሳይረጋገጥ ከወዲሁ አንቀጽ ካልተለወጠ በሚል ምክንያት ክስ እንዲሻሻል ትእዛዝ መስጠትና ይህ ካልተፈጸመ በሚል የክሱን መዝገብ መዝጋቱ ክስ እንዲሻሻል የሚደረግብትን ህጋዊ አላማ ያላገናዘበ ስለመሆኑ አንድ ተከሳሽ ላይ የቀረበ ክስ ሁለት ሆኖ 1ኛዉ ክስ ቀደም ሲል ፍርድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ተሻሽሎ ባለመቅረቡ የሚዘጋ ቢሆን ሁለተኛዉ ክስ ላይ ያለምንም ህጋዊ ምክንያት ዉሳኔ ሳይሰጥ ማለፍ ሥነ-ሥርዓታዊ ስላለመሆኑበወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁ/112፣113/2/፣119 Download here
-
156389 civil procedure/ execution / rent law
የአንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት አከራይ የሆነ ሰዉ ላልተከፈለዉ የዉዝፍ ኪራይ ክፍያ አከፋፈል ሲባል ተከራዩ በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት በመጀመሪያ ጨረታ ሽያጭ ላይ ተወዳድሮ አሸናፊ የተባለ ገዥ ዋጋ ከፍሎ ግዥዉን ባለመፈጸሙ ድጋሚ ጨረታ ሲደረግ የሽያጭ ዋጋ ቢቀንስ በሁለተኛዉ እና በአንደኛዉ ጨረታ መካከል ለተፈጠረዉ የዋጋ ልዩነትና ኪሳራ የመክፈል ግዴታ ሁለተኛውን ጨረታ ተወዳድሮ አሸናፊ የሆነው ሰው ላይ የማይወድቅ ስላለመሆኑ Download here
-
156408 contract law/ written contract/ signature
በአንድ የብድር ዉል ላይ ያለ ፊርማ የኔ አይደለም የሚል ክርክር በመነሳቱ በብድር ዉሉ ላይ ያለዉን ፊርማ ተበዳሪው በመካዱ በፎረንሲክ ምርመራ የእሱ ፊርማ አለመሆኑ የተረጋገጠ ሰነድ ላይ ፊርማው የተበዳሪው ስለመሆኑ አበዳሪው በሰዉ ምስክሮች ላስረዳ በማለት የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2006 እና 2472(1) Download here
-
156420 criminal law/ negligence/ car accident
አንድ የአሽከርካሪነት ሙያ ያለዉ ሰዉ የትራፊክ ደህንነት ደንብን ተላልፎ በተሽከርካሪዉ የኋላ የዉጭ አካል ላይ ሰው አሳፍሮ ሲያሽከረክር ተሳፋሪው ለመዉረድ ሲል መዉደቁ ወይም ለመዉረድ ሲል ዘሎ በመዉደቁ ለደረሰበት ጉዳት አሽከርካሪውን በቸልተኝነት ተጠያቂ ከመሆን የማያስቀረው ስለመሆኑ የወ/ሕ/አንቀጽ 24፣ 59፣543(3)፣ በትራፊክ ደህንነት ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 36(1) Download here
-
156425 constitution/ use of images/ advertisement/
የሰውን ምስል ያለባለቤቱ ፈቃድ ለማስታወቂያ ሥራ በቴሌቭዥን በማስተዋወቅ ጥቅም ላይ ያዋለ አካል ምስሉን ከባለቤቱ ፍቃድ ውጪ በመጠቀም ለሰራው ማስታወቂያ ተገቢውን ካሳ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 14፣የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 27፣28፣ 29 Download here
-
156758 civil procedure/ execution of judgement/ auction
አንድ ክርክር ያስነሳ ንብረት በአፈፃፀም ሂደት በጨረታ ከተሸጠና ገንዘቡም ለፍርድ ባለገንዘብ ከተከፈለ በኃላ በጨረታዉ ሂደት ጨረታዉን ሊያስፈርስ የሚችል ጉድለት ካልተገኘ እንዲሁም ንብረቱ ለ3ኛ ወገን እንዳይተላለፍ የተሰጠ ዕግድ በሕግ አግባብ ያልተመዘገበ መሆኑ ከተረጋገጠ የቀዳሚነት መብትን ለመጠቀም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418 መሰረት የሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 418፣426፣445 Download here
-
156999 criminal procedure/ appeal
የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ለይግባኝ ማቅረቢያና ተያያዥ ጉዳዮች የጊዜ ገደብ ቢያስቀምጥም በመታየት ላይ ያለ መዝገብ መዘጋቱ አስፈላጊ ሆኖ ከተዘጋ በኃላ እንደገና መከፈቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በምን ያህል ጊዜ ዉስጥ አቤቱታ ሊቀርብበት እንደሚገባ በግልፅ ስላላስቀመጠ የጊዜ ገደቡ የሚወሰነው የጉዳዩን ሁኔታዎችና የአቤቱታዉን ዓይነት በመመልከት እንጂ መዝገቡን ለማንቀሳቀስ የቀረበዉ አቤቱታ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የቀረበ ነው በማለት አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ የይግባኝ ባዩን መብት የሚጣብብ ስለመሆኑ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 22(2)፤በወ/ሕ/አንቀጽ 6፣ 9(1) Download here
-
158539 commercial law/ bank law/
አንድ ባንክ በአደራ የተቀበለውን የደንበኛውን ገንዘብ የመጠበቅ ሕጋዊ ግዴታ ያለበትና ከሕግ ውጪ የደንበኛውን ገንዘብ ወጪ እንዲሆን ያደረገ ሰው በባንኩ ገንዘብ ላይ ጉዳት ማድረሱ ከተረጋገጠ ደንበኛው ገንዘቡን ከባንኩ የማግኘት መብት በህግ የተጠበቀለት በመሆኑ ባንኩ ደንበኛውን በመተካት ወይም በራሱ ስም ሆኖ የደንበኛውን ገንዘብ ባልተገባ ወይም በወንጀል ተግባር ወጪ አድርጎ ለግል ጥቅሙ ባዋለው ሰው ላይ ክስ ቢያቀርብ ባንኩ በቅድሚያ የደንበኛውን ገንዘብ ስለመክፈሉ ወይም በደንበኛው የባንክ አካውንት ገቢ ስለማድረጉ የሚያሳይ ማስረጃ አላቀረበም በሚል ክሱ ውድቅ የሚደረግበት የሕግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የንግድ ህግ አንቀፅ 896-902፤አዋጅ ቁጥር 592/2000 አንቀፅ 52(1) Download here
-
158613 criminal law/ court contempt
የዳኝነት ስራ አካሄድ ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች በተለይም አንድ ችሎት በያዘዉ መዝገብ ላይ ችሎት መድፈርን በተመለከተ ወዲያዉኑ ቅጣት ሊወስን ስለሚችልበት አግባብ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 449 ፣ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/480 እና 481 Download here
-
158899 property right/ condominium houses
አንድ ሰዉ የኮንዶሚኒየም ግዥ ፈጽሟል ሊባል የሚችለዉ ከሚመለከተዉ አካል ጋር ስምምነት መፈጸሙ ሲረጋገጥ ብቻ ሲሆን ገዥዉ ቤቱን ለሦስተኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ማስተላለፍ የሚችለዉ ቤቱን ከገዛ 5 ዓመት ሲሞላዉ ሲሆን ጊዜው የሚቆጠረዉ ዕጣ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ሳይሆን ገዥዉ የቤት ሽያጭ ዉል ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር ከፈጸመበት ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ በአ/አ ከተማ አስተዳደር አካላት የአስተዳደሩን ቤቶች የማስተላለፍ ኃላፊነትና አፈፃፀሙን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 19/97 አንቀጽ 7(6-ለ)፣14(2) Download here
-
159414 property law/ possessory right
አንድ ባለይዞታ ወሰን አልፎ በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ያለአግባብ በመግባት የሰራው ግንባታ በሌላኛው ባለይዞታ ንብረት አጠቃቀም ላይ ጉዳት ያደረሰ መሆኑ በባለሙያ ከተረጋገጠ ባለሙያው ባለበት ተለክቶ በዚያው ልክ ወሰኑን ያለፈዉን ግንባታ እንዲያፈርስ መደረግ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 1204፣1205፣1225/1/ Download here
-
159474 succession law/ invalidation of will/ petitio heriditatis
የኑዛዜ ወራሽነት ይረጋገጥልኝ በሚል አቤቱታ በተከፈተ መዝገብ ላይ ኑዛዜው ሕጋዊ አይደለም የሚል ተከራካሪ ወገን በሚቀርብበት ጊዜ ፍ/ቤቶች ወደ ኑዛዜው ይዘት እና ሕጋዊነት ሁኔታ ገብተው ተገቢውን ውሳኔ መስጠት ያለባቸው በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ግራ ቀኙን በሕጉ አግባብ በመስማትና በሚገባ በማጣራት ተገቢውን ዳኝነት መስጠታቸው ስነ ስርዓታዊ እንጂ በንብረት ክርክር ጊዜ የሚታይ ነው ተብሎ የሚታለፍ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 996 Download here
-
162776 contract law/ bailment/ contract in writing
በአደራ የተሰጠ ገንዘብ መኖርን ለማስረዳት ተቀባይነት የሚኖረዉ ማስረጃ በጽሑፍ የተደረገ የአደራ ዉል እንጂ በሌላ የሰዉ ወይም የሰነድ ማስረጃ ስላለመሆኑ የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2782 እና 2472(1) Download here
-
162776 contract law/ penalty provision
በአንድ ውል ላይ የገደብ (የመቀጫ)ስምምነት በተደረገ ጊዜ ባለገንዘቡ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ውሉ እንዲፈፀም እንዲሁም የመቀጮ ገንዘብ እንዲከፈል ለመጠየቅ የሚችል ሲሆን ነገር ግን መቀጮ የሚከፈለው የውሉ መዘግየት ወይም ተጨማሪ ግዴታዎች ካሉ የእነሱ አለመፈፀም የመቀጮውን ክፍያ የሚያስከትል ሲሆን ስለመሆኑ ፍ/ብ/ህ/ቁ 1890(1)(2) Download here