23861 contract of agency/ agents and pleaders

ወኪል የሆነ ሰው ውክልናውን በሚገባ እስካሳየ ድረስ በማመልከቻው ላይ የራሱን ወይም የወካዩን ስም አስቀድሞ መፃፉ ወኪልነቱን ለውጦ ባለቤት የሚያደርገው ስላለመሆኑ

የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 58

የሰ/መ/ቁ. 23861

ጥቅምት 14 ቀን 2000 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ

ተገኔ ጌታነህ መስፍን Eቁበዮናስ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ Aመነው

Aመልካች፡- ሊቀስዩማን Aስፋ በሻህውረድ ወኪል ጀነነው Aሰፋ ቀረቡ ተጠሪ፡- የሣህሊተ ምህረትና ክርስቶስ ሳምራ ደብር Aስተዳደር Aልቀረቡም

መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሠጥተናል

ፍ ር ድ

ለዚህ Aቤቱታ መንስኤ የሆነው የAመልካች ወኪል ጀነነው Aሰፋ የተባለው በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ክስ መስርቶ ክሱ በመታየት ላይ Eያለ ፍ/ቤቱ Aቶ ጀነነው Aሰፋ ክሱን የመሠረተው “ከሳሽ ጀነነው Aሰፋ” ብሎ ፅፉል፣Eሱ ወኪል Eንጂ ከሳሽ ሊሆን Aይችልም በማለት ክሱን ውድቅ በማድረጉና በከፍተኛው ፍ/ቤትም Aያስቀርብም በመባሉ ነው፡፡

ለዚህ ፍ/ቤት የቀረበው Aቤቱታ መሠረተ ሃሳብም Aቶ ጀነነው Aሰፋ የAመልካች ወኪል በመሆኑ ክሱን የመሠረተውም Aመልካችን ወክሎ Eንጂ በራሱ ስላልሆነ ክሱ ውድቅ የተደረገው በማይገባ ነው በማለት ነው፡፡

Aቤቱታው ለሰበር ችሎት ያስቀርባል ተብሎ ለተጠሪ መጥሪያ ተልኮለት ባለመቅረቡ ክርክሩ በሌለበት ታይቷል፡፡

የሥር ፍ/ቤት የAመልካቹ ወኪል “ከሳሽ ጀነነው Aሰፋ” በማለቱ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.33 መሠረት ክስ ማቅረብ Aይቻልም ብሏል፡፡ ፍ/ቤቱ ውሣኔ በሠጠበት በግንቦት 29 ቀን 1997 ዓ.ም በውሣኔው ላይ የመዘገበው “ከሳሽ ጀነነው Aሰፋ” ብሎ ነው፡፡ በነሐሴ 2 ቀን 1995 ዓ.ም  በቀረበው የክስ ማመልከቻ ላይ ግን “ከሳሽ ጀነነው Aሰፋ ሊቀስዩማን Aሰፋ በሻህውረድ ወኪል”

ተብሎ ተፅፏል፡፡

 

የውክልና ሥልጣን ያለው ሰው በዋናው ባለመብት ስም የክስ ወይም የAቤቱታ ማመልከቻ ማቅረብ Eንደሚችል የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 58 ይደነግጋል፡፡ Aቶ ጀነነው Aሰፋ የሊቀስዩማን Aሰፋ በሻህውረድ ወኪል መሆኑ በፍ/ቤቱም የተገለፀ በመሆኑ Aመልካቹን ወክሎ ክስ ማቅረብ ይችላል፡፡ ክስ የመሠረተውም በውክልናው መሠረት ለመሆኑ ለየካ ምድብ ፍትሃብሄር ችሎት የፃፈው የክስ ማመልከቻ ያረጋግጣል፡፡ በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33/2/ በመጥቀስ በጉዳዩ ላይ መብት ስለሌለው ሊከስ Aይችልም ማለቱ ተገቢ ሆኖ Aላገኘነውም፡፡ ምክንያቱም ክስ የመሠረተው በውክልናው Eንጅ ባለመብት ነኝ በማለት ስላልሆነ ነው፡፡

ፍ/ቤቱ ውሣኔ በሰጠበት Eለት “ከሳሽ ጀነነው Aሰፋ” ብሎ ይመዝገብ Aንጂ የክስ ማመልከቻው ከሳሹ (ወኪሉ) የሊቀስዩማን Aሰፋ በሻህውረድ ወኪል መሆኑን ያሣያል፡፡ ወኪሉ ወኪል መሆኑን Eስካሣየና Eስከገለፀ ድረስ በማመልከቻው ላይ የራሱን ወይም የወካዩን ስም Aስቀድሞ መፃፉም ቢሆን ወኪልነቱን ለውጦ ባለመብት የሚያደርገው Aይሆንም፡፡ በክስ  ማመልከቻው ላይ ባለመብት ናቸው ተብለው ዋነኛ የጉዳዩ ባለቤት ተደርገው በዝርዝሩ የተጠቀሱት የAሁን Aመልካች ሊቀስዩማን Aስፋ በሻህውረድ ናቸው፡፡ ይህ Eየታወቀ ወኪሉ በከሳሽነት ዘንግ ሆኖ ክስ መስርቷል በሚል ክሱ ውድቅ መደረጉ ስህተት ነው፡፡

ወኪሉ በክስ ማመልከቻው ላይ የራሱን ስም ከወካዩ Aስቀድሞ መፃፉን ፍ/ቤቱ ግልፅነት ይጎለዋል Eንኳን ብሎ ቢገነዘብ ይህንኑ Aስተካክሎ Eንዲያቀርብ ማድረግ ሲችል ክሱን ያለመቀበሉ ተገቢ ባልሆነ Aሠራር ሙግት Eንዲራዘምና ባለጉዳይ Eንዲጉላላ ማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም የሚከተለው ተወስኗል፡፡


ው ሣ ኔ

1. የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ክሱን የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33 በመጥቀስ መዝጋቱም ሆነ ከፍተኛው ፍ/ቤትም ይግባኙን መሠረዙ ተገቢ ስላልሆነ ውሣኔዎቹን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348/1/ መሠረት ሽረናል፡፡

2. የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት Aቶ ጀነነው Aሰፋ የሊቀስዩማን Aሰፋ በሻህውረድ ወኪል በመሆን የመሠረተውን ክስ ተቀብሎ ግራ ቀኙን በማከራከር ተገቢውን ውሣኔ Eንዲሠጥ ታዟል፡፡ ይፃፍ፡፡ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡

 

የማይነበብ የAምስት ዳኞች ፊርማ Aለበት