- Hits: 2104
186626 contract-sale of immovable property-registration of sale contract-right of third parties
የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የሚደረግ የሽያጭ ዉል ንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ላይ መመዝገብ እንዳለበት ህጉ ሲደነግግ ገዥዉ ዉሉ እንዲመዘገብ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ ሲቀርብ ንብረቱ በሻጭ ስም መመዝገብ አለመመዝገቡን ወይም ሻጩ ዉሉን ለማድረግ ህጋዊ መብት ያለዉ መሆን አለመሆኑን ብቻ ሳይሆን በንብረቱ ላይ ዕዳ እና እገዳ ያለበት መሆን ያለመሆኑንም ለማጣራት ዕድል ያገኛል በሚል በመሆኑ ማንኛዉም ጠንቃቃ ገዥ ዉል ሲዋዋል ተገቢዉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የሚጠበቅበት ስለመሆኑ
የባልና ሚስት የጋራ ንብረት የሆነ ቤት ያለ አንደኛው ተጋቢ ፊቃድና ስምምነት ለሦስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ በፍርድ ቤት አስቀድሞ እግድ የተሰጠበት ስለመሆኑ ንብረቱ በተመዘገበበት መዝገብ ላይ ተረጋግጦ እያለ፣ የሽያጭ ዉሉም መመዝገቡም ሆነ የሚመለከተዉ አካል ዉሉን ሲመዘግብ ወይም ሲያረጋግጥ ተገቢዉን ጥንቃቄ ሳያደርግ ቤት በሽያጭ በመተላለፉ የገዛ ሰው እንደ አንድ ጠንቃቃ ገዥ ማድረግ የሚገባዉን ጥንቃቄ አለማድረጉን የሚያሳይና አስቀድሞ የተቋቋመ የሌላ ሰዉ መብትና ጥቅም ያለበትን የማይንቀሳቀስ ንብረት በመግዛት የተደረገ ዉል ጸንቶ የማይቀጥል ስለመሆኑ
የፍትሐ ብሔር ህግ አንቀጽ 1543-1566 እና 1185