ልጅነትን ስለማስረዳት
የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 126(1) 143(መ) እና (ሠ)
Cassation 22243
Cassation Decision no. 30959
Cassation Decision no. 32130
የአንድ ሰው አባት ነኝ በሚል የሚቀርብ ሰው አባትነቱን በህግ አግባብ በማስረጃ ማስረዳትና ማረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ የአማራ ክልል የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 147(1) 97(2)
Cassation Decision no. 34149
በአባት በኩል ያለን መወለድ መቃወም የሚቻለው የልጁ አባት ነው ተብሎ በህግ ግምት የሚሰጠው ሰው እሱ የሞተ ወይም ችሎታ ያጣ እንደሆነ ከተወላጆቹ አንዱ የመካድ ክስ በማቅረብ መቃወም የሚችል ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/1992/አንቀጽ 167፣174 እና 179
Download Cassation Decision
በፌደራል የቤተሰብ ህግ መሰረት በአባት በኩል ያለን መወለድ የመካድ ክስ በማቅረብ መቃወም ስለሚችሉ ሰዎች የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 177/1-3
Download decision
የባህሪ ወሳኝ ቅጣት ( DNA) ምርመራ አንዴ ሰው የሌጁ አባት ወይም እናት አይዯሇም ሇማሇት የሚቀርብ ማስተባባያ ማስረጃ ሉሆን የሚችሌ ቢሆንም የሚከናወነው አባትነትን በሚመሇከት የመካዴ ክስ ሇማቅረብ የሚያስችለ ቀዲሚ ሁኔታዎች ሲሟለ ስሇመሆኑ እና እናትነትን በተመሇከተም በቤተሰብ ህግ ከአንቀፅ 153 እስከ 166 ዴረስ የተዘረጋው ስርዒት የሚፇቅዴ ሁኖ በፌትሃ ብሓር ስነ ስርዒት ሔጉ የተመሇከቱትን የማስረጃ አቀራረብ ስርዒቶችን መሰረት በማዴረግ ሲቀርብ ስሇመሆኑአዋጅ ቁጥር 213/1992 ከአንቀጽ 167-179
Download here
ፀንቶ ባለ ጋብቻ ውስጥ የተወለደ ልጅ አባት በጋብቻ ውስጥ ባል የሆነው ወገን ስለመሆኑና የዚህን ሰው አባትነት ለመቃወም የሚቻልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 144 126 167 168 173
ልጅነት ሊረጋገጥ የሚችልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 156 168 158 169
ልጅነትን በማረጋገጥ በፍ/ቤት የሚሰጥ ውሣኔ የህግ ግምት የሚፈጥር እንጂ አስገዳጅነት ያለው እና የመጨረሻ ማስረጃ ተደርጐ መወሰድ የሌለበት ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 154 155 156
አባትነት በፍርድ ውሣኔ ሊታወቅ የሚችልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 43
አባትነት በህግ አግባብ ሊታወቅ የሚችልባቸው ሁኔታዎች የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 126 1(1) (2),128(1) 130(2) 125 106(1), የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 35(2)
የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን ያልተገባ የንግድ ውድድርን በተመለከተ የሚነሳ ክርክርን የመዳኘት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ የንግድ አሰራር አጣሪ ኮሚሽን ተግባርና ኃላፊነት አዋጅ ቁ. 329/95 አንቀጽ 10/2/ /ሀ/, 3, 15 አዋጅ ቁ. 501/98 አንቀጽ 49 አዋጅ ቁ. 67/89 አንቀጽ 46 አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 41/2/, 52
በጋብቻ ውስጥ የሚወለድ ልጅ አባት ባል እንደሆነ የህግ ግምት ሊወሰድ የሚችልበት አግባብ የዚህ የህግ ግምት የሚቋቋምበት አግባብ እና እንደ ማስረጃ ተወስዶ በፍ/ቤት እውቅና ሊያገኝ የሚገባ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 126, 143
በጋብቻ ውስጥ የተወለድኩ በመሆኔ ልጅነቴ እንዲረጋገጥልኝ በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ህጋዊ መሰረት ያለውና ፍ/ቤቶችም ተቀብለው በፍሬ ነገር ረገድ ሊጣሩ የሚገቡትን በማጣራት መወሰን ያለባቸው ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37/1/
የልጅ አባት ነህ የተባለ ሰውን በተመለከተ የመካድ ክስ ሊቀርብ የሚችልበት አግባብ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 177/3/
አባትነትን /ልጅነትን/ ከማረጋገጥ ጋር በተያያዘ በሚቀርብ አቤቱታና ክርክር የዲኤን.ኤ (DNA) ምርመራ እንዲደረግለት በመጠየቅ ክርክር የሚያቀርብ ወገን ለዚሁ የህክምና ማስረጃ የሚያስፈልገውን ወጪ የመሸፈን ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 259/1/