- Hits: 4
192580 Intellectual Property-Trade Mark-Trade name-exclusive use right-Nice Agreement
አንድ የንግድ ምልክት በባለቤትነት ያስመዘገበ ሰው ላስመዘገበበት የዓለም አቀፍ ምድብ የንግድ ምልክቱን በብቸኝነት የመጠቀም መብት (Exclusive Right) ያለው ስለመሆኑ፤
በንግድ ምልክትነት እና በንግድ ስምነት ተመዝግቦ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ በሌላ ሰው ባለቤትነት በንግድ ስምነት ሊመዘገብ አይገባም ወይም የተመዘገበው ሊሰረዝ ይገባል የሚል ክርክር ሲቀርብ ተቃውሞ የቀረበበት አንድ አይነት ስለመሆኑ ወይም የሚመሳሰልና ህዝብን የሚያሳስት እንዲሁም የአስመዘጋቢውን መብት የሚጎዳ ስለመሆን አለመሆኑ በማስረጃ ሊረጋገጥ የሚገባ እንጂ የህግ ማዕቀፍ የለም ተብሎ የሚታለፍ ስላለመሆኑ፤
ዓለም አቀፍ እቃዎች እና አገልግሎቶች ምድብ ለመወሰን የወጣ ናይስ ስምምነት (Nice Agreement Concerning the International Classification of Goods and Services for the purposes of the Registration of Marks)፣ አዋጅ ቁጥር 813/2006፣ ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008፣ በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 እና የእነዚሁ አዋጆች ማስፈፀሚያ ደንቦች