- Hits: 4
185700 criminal law-sentencing-sentencing guideline-suspension of penalty-aggravation
የቅጣት ውሳኔ እንዳይገደብ በወንጀል ህግ አንቀፅ 194 ስር የተቀመጠው ክልከላ ባልተሟላበት ሁኔታ ተከሳሽ ክሱን ክዶ ከመከራከሩም በላይ ከተበዳይ ጋር ታርቆ ለመካስ እና የፍርድ ቤትን ወጪ ለመሸፈን የሰጠው ማረጋገጫ የለም በሚል በመልካም ጠባይ የሚመራ ለመሆኑ በፍርድ ቤት እንዲያቀርብ የሚጠየቅ የዋስትና ማረጋገጫ ትዕዛዝ ቅጣትን ለመገደብ ቅድመ ሁኔታ ተደርጎ የሚወሰድ ስላለመሆኑ
በተደጋጋሚ ወንጅል ፈጽሞ የተቀጣ ተከሳሽ አዲስ ወንጀል ፈጽሞ በተገኘ ጊዜ ፍርድ ቤት ቅጣቱን ለማክበድ በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል ከተደነገገው ጣራ ቅጣት በማለፍ የዚህን መጠን እጥፍ በመያዝ መወሰን የሚችል ቢሆንም ይህ የሚቻለው ወንጀሉ የተደጋገመ መሆኑን ብቻ በማየት ሳይሆን ጥፋተኛው የፈጸማቸው ወንጀሎች ዓይነት፣ ክብደት እና ብዛት እንዲሁም ወንጀል ለመፈጸም የነበረው የአደገኝነት መጠን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 188 (1) እና (2)፣ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 02/2006 አንቀጽ 22/2