በተዋዋይ ወገኖች መካከል ውል ባለመፈፀሙ ምክንያት የጉዳት ኪሣራ እንዲከፈል በሚል ጥያቄ በቀረበ ጊዜ በውሉ ለዚሁ ዓላማ ተዋዋዮቹ ካመለከቱት የገንዘብ መጠን በላይ እንዲከፍል ለማስገደድ የማይቻል ስለመሆኑ፣ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ቦንድ መሰረታዊ ዓላማ በውል የተመለከተው ጉዳይ እንደውሉ ስለመፈፀሙ (የሚፈፀም ስለመሆኑ) ለማረጋገጥ ስለመሆኑ፣ አንድን ዕቃ ማቅረብ ጋር በተያያዘ የተደረገ ውልን አስመልክቶ በአቅራቢው በኩል ከእቃው ዋጋ ጋር በተገናኘ በመንግስት የታወቀ የዋጋ ግሽበት መከሰቱ አቅራቢው ውሉን ሙሉ ለሙሉ ለማቋረጥ የሚያስችለው በቂ ምክንያት ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3183(2),3188(1),1731,1734,1732,1889