የፍርድ አፈፃፀም ጥያቄ በህጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ የባለዕዳው ንብረት እዳውን ለመሸፈን ባለመቻሉ በከፊል ተፈጽሞ ከቆየ በኋላ የፍርድ ባለመብት የባለዕዳውን ንብረት አፈላልጐ በማግኘት አፈፃፀሙን ለመቀጠል ሲፈልግ ይርጋ ሊቆጠር ስለሚችልበት አግባብ፣ አበዳሪ የሆነ ባንክ ከዕዳው አከፋፈል ጋር በተያያዘ በባለዕዳው ላይ የአፈፃፀም ክስ መስርቶ እንደ ፍርዱ ለመፈፀም የማይችል መሆኑ የተረጋገጠ ከሆነ በሌላ ጊዜ በባለዕዳው ንብረት ላይ በፍርድ ባለመብቱ የሚቀርበው የአፈፃፀም አቤቱታ ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የይርጋ ጊዜ መቆጠር ስለሚጀምርበት ጊዜ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 384, 329(2) አዋጅ ቁ. 97/90