አንድ የንግድ ማህበር (ድርጅት) የሚጨበጥና የማይጨበጥ እንዲሁም የሚንቀሣቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት መብቶች ምን ምን እንደሆኑ በማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ የሚወሰን ስለመሆኑ አንድ የንግድ ማህበር (ድርጅት) ሥራውን የሚያከናውንበት የንግድ ቦታ ኪራይ መብት የማህበሩ ህልውና ጋር የሚያያዝ ነው ለማለት የማይቻል ስለመሆኑ፣ የንግድ ድርጅቱ የፈረሰ ቢሆንም የንግድ ሥራውን ሲያከናውንበት የነበረውን ቦታ በሌላ ጉዳይ በፍርድ እንዲለቅ በተወሰነ ጊዜ የማህበሩ ሒሳብ ተጣርቶ አለመጠናቀቅ ቦታውን ላለማስለቀቅ ምክንያት ሊሆን የማይችል ስለመሆኑ፣