84353 civil procedure/ contract law/ loan /banking/public auction/cassation/ mortgage/ bankrupcy/

ለተሰጠ የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣ የተያዘ በኪሣራ የፈረሰ ማህበር (ድርጅት) ንብረት በሀራጁ ጨረታ የተሸጠ በመሆኑ ሽያጩ ሊፈርስ ይገባል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ እና ፍ/ቤቶችም ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ፣  በመያዣ የተያዘውን ንብረት በባንኩ በሀራጅ የተሸጠ በመሆኑ በባለዕዳው በኩል ቢሸጥ የተሻለ ዋጋ ያስገኝ ስለነበረ ሽያጩ ሊፈርስ ይገባል በማለት የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣  በህግ የተቋቋመ ባንክ በብድር የሰጠው ገንዘብ በአዋጅ ቁ.97/90 እና 216/92 መሠረት አስቀድሞ ለብድሩ አመላለስ ዋስትና ይሆን ዘንድ ከያዛቸው መያዣዎች መካከል አንዱን በመምረጥ በሐራጅ ሊሸጥ ይገባል፣ ለመሸጥ የተንቀሳቀሰበትን የመያዣ ንብረት ከመሸጥ ድርጊት ይታቀብ ይህም በፍ/ቤት ትዕዛዝ ይሰጥልን በሚል የሚቀርብ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑና በአሻሻጡ ሂደት ባንኩ ህግን ባለመከተል የፈፀመው ስህተት ቢኖርና በባለዕዳው ላይ ጉዳት ቢደርስ ግን ለዚህ ጉዳት ባንኩ ለባለዕዳው ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርበት ስለመሆኑ እና ፍ/ቤቶችም ሀራጁን ለማስቆም ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ፣  የሰበር ችሎት የሚሰጠው አስገዳጅነት ያለው የህግ ትርጉም አንድ ክርክር የቀረበበት ጉዳይ (ድርጊት) ከተፈፀመ በኋላ ስለሆነ የተሰጠው የህግ ትርጉም በጉዳዩ ላይ ተፈፀሚነት የለውም በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 394-449,224 አዋጅ ቁ.97/90 አንቀጽ 3,4 አዋጅ ቁ.216/92 አዋጅ ቁ.98/90 አዋጅ ቁ.2584

Download Cassation Decision