debt of spouses

  • Family law

    civil procedure

    pecuniary effect of marriage

    debts in the interest of house hold

    በጋብቻ ወቅት በአንደኛው ተጋቢ ምክንያት የተፈጠረ ዕዳ ለጋራ ጥቅም መዋሉ በተረጋገጠ ጊዜ የዕዳው ወደ የጋራ ንብረት ወይም ወደ ሌላኛው ተጋቢ የግል ንብረት በመሄድ ሊከፈል የሚችለው በፍርድ አፈፃፀም ላይ ስለመሆኑና ከዚህ ጋር በተያያዘ በሌላኛው ተጋቢ ላይ ዕዳውን መሠረት በማድረግ ክስ ሊመሰረትበትም ሆነ ፍርድ ሊሰጥበት የማይገባ ስለመሆኑ

    Cassation Decision no. 22891

  • ከጋብቻ በፊት የተፈራ ንብረት ላይ ያለን ዕዳ ለመወጣት ከጋብቻ በኃላ ከባልና ሚስት የጋራ ገንዘብ መከፈሉ ንብረቱን የጋራ ንብረት የማያደርገው ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 62(1) እና 7ዐ(1)

    Cassation Decision no. 35376

  • ከዳኝነት ስራ ጋር ያልተያያዙ እና የአስተዳደር ስራ ሲያከናውኑ የሚፈፀሙ የወንጀል ጥፋቶች ዳኛውን ከተጠያቂነት የማያስቀሩ ስለመሆኑ፣

    የወ/ህ/ቁ. 402(1) እና (2)

    በትግራይ ክልል ዳኞች እና ሬጂስትራሮችን ለማስተዳደር ተሻሽሎ የወጣው ደንብ ቁጥር 1/2003

    ...
  • ጋብቻ በፍቺ ውሳኔ መፍረሱን ተከትሎ በንብረት ክርክር ወቅት የግል ዕዳ ነዉ ተብሎ ውሳኔ ያገኘ ዕዳ ፍ/ቤት ቀርቦ ባልተለወጠበት ሁኔታ በባለዕዳው ተጋቢ በኩል ለመጣው እዳ ሌላኛው ተጋቢ ተጠያቂነት የሌለበት ስለመሆኑ 
    የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 34 (1)፣ የፌደራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 57፣ 70፣ 71፣ 89 እና 93 

    Download

  • ባልና ሚስት በፍቺ ከተለያዩና የንብረት ክፍፍል ከተደረገ በኋላ ከአንደኛው ተጋቢ የግል ተግባር የሚመነጭ ዕዳ አፈፃፀም የተጠየቀው /የቀረበው/ ከፍቺ በኋላ እስከሆነ ድረስ ለዕዳው ምክንያት ከሆነው ተጋቢ ብቻ የሚጠየቅ ስለመሆኑ

    Cassation Decision no. 22930

  • አንድ ተጋቢ በግሉ ያመጣው ዕዳ ከሌለኛው ተጋቢ የጋራ ንብረት እንዲከፈል የሚደረገው ዕዳውን ያመጣው ተጋቢ ዕዳውን ለመክፈል አለመቻሉ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የደቡ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ እና የፌዴራል መንግስት የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ

    Download Cassation Decision

  • በትዳር ወቅት የተወሰደ ብድር የአንደኛው ተጋቢ ፈቃድ የሌለበት ቢሆንም ፈቃዱን ያልሰጠው ተጋቢ የብድር ስምምነቱ እንዲፈርስ ያላደረገ እንደሆነ ወይም ደግሞ ለትዳር ጥቅም አለመዋሉን ማስረዳት ያልቻለ ከሆነ ለትዳር ጥቅም እንደዋለ የህግ ግምት የሚወሰድ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 68(መ)

    Download Cassation Decision

  • በባል ወይም በሚስት ለጋራ መተዳደሪያቸው በሚል ከሚካሄድ የንግድ ሥራ ማስኬጃ ጋር በተያያዘ የተገባ ዕዳ የተጋቢዎች የጋራ እዳ እንደሆነ የሚቆጠር ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ.19 የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92, አንቀፅ 70

    Download Cassation Decision