ከውርስ በዝምታ ወይም ያለበቂና ህጋዊ ምክንያት የተነቀለ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ከጠቅላላ የኑዛዜ ተጠቃሚ ጋር እኩል ወራሽ ሆኖ የሟችን የውርስ ሃብት ሊካፈል የሚገባ ስለመሆኑ “በህይወቴ ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥረውብኛል” የሚል ምክንያት በመስጠት ብቻ ተወላጅን ለመንቀል የማይቻል ስለመሆኑ ሟች ካለው ሃብት እጅግ አነስተኛ የሆነ ንብረት /ሀብት/ ለተወላጁ በኑዛዜ የሰጠ እንደሆነ በውጤት ደረጃ ተወላጁ የተነቀለ መሆኑን መገንዘብ የሚቻልና ተወላጁ ከሌሎች የጠቅላላ ኑዛዜ ተጠቃሚዎች ጋር እኩል መካፈል ያለበት ስለመሆኑ