112725 criminal procedure/ bail/ appeal by prosecutor

አቃቤ ህግ በዋስትና መለቀቅ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ ፍርድ ቤት የዋስትና መብትን የሚከለከልበቻው ምክንያቶች ከተለየዩ ሁኔታዎች በመመልከት ሊመዝናቸው የሚገባቸው ስለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር67፣75

 

የሰ/መ/ቁ. 112725 ቀን 22/02/2008 ዓ/ም

ዳኞች፡-ተሻገር ገ/ስላሴ

 

ሙስጠፋ መሐመድ ተፈሪ ገብሩ

ሸምሱ ስርጋጋ አብረሃ መሰለ

አመልካች፡- አቶ ሀሰን አብዳል ጠበቃ ገበዮህ ይርደው ቀርበዋል

 

ተጠሪ፡- የፌዴራል ማዕከል ዐቃቤ ህግ የቀረ የለም

 

መዝገቡ ተመርምሮ ተከተዩ ፍርድ ተሰትቷል

 

 ፍ ር ድ

 

በዚህ ጉዳይ አመልካች የፀና ንግድ ፈቃድ ሳይኖረው የንግድ ስራ ሰርቷል በሚል በአዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 2(3) 31(1) እና 60(1) የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት ፈፅሟል በሚል የወንጀል ክስ የቀረበበት ሲሆን ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ እየተመለከተ የነበረው ፍርድ ቤትም የአመልካቾችን ዋስትና መብት በብር 50,000 ወይም ለዚሁ ብቁ የሆነ ዋስትና ከቀረበ በኃላ ከእስር እንዲለቀቅ በሚል የዋስትና መብቱን ጠብቆለታል፡፡ ተጠሪ ቅሬታ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት በማቅረቡ ግራ ቀኙን አስቀርቦ በዋስትና ጉዳይ ላይ እነዲከረከሩ ከዳረገ በኃላ የስር ፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ በመሻር የአመልካችን ዋስትና መብት ጥያቄ ከወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 67(ሀ) አንፃር በመካልከል አመልካች ማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን ይከታተል ስል ወስነዋል፡፡ የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስላወጥ ነው፡፡

 

የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በዋስትና መፍቀድ ላይ ዐቃቤ ህግ ይግባኝ ለማለት ስልጣን አለው የሚል አንቀጽ በወ/መ/ስ/ስ/ህጉ ላይም ሳይኖር ፍርድ ቤቱ ይህንኑ ተቀብሎ አከራክሮ ዋስትናውን መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ሊታረም ይገባል፤ ዐቃቤ ህግ አመልካች በዋስትና ቢወጣ የዋስትና ግዴታውን አክብሮ አይመጣም ለማለት የቀረበው ምክንያት አድራሻ የለውም ቢፈረድበት ብዙ ዓመት ስለሚቀጣ የሚል ሲሆን አድራሻ የለውም የሚለው አመልካች አድራሻ እንዳለው የተረጋገጠና ሊረጋገጥ የሚችል በመሆኑ የዋስትና  መብት


የሚያስከለክል ሁኔታ ስለሌላ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለለበት በመሆኑ ነው ተብሎ ተሽሮ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ፀንቶ አመልካች በዋስ ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል የሚል ትዕዛዝ እንደሰጠው የመለከተው፡፡ አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ችሎት እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪም ቀርቦ መልሱን በፅሑፍ ሰጥቶአል፡፡

 

ይህ ችሎትም አመልካችና አቃቤ ህግ ያቀረቡትን የፅሑፍ ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት  ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ ተመልክቶታል፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሲቀረብ እንዲታይ የተደረገው ጭብጥ ተጠሪ በአመልካች በዋስትና መለቀቅ ላይ ይግባኝ ማቅረብ የሚችል መሆኑ ያለመሆኑን ይህ ቢታለፍ ከሆነም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝን መሻሩ ከወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 67(ሀ) እና አዋጅ ቁጥር 686 (2002 አንቀጽ 60(1) ድንጋጌ አንፃር በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም የሚለውን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህም መሠረት ጉዳዩን እንደሚከተለው ተመልክተናል፡፡

 

አቃቤ ህግ በዋስትና መለቀቅ ውሳኔ ላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ ለመጠየቅ የሚችል መሆን ያለመሆኑን በተመለከተ፡- በመሠረቱ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 75 ርዕሱ ሲታይ በዋስትና ወረቀት እንዲለቀቅ ያልተፈቀዳ ሲሆን ለይግባኝ ፍርድ ቤት ማመልካቻ ስለማቅረብ በሚል የተቀመጠ ሆኖ ዝርዝር ይዘቱ በዋስትና ወረቀት እንዲለቀቅ ያልተፈቀደለት ተካሳሽ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ማመልካቸውን ማቅረብ የሚችል መሆኑንና የጊዜ ገደቡን የሚያስቀምጥ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ድንጋጌው አቃቤ ህግ የዋስትና መብት ሲፈቀድ ይግባኝ ማቅረብ የማይችል  መሆኑን አይደነግግም፡፡ የድንጋጌው ይዘትና መንፈስ በስነ ስርዓት ህጉ ስለ ይግባኝ አቅራረብ ከተመለከቱት ድንጋጌዎችና ከወንጀል ሕጉ መሰረታዊ አላማ ሲታይ የዋስትና መብት ጠይቆ ሊከለከል የሚችለው ተከሳሽ በመሆኑ ተከሳሹ በህጉ ሊኖረው የሚችለውን የመብት ማስከበሪያ መንጋድ ለመጠቆም ተብሎ የተቀመጠ ከመሆኑ ውጭ ህጉ በማይፈቅደው አግባብ የዋስትና መብት የተከበረለት ተካሳሽ ሁሉ ዋስትና መብቱ ተከብሮለት በዋስትና ወረቀት ሲለቀቅ የወንጀል ሕጉን የሚያስፈፅመው አቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ይግባኝ ለማለት አይችልም በሚል ሊተረጎም የማይገባው መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ በመሆኑም ድንጋጌው የአቀቤ ሕግን ይግባኝ የማቅረብ መብት የማይከለክል በመሆኑ በዚህ ረግድ ይግባኝ ሰሚው ችሎት የፈፀመው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አለ ለማለት አልተቻለም፡፡

 

አመልካች ወደ ፊት ቀጠሮ አክብረው ሊቀርቡ አይችሉም ተብሎ ግምት መወሰዱን በተመለከተ፡- የስር ፍርድ ቤትም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ችሎት በአመልካች ላይ የተጠቀሰው ድንጋጌ በረሱ ዋስትና የሚከለክል አለመሆኑን የተቀባሉት ጉዳይ ነው፡፡ ይግባኝ ሰሚው ለዋስትና መከለካል ምክንያት ያደረገው በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ ቁጥር 67(ሀ) ሲሆን ፍረድ ቤቱ ይህንኑ ድንጋጌ    ተግባራዊ


ሲያደርግ ግምትን መነሻ ለማድረግ የሚችለው ሕጋዊ ስልጣን ያለው መሆኑን ነው፡፡ የዋስትና መብት መሠረታዊ የሆነ ህግ መንግስታዊ መብት ቢሆንም ፍፁም መብት ሳይሆን በሕጉ አግባብ ሊከለከል የሚችል ነው፡፡ ፍርድ ቤት አግባብነት የለውን ልዩ ህግ መሠረት አድርጎ ጉዳዩን ሊመዝነውና ተገቢውን ውሳኔ ሊሰጥበት የሚገባው ጉዳዩ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

 

የስር ፍርድ ቤት የአመልካቾች የዋስትና ጥያቄ ያልተቀበለው በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 67(ሀ) መሠረት ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ በዋስትና ወረቀት የመልቀቅ ማመልካቻ ለመቀበል የማይቻልባቸውን ሁኔታዎችን አስቀምጧል፡፡ ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን ለመከለከል ግምቱን መነሻ የሚያደርግባቸው ሁኔታዎች በተጠቀሰው ድንጋጌ በግልፅ አልተመለከቱም እንዲህ ከሆነ አንድ ተካሳሽ የዋስትና መብት ቢከባርለት ግዴታውን የሚፈፅም፣ የማይመስል ነው ተብሎ ግምት የሚወስዳው በቂና እና ህጋዊ ሊባሉ በሚችሉ ምክንያቶች ሊሆኑ ይግባል ተብሎ የሚታመን ሲሆን ምክንያቶቹ በቂና ህጋዊ ናቸው የሚለው ጉዳዩ ከተለያዩ ከባባዊ ሁኔታዎችና ከጉዳዩ ልዩ ባህሪይ አንፃር እየተየ በፍርድ ቤቱ ግንዘቤ ሊወስድባቸው የሚችላቸው ነጥቦች ናቸው ተብሎ የሚታሰብ እንጂ ቁርጥ ያለ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የሚችልባቸው ሁኔታዎች አሉ ለማለት የማይችልበት ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም የወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 67 በጠቅላላው ሲታይ ፍርድ ቤት የወስትና መብትን የሚከለከልበቻው ሁኔታዎች የሚያሰይ ሲሆን ምክንያቶችን ፍርድ ቤቱ ከተለየዩ ሁኔታዎች በመመልከት ሊመዝናቸው የሚገባቸው ሲሆን የድንጋጌው ቅርፅ ይዘትና መንፋስ ሲታይ በሁኔታዎቹ ግምት የመውሰድ የለመውሰድ ጉዳይ የስር ፍርድ ቤት ስልጣን (Discretion) መሆኑን ያሰያል በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 59304 በቀረበው ጉዳይ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) መሠረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤት የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቶአል፡፡

 

ወደ ተያዘው ጉዳይ ስንመለስም ይግባኝ ሰሚ ችሎት የአመልካችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ቢወጣ የዋስትናውን ግዴታ አክብሮ ይገኛል ለማለት የሚችል አይደለም በሚል ምክንያት ነው፡፡

 

ይህ ግምት መሠረቱ በአመልካች ቋዋሚ አድራሻ አለመኖር ሳይሆን ትኩረት የተሰጠው በአመልካች ላይ የተመሰረተው ክስ ሊያስከትል ከሚችለው የእስራት ቅጣት ከፍተኛነትና ከወንጀሉ ልዩ ባህሪይ መሆኑ መገመቱን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ላይ ገልፀዋል፡፡

 

ፍርድ ቤቱ በእነዚህ ምክንያቶች ላይ በመመስረት ዋስትናውን ከልክለዋል፡፡ እነዚህን ምክንያቶች ለግምቱ መነሻ እንዲያደርግ ደግሞ ከላይ እንደተገለፀው በህጉ የተከለከለ ካለመሆኑንም በላይ ግምት የመውሰድ ጉዳይ በህጉ ለፍርድ ቤቱ ስልጣን የተሰጠው ነው፡፡ ግምቱ በቂ ነው ወይም አይደለም የሚለው ክርክር ደግሞ የጠቅላላ ሁኔታዎች ምዘና ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ሰበር


ችሎት ደግሞ በኢፌ/ዲ/ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3) ሀ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988   አንቀጽ 10 መሠረት የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለበትን ማንኛውንም የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ የማስረጃና የሌሎች ክባቢያዊ ነገሮችን ምዘና ጉዳይ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን አይደለም፡፡ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ግን ፍሬ ነገሩን የማጠረትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ስላለው ይህ ችሎት የክርክር አጠቃላይ በህሪይ መሰረት በማድረግ የሚዘው ድምዳሜ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ነው ሊባል የሚቸልበት አግባብ የለም፡፡ ስለሆነም ይጋባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በኢ/ፌ/ዲ/ሪ/ ህገ መንግስት አንቀጽ 19(6) እና የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 67(ሀ) መሠረት የሰጠው መሳኔ ሕጉ የተሰጠውን ስልጣን መሰረት ያደረገ እና በሕጉ አተረጋጓም አተገባበር ረገድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም፡፡ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

 

 ው ሳ ኔ

 

1. የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 110478 መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓ/ም መተሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 75(2) መሠረት ፀንቷል፡፡

2. አመልካች ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆኖው እንዲከታተሉ ተብሎ መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

 

 


 

 

ሩ/ለ


የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡