አንድ ፍ/ቤት ክስ ቀርቦለት ጉዳዩን የማየት ሥረ ነገር ስልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን የዘጋው እንደሆነ ዋናውን ክርክር እንዳላየ የሚያስቆጥር ሲሆን የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.5፣9 እና 231 በመዝገቡ ላይ የሰጣቸው ማናቸውም ትእዛዞች በማናቸውም ወገን ላይ ህጋዊ የሆነ አስገዳጅነት ውጤት የሌለውና በዚሁ ጉዳይ ለሚመለከተው ፍ/ቤት መዝገቡ ቢቀርብ ከዚህ ቀደም በፍርድ ያለቀ ነው ሊያስብል የማይችል ስለመሆኑ