ገንዘብን በአደራ የማስቀመጥ ዉል (deposit fund) መነሻነት አደራ ያስቀመጠ ባንክ የአደራ አስቀማጩን ገንዘብ የመጠበቅ፣ ሲጠይቁ ወጪ አድርጎ የመክፈል እና ከአስቀማጩ ዉጪ ለሌላ ሰዉ ያለመክፈል ከዉል የመነጨ ግዴታ ሲኖርበት ይህን ግዴታውን ባይወጣ አስቀማጩ ላይ ሊደርስ ለሚችል ጉዳት ከዉል የመነጨ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ባንኩ የሚቀርብለትን የክፍያ ጥያቄ ሲያስተናግድ፣ገንዘብ እንዲከፈለዉ ጥያቄዉን ያቀረበ ሰዉ በርግጥም አደራ አስቀማጩ መሆን አለመሆኑን በቅድሚያ የማረጋገጥ ግዴታ የሚኖርበት ስለመሆኑ
የንግድ ህግ 896 እና 897