በፍትሀ ብሄር ሥነ-ሥርዓት ህግ ከአንቀጽ 342-344 ያሉት ድንጋጌዎች በሥረ-ነገረ ታይቶ የተወሰነ ጉዳይ በተቻለ መጠን ወደ ሥር ፍርድ ቤት ሳይመለስ ጭብጡን በይግባኝ ሰሚ ችሎት በኩል እንዲለወጥ ተደርጎ ክርክሩ እንዲቋጭ የሚያዝ፣ መጣራት የሚገባው ነገር ካለ ግን ግራ ቀኙና ማስረጃዎች በቅርብ በሚገኙበትና ጉዳዩ በተጀመረበት ፍርድ ቤት እንዲታይ እድል የሚሰጥ፤ የተጣራው ውጤት ሲቀርብም አዲስ የይግባኝ መዝገብ ሳይከፈት ቀድሞ በተመለሰበት መዝገብ ተጠቃሎ ፍርድ የሚሰጥበት እንጂ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩ እንደገና እንዲጣራ በሠጠው ውሳኔም ሆነ የሥር ፍርድ ቤት አጣርቶ በደረሰበት ድምዳሜ ላይ የይግባኝም ሆነ የሠበር አቤቱታ የማይቀርብበትና ተጠቃሎ ሲመጣ በሠበር አቤቱታ የሚታይ ስለመሆኑ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343 መሠረት ይግባኝ የቀረበለት ፍርድ ቤት ጉዳዩ በፍሬ ነገር የሚጣራና የሥር ፍርድ ቤት እንዲመለከተው የሚመለስ ከሆነ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ፍርድ የሚሰጥበት ሳይሆን ተጣርቶ እንዲቀርብለት ባዘዘው መሰረት የሥር ፍርድ ቤት አጣርቶ እስኪልክ ውጤቱን የሚጠብቅበትና መዝገቡን ለጊዜው በመዝጋት ውጤቱን መላክ እንጂ ጉዳዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤት እንደ አዲስ እንደገና በሕግ አግባብ የመሠለውን እንዲወስን መመለስ የሥነ-ሥርዓት ሕጉ ከሚያዘው ውጪ ስለመሆኑ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት የሥር ፍርድ ቤት ጉዳዩን እንደገና ተመልክቶ ማስረጃ በማጣራትና ተገቢ ያለውን እርምጃ በመውሰድ ለመለሰለት ፍርድ ቤት አባሪ በማድረግ የሚመለስበት ሥርዓት ማስረጃ ማጣራትና መመዘን የሚጠይቅ ተግባር ከሆነ ሰበር ሰሚ ችሎት ይህን የማድረግ ሥልጣን ስለሌለው የሥር ፍርድ ቤት አዲስ ያጣራውን አባሪ አድርጎ ሳይልክ ቀድሞ ከተሰማው ማስረጃና ክርክር ጋር አጣምሮ እንደ አዲስ ውሳኔ የሚሰጥበት እንጂ ለሰበር ችሎት ሊመለስ የማይችል ስለመሆኑ